Wednesday, May 14, 2014

አምነስቲ በኦሮምያ ግድያ የፈጸሙት ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠየቀ

-አለምአቀፉየሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። በመዳ ወላቡ ዩኒቨርስቲ 3፣ በጉደርና በአምቦ ከ15 በላይ ሰዎች መገደላቸውን አውስቷል::አብዛኞቹ ሟቾች ተማሪዎች እና መምህራን መሆናቸውን የተለያዩ የአይን እማኞችን በማነጔገር  በሪፓርቱ ያሰፈረውአምነስቲየሟቾች ቁጥር በገለልተኛ ወገኖች ቢጣራ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችልም ገልጿል።
ከሟቾች መካከል የ11 አመት ህጻናት እንደሚገኙበት የገለጸው አምነስቲ፣ መንግስት ከሚገባው በላይ ሃይል መጠቀሙንም ጠቁሟል።
በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች የታሰሩት ሰዎች ቁጥር በሺዎች እንደሚቆጠር የኦሮሞ ፌደራሊስት ንቅናቄን በዋቢነት ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ አካባቢዎችና በዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጸጥታ ሃይሎችን ማሰማራታቸውን አምነስቲ አክሎ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት_የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት ከልክ ያለፈ የሃይል እርምጃ በገለልተኛ ወገኖች እንዲጣራ እንዲያደርግ አንዲሁምአጥፊዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡና የታሰሩት  እንዲፈቱ  ድርጅቱ ጠይቋል።
ኢሳት ዜና 

Thursday, May 8, 2014

ተዋርዶ መገዛት ይብቃን!

የወያኔ ሹማምንትና አደርባይ ሎሌዎቻቸው አንገቱን አስደፍተው የሚገዙትንና የሚዘርፉትን ህዝብ ይበልጥ ስብእናውን አዋርደው ሊገዙት ለምን እንደሚፈልጉ የማይገባን ጥቂቶች አይደለንም። እነዚህን ግፈኞች ቀረብ ብሎ ላያቸው ግን ይህ ድርጊታቸው እንቆቅልሽ አይደለም።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝብ አይሰማንም ብለው በር ዘግተው ከሚያካሂዷቸው ጉባኤዎች እያፈተለኩ የሚወጡ የቪዲዮና የድምጽ መረጃዎች የነዚህን ግፈኞች ስነ ህሊና ግልጽ አድርገው ያሳያሉ።
ከወራት በፊት የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሀገር ሽማግሌ ሰብስቦ የወያኔ አላማ ከእሱ ጎሳ ጋር ተባብሮ ሌላውን ብሄረሰብ የበታች አድርጎ መግዛት መሆኑን ሲናገር የሚያሳይ ቪዲዮ ተመልክተን ነበር። የክልሉን ህዝብ የሚጨፈጭፈው ለዚህ ሲባል መሆኑን ለማሳመን ነበር በሩን ዘግቶ የተናገረው።
ሰሞኑን ደግሞ አንድ የአማራ ክልል የወያኔ ሹምና ሎሌ አንደ እንደሶማሌ ሹም ካድሬዎቹን ሰብስቦ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቀ፤ ለ እግራቸው ጫማ የላቸውም በሚላቸው የአማራው ተወላጅ ላይ ለሰሚ በሚሰቀጥጥ ቋንቋ ያወርደው የነበረ ስድብ የሚነግረን ተጨማሪ ነገር ተመሳሳይ የወያኔን ምንነትን ነው።
እነዚህ ግፈኞች በህዝብ ላይ የሚሰሩትን አዋርዶ የመግዛት ግፍና ዝርፊያ አሳምረው ያውቃሉ። ከዚበላይ ደግሞ የዚህ ሁሉ ንቀትና ጥላቻ ሰለባ የሆነው ህዝብ እንደሚጠላቸውና ቀን እንደሚጠብቅላቸው ያውቃሉ። ስለዚህም ህዝቡን ይፈሩታል። ከፍርሃታቸው የሚያስታግስላቸው ህዝቡን ይበልጥ ቅስሙን ለመስበር ከቻሉ ስለሚመስላቸው በተዘጋ ቤት ውስጥ እየተሳለቁ ያስጨበጭባሉ።
የወያኔ ሹማምንት የህዝብ ብሶትና እሮሮ ማየሉን ሲሰሙ መልሰው ህዝቡን የሚሰድቡትና የሚያጠቁት፣ እንዲሁም ግንቦት 7 ሲጠነክርባቸውና የመውደቂያ ቀናቸው ሲያስቡ አሸባሪ ብለው የሚሸበሩትም ለዚህ ነው።
ህዝቡ ቅስሙ ከተሰበረ ሰላም ያገኙ ይመስላቸዋል። ወያኔዎችና የሲቪል ሰርቪስ ሎሌዎቻቸው በር ዘግተው በተሰበሰቡ ቁጥር ይህንን ፍራቻቸውን የሚያስታምሙት ህዝቡን ቅስሙን መስበራቸውን ለማረጋገጥ በሚያካሄዱት ወይይት ነው። ለዚህ ነው ህዝባችን እርስ በርሱ የሚባላበትን፤ እርስ በርሱ ጎሪጥ የሚተያይበትን መንገድ ሲቀይሱ የሚውሉት በዚህ ምክንያት ነው።
ወያኔዎች በየክልሉ እንደ አለምነው መኮነን አይነት ከጭንቅላታቸው፣ከህሊናቸው ይልቅ አፋቸው የሚቀድም ጥራዝ ነጠቅ ሎሌዎችን የሚያሰማሩትም የህዝብን ቅስም የሰበሩ አየመስላችዉ ነው::
 ወያኔና ሎሌዎቹ ህዝብየሚያታልሉበት ካርድ ከእንግዲህ አልቋል። አዋርደውናል፣ ገድለውናል፣ አስረውናል፣ አስርበውናል፣ ለስደት ዳርገዉናል፣ አለያይተውናል። ከዚህ በላይ ምን ሊያደርጉን ይችላሉ? ስለዚህ ቀኑ መሽቶባቸዋል እናበፍጥነት  ሊወገዱ ይገባል
በዚህ ወሳኝወቅት ሁሉምየኢትዮጵያእንደ አንድ ህዝብ በአንድ ላይ በመነሳት የወያኔ ጉጅሌና አጎብጓቢ ሎሌዎቻቸው ያዘጋጁልንን ወጥመድ መስበርና ክብራችንን ማስመለስ ይኖርብናል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተዘጋው የወያኔ በር እየተዋረደ፣ እየተገረፈ ነውና።
ግንቦት 7 እንደሁልግዜው ዘላቂ መፍትሄ የሆነው ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን እንዲጎለብት፣ ማንነታችን ክብራችን እንጂ መሳለቂያ እንዳይሆን በተባበረ ሃይላችን የክብራችን ባለቤት እንድንሆን ጥሪውን ያቀርባል።
በተባበረ ሃይላችን ክብረ-ስብእናችንን እናስመልስ! ተዋርዶ መኖር ይብቃን! በቃ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

የዞን ዘጠኝ ጀግኖች ብረሳችሁ ታሪክ ይርሳኝ” በውቀቱ ስዩም

ነጻነትና ፍትህ በሌሉበት አገር ውስጥ የልማት አውታሮችን መገንባት የት ለመድረስ ነው?የባቡር ሀዲድ ግንባታ ሳይ፣ የሚመጣብኝ እንደ አይሁድ በባቡር ታጭቀው ወደ መግደያ ጣቢያ የሚጓጓዙ ዜጎችን ነው። የኤሌክትሪክ ግንባታ ሳይ የሚመጣብኝ የኤሌክትሪክ መግደያ ወንበር ነው። የሚቆፈር ነገር ሳይ ድቅን የሚልብኝ የጅምላ መቃብር ነው።
የዞን ዘጠኝ ጀግኖች ብረሳችሁ ታሪክ ይርሳኝ። ባንድ በኩል የዘመናችሁ ተካፋይ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል። በሌላ በኩል፣ የመከራችሁ ተካፋይ ባለመሆኔ ሐፍረቱን አልችለውም። ያም ሆኖ ‹‹በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዛው ነው። ወትሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው›› የሚለው የዓለሙ አጋ የበገና እንጉርጉሮ ባጸደ-ነፍስ ላሉት ብቻ ሳይሆን ባጸደ-ወህኒ ላሉትም ይሆናል። ስሜቴን እንዴት መግለጽ እንዳለብኝ አላቅም። የገላውድዮስ ዜና- መዋእል ጸሐፊ በዚህ ሰዓት የሚሰማኝ ስሜት ከምእተ አመታት በፊት ተሰምቶት ነበር።
መዓልትኒ ኮነ ሌሊተ፣ዘኢነአምሮ ወጽልመት ዘኢልማድ መጽአ
ወደፈነ እንስሳ ወሰብአ
(ቀኑ ሌሊት ሆነና፣ ወጋገኑ ተሰደደ
እንግዳ ጨለማ መጣ፣ጠባዩ ያልተለመደ
ሰውን፣ እንስሳን ጋረደ)    በውቀቱ ስዩም (በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)