Thursday, October 30, 2014

ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!

ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!
ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡ በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡
የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡
በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡
ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-
1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡
2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡
3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡
4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡
5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡ በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም
ሰማያዊ ፓርቲ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

Wednesday, October 29, 2014

በቦሌ የድምጻችን ይሰማ መፈክሮች በሌሊት ተጽፈው አደሩ

የፌደራል ፖሊሶች ሰኞ እለት አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል በማለት በቦሌ አካባቢ ፍትሻ ባደረጉ ምሽት መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳውን ጥያቄ እንዲመልስ የሚጠይቁ መፍክሮች  በቦሌ ወሎ ሰፈርና በደንበል አካባቢዎች ተጽፈው አደረዋል።  መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም፣ ድምጻችን ይሰማ፣ በመንግስታዊ ጥቁር ሽብር ተስፋ አንቆርጥም የሚሉ መፈክሮች በየመንገዱ ተለጥፈው ታይተዋል።
ተመሳሳይ መልእክት የያዙ መፈክሮች ከዚህ ቀደም በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሌሊት ተለጥፈው ታይተዋል። መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ በሃይል ለማዳፈን ሙከራ ቢያደርግም ተቃውሞው ውስጥ ለውስጥ እየተካሄደ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲል ዘገባውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።
የድምጻችን ይሰማ መሪዎች የፍርድ ሂደት በሰበብ አስባቡ እየተጓተተ መሆኑ መዘገቡ ይታወቃል።
 ኢሳት ዜና 

Monday, October 27, 2014

ባነሰ ወጪ ድልን መቀዳጃ አመቺ ጊዜ ላይ ነን – እንጠቀምበት!

በአለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምንም የማይገናኙ እና የተመሰቃቀሉ የሚመስሉ፤ በጥልቀት ላያቸው ግን የተያያዙና የተደጋገፉ ከመሆናቸው አልፎ እንደከዋክብት ፈለግ አቅጣጫን የሚያመላክቱ በርካታ ክስተቶች ተስተውለዋል። የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን ሳንጠብቅ አንዳንዱን ለአብነት ያህል እናንሳ።
በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የዘነበው የዘለፋና የዛቻ ውርጅብኝ ህወሓት በቀጥታ በማይቆጣጠራቸው ማኅበራት ላይ ሁሉ ሲደርስ የቆየው ነፃ ማኅበራትን የማፍረስ ዘመቻ አካል መሆኑን መገንዘብ ቀላል ነው። ህወሓት የእስልምና እምነት ተከታዮችን ነፃ ማኅበርን በቁጥጥሩ ውስጥ ካስገባ በኋላ ፊቱን ወደ ክርስትና በተለይም ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማዞሩ የተረጋገጠ ነገር ሆኗል። ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ ማንም ከጥቃት እንደማያመልጥ፤ ለምንም ጉዳይ ይቋቋም ወያኔ የማይቆጣጠረው ማኅበር እንዲኖር የማይፈልግ መሆኑ ከዚህ በፊት የሚታወቅ ቢሆን በድጋሚ ማረጋገጫ የሰጠበት አጋጣሚ ሆኗል።
በመዠንግር ከአስራ አምስት በላይ የሥርዓቱ ታጣቂዎች ከነመሣሪያዎቻቸው አገዛዙን ክደው ጠፍተዋል። የጠፉትን ለማደን የመጡ ወታደሮች ደግሞ ከሕዝቡ ጋር በፈጠሩት ግጭት በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በዚህ ግጭት ብቻ ከ40 በላይ ወታደሮች መገደላቸው ይነገራል። በጋምቤላ እና በቤንሻንጉልና ጉሙዝ ወረዳዎች ውጥረት ሰፍኗል። ከመሃል አገር ሄደው ኑሮዓቸውን እዚያው ያደረጉ ዜጎች ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርስባቸው አፈናና እንግልት ጨምሯል። ግድብ እየተሠራበት ነው በሚባለው አካባቢም ከአሁኑ የፀጥታ ችግር እየደረሰ መሆኑ መረጃዎች ይጠቅማሉ። ወያኔ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን ውስጥ የገባበት ዓይነት ማጥ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያም እየመጣ መሆኑ አመላካች ነው። የመከላከያ ሠራዊት አባላት መፍለስና የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል የእለት ለእለት ትዕይንት እየሆነ ነው። ወያኔ በመሃል አገር በሙስሊም እና በክርስቲያን ወገኖቻችን የእምነት ማኅበራት ላይ በከፈተው ግንባር “ጠብ ያለሽ በዳቦ” ሲል ዳር ዳሩን ሠራዊቱና ሕዝቡ ለማይቀረው ፍልሚያ እየተዘጋጁ ነው።
በርካታ ጋዜጠኞችና አሳታሚዎች ለስደት ከተዳረጉ ጥቂት ሣምታት በኋላ “የሚመጣውን ሁሉ አገሬ ውስጥ ሆኜ እቀበላለሁ” ያለውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ አሳዛኝም አስቂኝም በሆኑ ክሶች ጥፋተኛ ተብሎ ወደ ወህኒ ተግዟል። በጋዜጠኞች ሕይወትና ሞት ወያኔ የፓለቲካ ቁማር መጫወቱ አጠናክሮ ቀጥሏል። በአንፃሩ ደግሞ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያን አምርረዋል። የወያኔ ሹማምንት በአሜሪካ እና አውሮፓ የሚዘዋወሩት በሰቀቀን ሆኗል፤ በየደረሱበት ውግዘትና ውርደት ይጠብቋቸዋል። የወያኔ ሹማምንት በኢትዮጵያዊያን የተጠሉና የረከሱ ተደርገዋል።
የዩ.ኤስ. አሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኢትዮጵያ ቴሌቬዥን ባላነሰ ወያኔን በልማት አምጭነት አሞካሽተዋል። የአውሮፓ መንግሥታት በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ወያኔን እየተቹም ቢሆን ወያኔ በሚሰጣቸው ቁጥር እየማለሉ “እውነትም ልማት እየተፋጠነ ነው” በሚል ተስፋ ማበረታቻ እየሰጡት ነው። በዚህ ደስታ አቅሉን ያጣው ኃይለማርያም ደሣለኝ የውሸት ቁጥሮችን የመፈብረክ ሥራ ከስታትስቲክስ ጽ/ቤት ነጥቆ የራሱ የሥራ ድርሻ አድርጎታል። በዚህ አዲሱ ሥራውም ውጤት እያስመዘገበ ነው። ሁለት መቶ አምሳ (250) ሚሊዮን ኩንታል ሰብል አመረትን ባለ በሶስት ወሩ ሶስት መቶ (300) ሚሊዮን ኩንታል አመረትን በማለት በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ የ20 በመቶ የግብርና ምርቶች የውሸት እድገት ፈጥሯል።
የውሸት ቁጥሮች ፈጠራ እንዲህ ቢፋፋምም፤ ቁጥሮቹን የሰሙ ኦባማ፣ የአውሮፓ መንግሥታት ሆነ ዓለም ባንክ ቢያወድሱትም አገር ውስጥ ያለው ሀቅ አልቀየረም። ስኳር፣ ዘይት፣ እንቁላልና ሌሎች የምግብ ግብዓቶች የደረሱት የሚያውቅ ጠፍቷል። ውሃ የለም፤ መብራት የለም፤ ኔት ዎርክ የለም። የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በመቸውም በባሰ መጠን በነዳያን እና በቤት አልባ በረንዳ አዳሪ ዜጎች ተጥለቅልቀዋል። ድህነት ከጎጆዎች ወጥቶ ጎዳናዎች ላይ ፈሷል። የገንዘብ ዋጋ ወርዶ ወርዶ ብር ቁራጭ ወረቀትን ማከል አቅቶታል። በጥቂት በዝርፊያ በደለቡ የህወሓት ሹሞችና በብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት ማነፃፀር እንኳን እንዳይቻል ሆኖ ተራርቋል።
የመከላከያ ሠራዊት አባላት በኑሮም በዘረኝነትም እየተማረሩ ነው፤ አለቆቻቸው ግን አሁንም በዝምድና እየተፈላለጉ እየተሿሿሙ ነው። አሁንም በዝምድና እየተፈላለጉ እርስ በራሳቸው እየተሿሿሙ ጄኔራሎች ሁሉ ዘመዳሞች ሆኑ፤ በሥራቸው ያለውን ኢትዮጵያዊውን ወታደር ግን እንደ ግል አሽከራቸው እንኳን ማየት ተጠይፈዋል። በጄኔራሎችና በሠራዊቱ መካከል ያለው ግኑኝነት ከጌታና ሎሌም የባሰም ሆኗል።
እነዚህ ምስቅልቅል ያሉ ሁኔታዎች ምንን ያመለክታሉ?
እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ምስቅልቅል ያሉ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ የተነተነ ሰው በምስቅልቅነታቸው ፋንታ ሥርዓት የያዙ ፈለጎችን ያገኛል። ከእነዚህ ፈለጎች አንዱ የሚያመላክተው መጪዎቹ ጥቂት ወራት ለኢትዮጵያ ወሳኝ ጊዜያት እንደሚሆኑ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ምስቅልቅል ውስጥ ያለው ወያኔ ነው። ወያኔ፣ በድንገት አዕምሮዉን እንደሳተ ሰው ይይዘው ይጨብጠው ጠፍቶታል። በዚህ ምስቅልቅል ወቅት ውስጥ በቢሊዮን የሚገመት የሕዝብ ሀብት አውጥቶ፤ የማይረቡ ድርሳናትን ጽፎ የአገሪቱን ዜጋ በሙሉ ካላሰለጠንኩ ሞቼ እገኛለሁ ማለቱ ራሱ የውስጡን መመሰቃቀል ማሳያ ነው። ስልጠናውን ሰልጣኞች ብቻ ሳይሆን አሰልጣኞችም ጭምር የጠሉት ቢሆንም ፋታ የሚሰጠው መስሎት ገፍቶበታል። የነፃነት ኃይሎች በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ኃይላችንን አሰባስበን ከገጠምነው ባነሰ ወጪ ድልን መቀዳጃ አመቺ ጊዜ ይሆናል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያለንበት ወቅት ወሳኝነት በመገንዘብ ከመሰል ድርጅቶች ጋር ውህደት በመፍጠር፤ ከሌሎቹ ጋር በጥምረት ትግሉን ለማፋጠን ቆርጦ ተነስቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የወቅቱን ልዩ ባህሪ በመገንዘብ በአንድ ልብ ለትግል እንዲነሳ ግንቦት 7 ጥሪ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
አባይ ሚዲያ

Sunday, October 26, 2014

የወያኔ ወሮበላ ዲፕሎማሲያዊነት፣

እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩ በጠረጴዛ ውይይት እና የሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካ በመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትናበማድረግ በንጹሀንዜጎች ደም ላይ ተረማምዶ የጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በኃይልበህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘው የሽፍታ ቡድን የበላይነትየሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥአካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት አምባገነን እና አረመኒያዊስብስብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስገልጽቆይቻለሁ፡፡ ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊአስተዳደር ከሆነ የወሮበላ አገዛዝ መንግስትደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እናለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያ ቡድን ነው፡፡
በዚህች ትችቴ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እያራመደ ያለውን የሀገር ውስጥየዲፕሎማሲፖሊሲ ለመቃኘት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ትኩረት በማድረግ ለመዳሰስ የምሞክረውህዝባዊ ወያኔ ሀርነትትግራይ የተባለው የወሮበላ ስብስብ ቡድን በማራመድ ላይ ያለውን ዓለምአቀፍ የዲፕሎማሲ ፖሊሲንለመቃኘት ነው፡፡ በቅርቡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ አረመኒያዊ እና ግልብ መንፈስየተጠናወተው አንድ የጦር መሳሪያ ታጥቆ ኢትዮጵያውያን/ት ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ተኩሶ ለመግደልበርካታ ጥይቶችን ሲተኩስ የነበረውን እና ለግድያሀራራው ሳይሳካለት የቀረውን የወያኔ ወኪል ለመግለጽየወሮበላ ዲፕሎማሲ እና የወሮበላዲፕሎማት የሚሉትን ቃላት እጠቀማለሁ፡፡
እንደ ሬውተርስ የዜና ወኪል አገላለጽ ‘ባለጠመንጃው ሰው’ እየተባለ ይጠራ የነበረው በአሜሪካየኢትዮጵያኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደጅብራ ተገትሮ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዎቻቸውንለማቅረብ ወደኤምባሲው ቅጥር ግቢ በሄዱት በንጹሀን ኢትዮጵያዊያን/ት ዜጎች ላይ ሲተኩስየነበረው በስም ሰሎሞንታደሰ ገብረስላሴ የተባለው የወያኔ ባለሙሉ ስልጣን የደህንነት አታሼነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር29/2014 የተደረገው የሰሎሞን ገብረስላሴ አስደንጋጩ እናአሳፋሪው የእሩምታ ተኩስ ጉዳይ በዓለምአቀፉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮበክብር እና ሞገስ ሳይሆን በቅሌት እና በውርደት፣በጥበበኛነት እና በምሁርነት ሳይሆንበጅላጅልነት እና በደንቆሮነት፣ በታጋሽነት እና በአርቆ አስተዋይነትሳይሆን በግልፍተኝነት እናበቅርብ አሳቢነት ሲታወስ ይኖራል፡፡
እንደ ሬውተርስ የዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ “የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ቃል አቀባይ ከቀኑበ12፡15ሰዓት በሰሜናዊ ምዕራብ ዋሺንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ ተኩስእንደተሰማ ፖሊስ በስፍራው በመገኘት ተኳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ እስርቤት ልኮታል፡፡ የዓይንእማኞች እንደገለጹት ከሆነ የጥይት ተኩሱ የተከናወነው ሰላማዊተቃዋሚዎች ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢበተጠጉ ጊዜ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነውብለዋል…“
“የወያኔን ኤምባሲ መውረር”
በሰላማዊ ተቃዋሚዎች የተወሰዱ በርካታ የቪዲዮ ክሊፖች እንደሚያስረዱት እና የኢትዮጵያሳቴላይትቴሌቪዥን/ኢሳት አገልግሎት እንዳመለከተው በቅርቡ በኢትዮጵያ በኦጋዴን እናበጋምቤላ ክልሎች በወያኔገዥ አካል ታጣቂዎች በንጹሀን ዜጎች ላይ የተወሰደውን አረመኒያዊጭፍጨፋ እና ግድያ በማስመልከትበኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ተቃውሟቸውንለመግለጽ እና የወያኔው አምባሳደር ከሆኑትከአቶ ግርማ ብሩ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ የፊት ለፊትውይይት ለማድረግ በሄዱት የሰላማዊ ተቃዋሚ ቡድንግለሰቦች ጥያቄ ማቅረብ ምክንያት ነበር፡፡
አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ ከወሰደው የቪዲዮ ክሊፕ እንደሚታየው ሰላማዊተቃዋሚዎችበመጀመሪያ ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ ለመግባት ሲያደርጉ የነበረውን ሁኔታ በግልጽያመለክታል፡፡የተወሰደው የቪዲዮ ምስል የተሰባሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በኤምባሲው ቅጥር ግቢበመግባት በግቢውውስጥ ባለ መቀመጫ ቦታ ላይ የደረሱ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ የኤምባሲውሰራተኞች ለደህንነት ተብሎከታጠረው መስታወት በስተጀርባ ሆነው በመመልከት ላይ ነበሩ፡፡ሰላማዊ ተቃዋሚዎች አምባሳደሩንማነጋጋር እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ በርካታዎቹ ሰላማዊተቃዋሚዎች ድምጻቸውን ከፍ በማድረግጩኸት በማሰማት መፈክሮችን ያስተጋቡ ነበር፡፡ከመካከላቸው አንዱ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “ይህየወያኔ ኤምባሲ እንጂ የኢትዮጵያ ኤምባሲአይደለም፡፡“ ሌላኛው ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ የሚልጥያቄ አቀረበ፣ “ከአቶ ግርማ ብሩ(ከወያኔው አምባሳደር) ጋር ለመነጋገር እንፈልጋለን፡፡ ከእርሳቸው ጋርስለኦጋዴን፣ ጋምቤላ እናስለአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ መወያየት እንፈልጋለን፡፡“ ሌሎች ሰላማዊተቃዋሚዎች ደግሞየአንዳርጋቸው ጽጌ (ከጥቂት ወራት በፊት በወያኔ ገዥ አካል ከየመን ተጠልፈው ወደኢትዮጵያከተወሰዱት የግንቦት 7 የአመራር አባል) ምስል ያለበትን ቲሸርት በመልበስ እርሳቸውከእስርእንዲፈቱ ሲጠይቁ ነበር፡፡ ሌላ አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣“እስክንድርነጋ (በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው እና  በወያኔ ገዥ አካል የ18ዓመታትእስራት ተበይኖበት በአሁኑጊዜ ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት በመማቀቅ ላይ የሚገኘው)ጋዜጠኛ ይፈታ“ ሌላው ማንነቱበውል ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህ በማለት ጨኸትሲያሰማ ነበር፣ “በጎሳ ክፍፍል አገዛዝ ታመናል፣እናም ሰልችቶናል“ በግልጽ እንዲህ የሚል ጥያቄአቅርቦ ነበር፣ “በእንደዚህ ያለ ወሮበላ አገዛዝ እስከ መቸድረስ ነው ስንገዛ የምንኖረው? እኛታመናል፣ እናም በዘራፊዎች እና በወሮበሎች መገዛት ሰልችቶናል!“
በኢሳት የተወሰደ የቪዲዮ ምስል እንደሚያሳየው ሁሉም ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙት ነገሮችሁሉከኤምባሲው ቅጥር ግቢ የተከናወኑ መሆናቸውን ነው፡፡ ከአራት ሰላማዊ አመጸኞች መካከልአንደኛውየኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ የያዘ ሲሆን ጥቁር ልብስ ወደ ለበሰው እና መሳሪያወደታጠቀው ገብረስላሴየሚባል የኤምባሲው አታሼ ሲቀርብ ያሳያል፡፡ ወዲያውኑም ገብረስላሴበማነጣጠር ወደ ሰላማዊተቃዋሚዎች አቅጣጫ መተኮስ ጀመረ፡፡ ሆኖም ግን ዒላማውን ስቷል፡፡ሰላማዊ አመጸኞች ያለምንምፍርሀት ወደ ገብረስላሴ መቅረብ ጀመሩ፡፡ ማንነቱ በውል ያልታወቀአንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህበማለት ድምጹን ከፍ በማድረግ በድጋሜ ጩኸቱን ማሰማትጀመረ፣ “እኛ ወንጀለኞች አይደለንም፣ ግርማብሩን ጥሩልን፣ ከእርሳቸው ጋር ለመነጋገርእንፈልጋለን፡፡“ ሌላው ሰላማዊ ተቃዋሚ ገብረስላሴን በድፍረትእንዲህ ይለው ነበር፣ “ወደ ፊትቀጥል፡፡ ተኩስ!“ በዚህን ጊዜ ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊተቃዋሚዎች በማነጣጠር እነርሱንስሜታዊ እንዲሆኑ በመገፋፋት ወደ ኤምባሲው ዋና ህንጻ በመግባትየሽሽት ሙከራ ማድረግጀመረ፡፡ በዚህ ሂደት ላይም ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችበመደገን በተደጋጋሚለማስፈራራት ሞከረ፡፡ በመጨረሻም ጥይቶቹን በሙሉ ተኩሶ ስለጨረሰ ሽጉጡጥይት አልባበመሆን የባዶ ሽጉጥ ድምጽ ሲያቃጭል ይሰማ ጀመር፡፡ ባለመሳሪያው እብሪተኛ ደንቆሮወደኤምባሲው ህንጻ ዘልቆ በመግባት አስተማማኝ ጥበቃ ባለበት ለእንግዶች ጊዚያዊ ማረፊያወደተዘጋጀውወደ ሰራተኞች አካባቢ በመሸሽ ሄደ፡፡ በመጨረሻም አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ ወደባንዲራ መስቀያ ቦታውበመሄድ በመሀከሉ ላይ የኮከብ ምልክት ያለበትን የወያኔን ባንዲራከተሰቀለበት በማውረድ በኢትዮጵያሰንደቅዓላማ በመተካት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ሲሰቅልታየ፡፡ በመጨረሻም ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ወደኤምባሲው ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት ወደጊዚያዊ ማረፊያ ቦታው በመሄድ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግመጮህ ጀመሩ፣”ነጻነት ነጻነት…“በማለት፡፡
ለተለያዩ ድርጅቶች የሚሰራው የምርመራ ጋዜጠኛ እና ዕውቁ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተሟጋችየሆነውአበበ ገላው ከሌላ ምንጭ ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣“በዩኤስ አቃቤሕግ በዋሺንግቶን ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ቢል ሚለር በገብረስላሴላይ በመግደል ሙከራእና ታጥቆም በመገኘቱ ምክንያት ለህግ ቢቀርብ እስከ 30 ዓመታትበእስራት ሊያስቀጣ የሚችል የክስመጥሪያ ወጥቶበታል“ብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካ መንግስት መምሪያቃል አቀፈባይ የሆኑት ጀን ፔንሳኪ የወያኔገዥ አካል የተኳሹን የገብረስላሴን ያለመከሰስ መብትለማንሳት እና ለህግ እንዲቀርብ ለማድረግ ፈቃደኛያለመሆኑን መግለጹን በማስመለከት እንዲህብለው ነበር፣ “ለኤምባሲው የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆኗል፣እናም በአሁኑ ጊዜ የወንጀልተጠርጣሪው ግለሰብ አገር ለቅቆ ወጥቷል፡፡“
አስቀያሚውን የጫካ ትዝታ በዋሺንግተን ዲ.ሲ መተግበር?
እስከ አሁን ድረስ በዋሺንግተን ዲ.ሲ የዲፕሎማሲ ታሪክ የወያኔ “ዲፕሎማሲ” በሰላማዊመንገድጥያቂያቸውን ባቀረቡ ዜጎች ላይ መሳሪያ አውጥቶ በመተኮስ ማስተናገድ የዴሞክራሲአባትበሆነችው አሜሪካ ውስጥ ካሉ በየትኛውም ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በታሪክያልተሞከረየመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ሰሎሞን ገብረስላሴ አነጣጥሮ ተኳሽ ነውን? ጫካውስጥበነበረበት ወቅት ከደርግ ጋር ሲያካሂደው የነበረው የዚያ ጦርነት አስቀያሚ ትዝታ ድንገትብልጭብሎበት ይሆን እንዴ? ሰሎሞን ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሟቸውንበሰላማዊመንገድ ለማሰማት በተሰባሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ በየትኛውም የዲፕሎማሲያዊ ተቋምላይተሞክሮ ያልታወቀውን ስልጣኔ የጎደለውን የደንቆሮዎች ድርጊት በመናፈቅ ተኩስ ከፍቶወገኖቻችንንለመጨረስ መሞከሩ በእውነት በጫካ በነበረበት ጊዜ ወያኔን ሲቃወሙ የነበሩትንወገኖቻችንን ሁሉሲጨርስ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ያንን እኩይ ምግባር የዓለም የዴሞክራሲተምሳሌት በሆነችው አሜሪካእምብርት ዋሺንገተን ዲ.ሲ. ላይ ልምዱን ለማስታወስ ያህልሲነሽጠው የክለሳ ስራ መስራቱ ይሆን እንዴ? ‘ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ’ እንዲሉ!
ገብረስላሴ የፈጸመው እኩይ ድርጊት በስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ተመራማሪዎች ‘አስቀያሚትዝታ’በመባል የሚታወቀውን ከአዕምሮ ጋር ተቆራኝቶ የሚኖረውን እና ሳይታሰብ እና በድንገትቅጽበታዊበሆነ መልኩ በአንድ ምክንያታዊም ሆነ ኢምክንያታዊ ክስተት በሚፈጸምበት ጊዜ ላይ ግንፍልብሎበመውጣት ወደ ድርጊት ከሚሸጋገር ስነልቦናዊ ድርጊት ጋር ይመሳሰላል፡፡ ከዚህ አንጻርገብረስላሴያልታጠቁ ሰላማዊ አመጸኞችን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ አካባቢ በተመለከተ ጊዜበአዕምሮስነልቦናው ውስጥ ተቀርጾ የተነበበው በከፍተኛ ወኔ እና ከባድ መሳሪዎችን ታጥቆበመምጣትየእርሱን የአማጺ ቡድን ወያኔን ለመውጋት የመጣ ሰራዊት መስሎ ነው የታየው፡፡በግልብአዕምሮው ውስጥ ተጽፎ የሚታየው ይኸው ነው፡፡ ሌላ በጎ ነገር በቡድንም ሆን በግልያልለመዱትንእና ያላዩትን ነገር ለሰሎሞን ገብረስላሴ ከየትኛው ተሞክሮው ተቀምሮ በአዕምሮውጓዳ ውስጥ አድሮሊከሰት ይችላል ተብሎ ይታሰባል? ጀግናው ገብረስላሴ ያንን የመሰለ ድርጊትበሚጽምበት በዚያን ጊዜየሀገሮች መስተጋብር ማስፈጸሚያ የሆነውን ኤምባሲን የሚጠብቅ መስሎአልታየውም፡፡ ይልቁንምበአዕምሮው ላይ ተቀርጾ የኖረው እና አሁንም ያለው የወያኔን የመሬትውስጥ ምሽግ ጫካ በነበረበት ጊዜከጠላት ለመከላከል የሚያደርገውን ቅጽበታዊ እርምጃመውሰድን ነው የሚያስታውሰው፡፡ ወዲ ገብረስላሴበድል አድራጊነት በሚመስል መልኩ ሽጉጡንእያወዛወዘ በዲፕሎማት ወግ ጥቁር ሱፉን ገድግዶ ለብሶበሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩስበታላቋ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ በከፍተኛደረጃ የውጭ አገርየዲፕሎማት ሰው መቀመጫ ወንበር ላይ መሆኑን ፍጹም በሆነ መልኩ እረስቶታል፡፡አይ ጫካመኖር! የጫካ አስተሳሰብ እኮ በጫካው ውስጥ ያሸነፈ ይኑር የሚለውን የአራዊትአስተሳሰብንየተላበሰ ሆኖ ይገኛል፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በጫካ ህይወቱ ጊዜ ጠላትን ለመከላከል እናአለቆቹንጠላት ከሚያደርሰው ጥቃት ለመጠበቅ ከአዛዦቹ ይሰጥ የነበረውን ትዕዛዝ ተቀብሎይተገብርወደነበረበት የወያኔ አማጺ ቡድን እግረኛ ተዋጊነት ስራው ተመለሰ እንጅ ዘመናዊ አስተሳሰብእናየትምህርት ክህሎት ከሚጠይቀው ዲፕሎማትነት ጋር ትውውቅም ሆነ ዝምድና የሌለው መሆኑንበሚገባተግብሮ እና አስመስክሮ ወደ አገሩ ሳይሆን ወደ መፈንጫው ተመልሷል፡፡
ሰሎሞን ገብረስላሴ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ተልዕኮ እና የውጭ ዲፕሎማት የኗሪነት ፖሊሲእና ህግጥበቃ ምን እንደሆነ እና ምን እንደሚመስል የማያውቀው መሆኑ በግልጽ ይነበባል፡፡አሜሪካ በውጭየሚገኙ ኤምባሲዎቿን ከማንኛውም የጠላት ጥቃት ለመከላከል ፈጣን የሆኑ የባህርኃይል ሰራዊቷንበማሰማራት ጥበቃ እንደምታደርገው ሳይሆን በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካየሚገኙትን የዲፕሎማሲፋሲሊቲዎችን ጥበቃ በሚመለከት ግን ኃላፊነቱ የወደቀው በአሜሪካየመንግስት መምሪያ፣ በደህንነትአገልግሎቱ እና በአካባቢ የፖሊስ ወኪሎች የጋራ ጥረት ላይ ነው፡፡ከዚህ አንጻር የዋሺንግቶን ከተማ ፖሊስለዲፕሎማሲያዊ ፋሲሊቲዎች ደህንነት ሲባል የተለያዩመንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ጥበቃበማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ለጥበቃው በተለይምዘብ ለተወሰኑ ፋሲሊቲዎች ወይም ደግሞለደህንነት ጉዳይ ሲባል እየተዘዋወሩ የሚጠብቁ ዘቦችንበመመደብ እና የፖሊስ ምልክት ያለባቸውንተሽከርካሪዎች በማሰማራት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡እንደዚሁም ደግሞ መረጃ የማይሰጠው የደህንነትአገልግሎቱ መስሪያ ቤት በዋሺንግትን ዲ.ሲአካባቢ ላሉ የዲፕሎማሲያዊ ተቋማት ተገቢ የሆነ ጥበቃይሰጣል፡፡ ይህ የደህንነት አገልግሎትመስሪያ ቤት በዲፕሎማቱ ማህበረሰብ እና በዲፕሎማቶችፋሲሊቲዎች ላይ ሊፈጸም የታሰበአስተማማኝ አደጋ መኖሩን ሲያረጋግጥ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
ያለመከሰስ መብት የተጎናጸፉት ዲፕሎማቶች በማንኛውም መልኩ የጦር መሳሪያን በመጠቀምሌሎችንሰላማዊ በሆነ መልክ ተቃውሟቸውን በሚገልጹ ያልታጠቁ ወገኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር፣ዲፕሎማቶችበእራሳቸው ሀገር በሌሎች ወገኖች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲባል የጦር መሳሪያ ደብቆመገኘት፣ ወይም ደግሞበድብቅ መሳሪዎችን በማከማቸት በዩናይትድ ስቴትስ ወይም በዩናይትድስቴትስ በሚኖሩ ሌሎች ተመሳሳይተግባራትን በሚያካሂዱ ዲፕሎማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘርንየሚፈቅድ ህግ፣ ፖሊሲ ወይም ደግሞ ልምድበፍጹም የለም፡፡ ዲፕሎማቶች አለመግባባቶችን እናውዝግቦችን በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ ለመፍታትየቃላት “ጥይቶችን” ይጠቀማሉ እንጅእንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ እየተገበረው እንደነበረው ቁጥር 38የካሊበር ሽጉጦችንአይጠቀሙም፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ አካባቢ መሳሪያ በመተኮስያልታጠቁሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ለመግደል በተደጋጋሚ ባደረገው የግድያ ሙከራ በዋሺንግተንዲ.ሲየዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ህሊና ቢስ እና የሞራል ስብዕናን የጣሰ የወንጀል ድርጊት ሆኖሲታወስይኖራል፡፡ ይህ አስነዋሪ የወንጀል ድርጊት ወደፊት ለሚመጡት አስርት ዓመታትየወሮበላየዲፕሎማሲ እኩይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የሚያግዙ ለዓለም አቀፍ የህግ እናየዲፕሎማሲተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የማስተማሪያ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት ታላቅ እገዛንያደርጋል፡፡
ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱንልታላቀቀውአትችልም፣
የዲፕሎማት ሰዎች ተቀራርቦ በመነጋገር፣ ስምምነት በማድረግ እና በመቻቻል (አብዛኛውን ጊዜበማታለል)ባለመግባባት የሚከሰቱ ውዝግቦችን ለመፍታት ይፈልጋሉ፡፡ የወሮበላ ዲፕሎማቶችሁሉንም ችግሮች እናከዚእነዚህ ክሶች ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ውዝግቦችን በመግደል፣በመደብደብ ወደ ዘብጥያ በመወርወርእና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን እና ጠላቶቻቸውንበማሰቃየት ይፈታሉ፡፡ ዲፕሎማሲ “በመንግስታትተወካዮች መካከል የሚደረጉ ስምምቶችንለማምጣት የሚያገለግል ትምህርት እና የተግባር ተሞክሮ ነው፡፡“ወሮበላ ዲፕሎማት ሰሎሞንገብረስላሴ የዲፕሎማት ትምህርቱን ያገኘው እና የቀሰመው ዙ ኢንላይከሚባለው ተረታዊየዲፕለማት ትምህርት ቤት ነው፡፡ “ሁሉም ዲፕሎማሲ በማንኛውም መንገድ ቢሆንየጦርነትቀጣይነት ነው፡፡“ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ በዲፕሎማቲክ ያለመከሰስ መብትን መደበቂያምሽግበማድረግ ለአስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የዘለቀውን አከፊውን የወያኔን የጫካ ጦርነትወደዩናይትድ ስቴትስ ለማምጣት ፈለገ፡፡
የሰለጠኑ ወሮበላ ዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ የሚመረጡት እና የሚላኩት እጅግአናሳበሆነ አጋጣሚ ነው፡፡ አብዛኞቹ አገሮች ወደ ሌላ አገር የሚያሰማሯቸውን ዲፕሎማቶችየሚመርጧቸውበመንግስት መስሪ ቤቶች ከሚመድቧቸው በከፍተኛ ደረጃ ካሉ ሰዎች መካከልነው፡፡ አብዛኞቹየሚመረጡት ዲፕሎማቶችም በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት የቀሰሙ፣ ሰፊ ልምድያካበቱ እና ጠለቅ ያለየፖለቲካ እውቀት ያላቸውን ዜጎች ነው፡፡ ብዙ አገሮችም የዲፕሎማትሰዎቻቸውን ሾመው ወደመደቧቸውአገሮች ከመላካቸው በፊት ሙያዊ የሆነ እና ከሙያው ጋርአግባብነት ያለው ስልጠና በማዘጋጀትእንዲሰለጥኑ ያደርጋሉ፡፡
እጅግ በጣም ውሱን ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሀገር ቢሆን እንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴያለውን ተራማይም ደንቆሮ መርጦ እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ባለች አገር ላይ ዲፕሎማት ብሎአይልክም፡፡ በዲፕሎማቲክመስኩ በጣም ቀልጣፎች ያልሆኑ አገሮች እንኳ ለዲፕሎማሲ ተልዕኮየመለመሏቸውን ሰዎች ወደየሀገሮችከመላካቸው በፊት ስለዲፕሎማሲ ስራ ሰልጠና ይሰጧቸዋል፡፡በዚህም መሰረት በየጊዜው ከሚለዋወጠውዓለም አቀፍ ሁኔታ ጋር አብረው ለመሄድ እንዲችሉእገዛ ያደርግላቸዋል፡፡ ያ የሚሰጠው ስልጠናምበትክክለኛው መንገድ በዲፕሎማሲ ስራ እና ተግባርላይ ትኩረት ያደረገ እንጅ ስለጦርነት ስልት እውቀትወይም ዜጎችን በአገራቸው እንዴት መግደልእንደሚችሉ ለማሰልጠን አይደለም፡፡ ለምሳሌም ያህልአዘረባጃን የእራሷ የሆነ “የዲፕሎማሲአካዳሚ” አላት፡፡ ቡልጋሪያም የግሏ የሆነ የዲፕሎማሲ ማሰልጠኛተቋም አላት፡፡ እንደዚሁምደግሞ ጋና ኮፊ አናን የሰላም ጥበቃ ስልጠና ማዕከል/Kofi Annan Peace Keeping Training Center የሚባል የዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ ተቋም አላት፡፡ በሌላበኩልም የግልየዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ ዩኒቨርስቲዎች ማለትም እንደ Tuft University’s Fletcher School of Law and Diplomacy እና ሌሎች ተቋማትም ከዓለምአቀፋዊድርጅቶች ጋር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶች አሉ፡፡
ሊታምን በማይችል መልኩ የሚያስደንቀው እና የሚገርመው ነገር በአጠቃላይ የወያኔ የውጭጉዳይሚኒስቴር አመራር በዲፕሎማሲ የሙያ ዘርፎች ላይ የሰለጠነ ወይም ደግሞ በዚህ ሙያ ላይበቂልምድ ያለው ዲፕሎማት የለውም፡፡ ለምሳሌ ያህል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበላይ ቁንጮ የሆነውሰውየዲፕሎማሲ ሙያ ስልጠናም ሆነ ልምድ የላቸውም፡፡ ምንም፣ ባዶ! የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርቴዎድሮስአድኃኖም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከአስመራ ዩኒቨርስቲ በስነሕይወት/Biology የትምህርትመስክ ነው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በማስተር ኦፍሳይንስ በImmunology of Infectious Diሰዓሰስ በሚል ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ ያገኙሲሆን የፒኤች ዲ ዲግሪያቸውን ደግሞበህብረተሰብ ጤና/Community Healthየትምህርት መስክ በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘውከኖቲንግሀም ዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል፡፡ ለጤናሚኒስትርነት ተሾመው ነበር፡፡ በአንድ ጀንበር ምሽት ከመለስዜናዊ ህልፈት በኋላ እራሳቸውንየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገኙት፡፡ (እርግጠኛ ነኝ በአንድ ጀንበርምሽት ደግሞ እራሳቸውንጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገኙታል)፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነውመሾማቸው ለጠቅላይሚኒስትርነት መወጣጫነት የመጀመሪያ ደረጃ እና ለሚጠብቃቸው የጠቅላይሚኒስትርነትሹመታቸው ለይስሙላም ቢሆን ለማሟሻነት ቢጠቅም በሚል እኩይ ስሌት የተቀነባበረ ነው፡፡እርግጥ ነው አምባገነንነት እና ወሮበላነት በተንሰራፋባት የመጨረሻ ደኃ ሀገር ለዲፕሎማትነትመስፈርቱዘር እና ታማኝነት እንጅ ትምህርት እና ልምድ ምን ፋይዳ ይኖረዋል! (ሟቹ መለስዜናዊ በአንድ ወቅትስለሚኒስትሮቹ አሿሿም የትምህርት ብቃት ማነስ ጉዳይ በቴሌቪዥን ጥያቄበቀረበላቸው ጊዜ “ታማኝነትእንጅ ማይም ይሁኑ” በማለት የሰጡትን አስገራሚ እና ፈጣጣየስላቅ መልስ ልብ ይሏል፡፡)
ጉድ እኮ ነው ጎበዝ እንዴት አንድ ምንም ዓይነት የዲፕሎማትነት ልምድ እና በመስኩም አስፈላጊየሆነውትምህርት ሳይኖረው ወይም ደግሞ ምንም መነሻ መሰረት ሳይኖረው እንዲሁምበአምበሳደርነት (ስለዓለምአቀፍ ህግ እና ዲፕሎማሲ ፍጹም ባይተዋር የሆነ [ከኢትዮጵያ እሳትወደ ሳውዲ አረቢያ እረመጥ] በሚልርዕስ ያቀረብኩትን ትችት ይመልከቱ)   እንኳ ሳይሰራበድንገት እና ቅጽበታዊ በሆነ ሁኔታ የውጭ ጉዳይሚኒስትርነትን ያህል ከባድ ኃላፊነት የሚጠይቅየሚኒስትርነት ቦታን ይይዛል?
ለዚህ መልሱ ግልጽ እና አጭር ነው፡፡ አድኃኖም በዘር ሀረጋቸው ብቻ እና ብቻ ነው የወያኔየከፍተኛዲፕሎማት ስልጣን የተሰጣቸው፡፡ በእርግጥ ይኸ ጉዳይ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ በአሁኑጊዜ በህይወትየሌለው መለስ ዜናዊ ምን ዓይነት የትምህርት ማስረጃ እና ብቃት አቅርቦ ነውጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው?መለስ በርቀት የትምህርት ፕሮግራም በተልዕኮ ከእንግሊዝ ሀገርበቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የመጀመሪያዲግሪውን አገኘ፡፡ ለሁለተኛ ዲግሪውም ከኢራስመስዩኒቨርስቲ የዓለም ብቸኛው ታላቅ አዋቂ ነኝ አያለሲፎከርበት የነበረውን የልማት ምጣኔሀብት/Development Economics የመመረቂያ ጽሁፉንማጠናቀቅ ያልቻለ ሰው ነበር፡፡
ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ለወሮበላ ዲፕሎማት ልዩ ስልጠና እየተሰጠ በብቃት ላይሳይሆንበዘር እና በታማኝነት ላይ ትኩረት በማድረግ የሚኸድበት ስልት እውነተኛውንየዲፕሎማሲ ስራ አካሄድእንዲበላሽ አድርጎታል፡፡ ለአፍሪካውያን/ት የወሮበላ ዲፕሎማቶችማሰልኛ ተቋም በቅርብ ጊዜ ውስጥከአፍሪከ ህብረት የለማኞች አዳራሽ፣ ለአፍሪካ አምባገነኖች እናወሮበሎች መሰብሰቢያ ከተሰራው አዳራሽፊት ለፊት በቅርብ ርቀት ላይ ይገነባል የሚል ግምትአለኝ፡፡ የሚያስገርም ጉዳይ ይሆናል፡፡
ከእውነታዎች ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ አለብን፡፡ አሳማን የከንፈር ቀለም መቀባት ይቻላልቆንጆለማስመሰል፣ ሆኖም ግን ከዕለቱ መጨረሻ ያው ዓሳማ ዓሳማ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እንደሰለሞንገብረስላሴ፣ ግርማ ብሩ ወይም ቴዎድሮሰ አድኃኖም እና ሌሎች በርካታዎቹ ብሪፍ ኬዝ/ቦርሳ እናየይሰሙላ ክብር መስጠት ይቻላል፡፡ በቀኑ መጨረሻም እራሳቸው እራሳቸውን ሆነውያገኙታል፡፡ ወሮበላዘራፊዎች!
መንግስታዊ አገዛዝ ከወሮበላ (የጫካ አገዛዝ ጋር) ሲነጻጸር፣
የወያኔን አገዛዝ የወሮበላ አገዛዝ ነው በማለት በምገልጽበት ጊዜ ከምንም በመነሳት በጥላቻ  ወይምደግሞለቡድኑ ክብር ካለመስጠት አይደለም፡፡ አንዲሁም መለስ ዜናዊን “የአፍሪካ የለማኞችአለቃ” ነው በማለትስገልጽ እራሱ በሚጠቀምባቸው ቃላት ላይ መሰረት አድርጌ ነው፡፡ የእራሴንቃላት እና ሀረጎች እርሱከሚሰራቸው እውነታዎች በመነሳት ነው የምርጣቸው፡፡
የወያኔ አለቆች በምንም ዓይነት መልኩ ከወሮበላነት (የጫካ) አገዛዝ ወደ መንግስታዊ አስተዳደርበፍጹምሽግግር አያደርጉም፡፡ በጫካው ዘመናቸው ወጣት በነበሩበት ጊዜ የነበራቸው ልምድየምሁርነትአስተሳሰባቸውን፣ የሞራል ስብዕናቸውን እና የማህበራዊ ልማት እይታቸውን በጫካውየቅኝት አስተሳሰብብቻ እንዲወሰን አድርጎታል፣ ሸፍኖት ቀርቷል፡፡ ከዚያ አልፎ አንዳንዶቹ ዘመናዊእና ላቅ ያለ የአካዳሚትምህርት የማግኘት ዕድል ያገኙ አባላቱ እንኳ ስልጣን ከያዙ በኋላበተመሳሳይ መልኩ ድሮ ወደነበሩበትየአስተሳሰብ አድማስ በመመለስ የአስተሳሰብ ግልብነት እናየሞራል ዝቅጠትን እና ባዶነትን አንጸባርቀዋል፡፡
የወጣትነት የመጀመሪያዎቹን ዓመታት በጫካ ውስጥ አማጺ ሆኖ ከማሳለፍ አንጻር ለመቀየርየማያስችል እናቋሚ የሆነ የተቸከለ አስተሳሰብን ይፈጥራል፡፡ በአካዳሚክ ዓለሙ ያሉም ሰዎችይህን ሲመለከቱቱ የአማጺያንን የጫካ ህይወት መኖር ያልረሱት እና በአዕምሯቸው ላይ የማይለቅችካል ስለሆነ ሆብስ“የመሆን ሁኔታ” እንዳለው በአእምሯቸው ላይ በጫካ አስተሳሰብ የተቃኘአንዳች የሆነ ነገር አንደሚፈጠርነው።  የእንግሊዝ ፈላስፋ የነበሩት ቶማስ ሆብስ የሰለጠነመንግስት በሌለበት ጊዜ “እያንዳንዱ ሰውከሌላው ሰው ጋር በጦርነት ይኖራል” በማለት የሙግትጭብጣቸውን አቅርበው ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳህይወት በመሆን የተፈጥሮ ህግ ላይ “ብቸኛ፣ ደኃ፣በጭካኔ የተሞላ፣ አውሬአዊ እና ኋላቀርነት አስተሳሰብንየተላበሰ ይሆናል“፡፡ ሆኖም ግን ሊነሳየሚችለው ጥያቄ ሆብስ የመሆን ሁኔታ እዳሉት ለአስርት እና ግማሽዓመታት በአማጺነት በጫካሲኖሩ የነበሩት የወያኔ አማጺ አመራሮች ከጫካ ህይወታቸው ወጥተውስልጣንን በኃይል ነጥቀውበስልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡ እና የሰለጠነ መንግስታዊ መዋቅር መሪዎችከሆኑ በኋላበእርግጠኝነት ሊሆን የሚችለው ምንድን ነው? በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ሲመሩበትየነበረውንየመሆን ሁኔታ እርግፍ አድርገው ትተው የወሮበላነትን መንግስታዊ አገዛዝ በሰለጠነመንግስታዊአስተዳደር እንዲቀየር በማድረግ የህግ የበላይነትን በማስፈን እውነተኛ ሽግግርን ሊያመጡእናህዝቡን በሚፈልገው መልክ ማስተዳደር ይችላሉን?
አጋጣሚ ሆኖ ከእነርሱ አባባል ታምራዊ ሀረጎች በመዋስ “እድገት እና ትራንስፎርሜሽን”ለማምጣትየምሁራዊ እና የሞራል ብቃቱ ሳይኖራቸው ቀርቷል፡፡ ለወያኔ አለቆች በሰለጠነማህበረሰብ ውስጥ ገብቶአብሮ መኖር አሁን ብዙ ገንዘብ እና ሀብት ከመዝረፍ በስተቀር ለእነርሱህይወት በጫካ ውስጥ ይኖሩበትእንደነበረው ዓይነት ቀጣይነት ያለው ነው፣ ምንም ዓይነት ልዩነትየለውም፡፡ በእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስምንም ዓይነት የተቀየረ ነገር የለም፡፡ ለ23 ዓመታትበስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጠው ከቆዩ በኋላ ምንምዓይነት የተማሩት ቁም ነገር የለም፡፡አሁንም ቢሆን በጫካ በነበሩበት ጊዜ ሲያራምዱት የነበረውንሚስጥራዊ የፖለቲካ ፍልስፍናበህዝቡ ላይ በመጫን ለመቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜየተጠያቂነት እናየግልጽነት ባህሪን አያራምዱም ነበር፣ አሁንም ቢሆን አንድን ታላቅ አገር በቁጥጥራቸውስርአድርገው ስርዓት ባለው መልኩ ተጠያቂነት እና ግልጽነትን በተላበሰ ሁኔታ መምራት ሲችሉይህንንመተግበር ተስኗቸዋል፡፡ በጫካ ውስጥ ሆነው ከደርግ ወታደራዊ አምባገነን ጋር ትግልሲያደርጉበነበሩበት ወቅት ውሳኔ ሰጭነት በጥቂት የወያኔው መሪዎች ብቻ እና ብቻ ነበር፡፡ በዚያንወቅትእነዚህ ጥቂት አመራሮች ይመሩት በነበረው ሰራዊት እና በአጠቃላይ በቁጥጥራቸው ስርአድርገውትበነበረው ህዝብ ላይ ጥሬ የሆነ አስተሳሰብን፣ ጭካኔ የተሞላበት ኃይልን ይጠቀሙ ነበር፡፡ሰላማዊአማጺያንን እና የሰላ ትችት ያቀርቡባቸው በነበሩት ወገኖች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃመውሰድጀመሩ፡፡ ከእነርሱ ሀሳብ ጋር ስምምነት የማያደርጉ ዜጎችን ማግለል፣ እንደ ሰላይነትበመቁጠር መግደል እናማጥፋት ጀመሩ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መንግስታዊ ስልጣንን ከተቆናጠጡበኋላም የተቃዋሚ የፖለቲካፓርቲ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና ሌሎችንም ለስልጣናቸው አስጊናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውንወገኖች ማዋከብ፣ ማሰር፣ መግደል እና ከሀገር እንዲወጡማድረግን ስራየ ብለው መተግበር ጀመሩ፡፡ከእራሳቸው መካከል በሀሳብ በመለያየታቸውየተገነጠሉትን ተስፈንጣሪ ቡድኖች  ርህራሄ በሌለው መልኩአስወገዷቸው፣ አዋረዷቸው!
በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ስልጣንን፣ ገንዘብን በመዝረፍ እራስን እንደማበልጸጊያ፣ የፖለቲካየበላይነትእና ማስፈራራትን እንደ መሳሪያ በመቁጠር ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔአገዛዝ በሙስና የበከተእና የሙስናው በሽታ በኢትዮጵያ አካል ላይ እንደ ነቀርሳ እየተሰራጨመሆኑን ሙስናን በኢትዮጵያመመርመር/Diagnosing Corruption in Ethiopia በሚል ርዕስ  የዓለም ባንክ አዘጋጅቶባወጣው በባለ550 ገጽ ዘገባው ላይ በግልጽአስፍሮታል፡፡ ወያኔ በጫካ በነበረበት ጊዜ አመራር ላይመሆን ማለት የእራስን ስብዕና መትከልየነበረ ሲሆን አሁንም ቢሆን በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው መለስዜናዊ በእርሱ ደቀመዝሙሮችእንደ ትንሹ አምላክ ያህል ይመለክ ነበር፡፡ የእነርሱ ከጫካ አገዛዝ ወደመንግስታዊ አስተዳደርያደረጉት ሽግግር የአንድ ሰው፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነት የነበረውን የደርግ አገዛዝበማስወገድበአንድ ሰው፣ በአንድ ፓርቲ የወያኔ አገዛዝ ተኩት፡፡ የወያኔ አመራሮች በደርግ አገዛዝ ላይያደረጉትለውጥ አለ ከተባለ “ለወያኔ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለኢትዮጵያ ህዝብም ጥሩ ነው”የማለታቸውአምባገናናዊ አመለካከታቸው ብቻ ነው!
ከወሮበላነት/ከጫካ አገዛዝ ወደሰለጠነ መንግስታዊ አስተዳደር የሚደረግ እውነተኛ ሽግግርየፍልስፍና እናየፖሊሲ ሁለቱንም ነገሮች ስርነቀል በሆነ መልኩ መቀየርን ይጠይቃል፡፡ ይኸ ግንባዶ ተስፋ ሆኖ ቀርቷል፡፡በተደጋጋሚ ጊዜ እንደምለው የወያኔ አመራሮች ትክክለኛ መንግስታዊመዋቅርን ይመሰርታሉ ወይም ደግሞትክክለኛ መንግስታዊ ስርዓትን ያራምዳሉ ማለት ሰይጣንከመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሰ ያስተምራልእንደማለት ነው፡፡
ዴሞክራሲያዊ የመንግስት አስተዳደር መሰረታዊ የሆኑትን መርሆዎች ማለትም የህግ የበላይነት፣የስልጣንክፍፍልን፣ የቁጥጥር እና የኃይል ሚዛንን እና ህገመንግስታዊ የአስተዳደር ሂደትንበመተግበር በእውነታ ላይየተመሰረተ ትችትን በትክክል ለተከናወኑ ስራዎች ደግሞ አድናቆትመስጠት እና መግባባትን ይጠይቃል፡፡የወያኔ ወሮበላ አመራሮች ለእንደዚህ ዓይነቶቹ ጉዳዮችእጅግ በጣም አነስተኛ የሆኑ ልምዶች ወይም ደግሞየተግባር ተሞክሮ ጭራሹንም የላቸውም፡፡በዚህም መሰረት ማንም ቢሆን እነዚህ የወሮበላ ስብስብአመራሮች በፖለቲካ ህይወታቸው ውስጥያልነበራቸውን እና በተሞክሮም የማያውቁትን ተጠያቂነትን እናግልጸኝነትን ሊያሰፍን የሚያስችልየፖለቲካ ስርዓት ለህዝቡ ማስፈን እና መተግበር ይችላሉ ብሎ መጠበቅየዋህነት ነው፡፡ በጫካውስጥ በነበሩባቸው ጊዚያት ምንም ዓይነት ነጻ ምርጫ አካሂደው አያውቁም፣በመሆኑም እ.ኤ.አበ2005 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በዝረራ በተሸነፉበት ወቅት ተአምር የሆነያህልተገርመው ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ታላቅ ትምህርትን ቀስመዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገውአገርአቀፍ ምርጫ 99.6 በመቶ የድምጽ ውጤት በማምጣት (በመዝረፍ አላልኩም) ድልተቀዳጅተናል፡፡በጫካ በነበሩባቸው ጊዚያት የሚናገሯቸው ቃላት እራሳቸው ህግ ነበሩ፣ ስለ የህግየበላይነት ምንም ዓይነትሀሳብ አልነበራቸውም፡፡ አንድ ጊዜ ስልጣንን ከጨበጡ በኋላ የእነርሱቃል እራሱ ህግ ሆኖ ቀጥሏል፡፡በእራሳቸው ስልጣን ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ይቀጣሉ፡፡ በጫካ ውስጥበነበሩበት ጊዜ እነርሱ እራሳቸው ዳኛ፣ችሎት እና አስፈጸሚ ነበሩ፡፡ በስልጣን ላይ ባሉበት ጊዜበጫካ ላይ ከነበሩበት ጊዜ የተለየ ነገር የላቸውም፣ልዩነት አለ ከተባለም በጫካው ጊዜ ይፈጽሙትያልነበረ አሁን ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር መዋቅርንከተቆጣጠሩ በኋላ ለይስሙላ የዝንጀሮፍርድ ቤቶችን በማቋቋም እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ውሳኔውእንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ በጫካውስጥ በፍርሃት እና በበቀል ነው የኖሩት፣ እናም የሲቪል ነጻነቶች እናየእነዚህ ነጻነቶች አተገባበርለእነርሱ ባዕድ ናቸው፣ ፈጽሞ አይተዋወቁምና፡፡ በአሁኑ ጊዜም ህዝቡበድንገተኛ መሬትአንቀጥቅጥ አመጽ ያስወግደናል በሚል ፍርሀት ውሰጥ ተቀርቅረው ሌት ቀን ሲባንኑይውላሉ፡፡እናም የሲቪል ነጻነቶች እና መብቶች ቅንጦት የሆኑ ነገሮች ሲሆኑ እነዚህ ቅንጦት የሆኑነገሮችምለእኛ ሳለይሆን ለምዕራባውያን ሰዎች ብቻ የተተው እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ሆኖምግንእነርሱ፣ የእነርሱ ደቀመዝሙሮች እና ደጋፊዎቻቸው ለሚሰሯቸው ወንጀሎች እና የሲቪልወንጀሎችሳይቀር ያለመከሰስ መብትን በመጠቀም የተለያዩ ወንጀሎችን እየፈጸሙ እራሳቸውን በማስደሰትላይይገኛሉ፡፡ በአጭሩ ከዚህ የእኩይ አስተሳሰብ ባለቤት ከሆነው የወሮበላ ቡድንዴሞክራሲያዊአስተዳደርን የተላበሰ ስርዓት በኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን የሚያስችለል መንግስታዊ መዋቅርመጠበቅከባዶ ተስፋ የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡
ሰላማዊ ሰልፈኞችን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዴት?
በአንድ ታትሞ በወጣ ዘገባ እንደቀረበው የወያኔ አገዛዝ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 29/2014በዋሽንግተንዲ.ሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ወገኖቻችን ላይክስ ለመመስረትእንደሚንቀሳቀስ አሳውቋል፡፡ ዲና ሙፍቲ የተባሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይሚኒስቴር ቃል አቀባይይህንን ጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፣ “የዩናይትድ ስቴትስመንግስት በኤምባሲው ቅጥር ግቢገብተው ጸረ መንግስት የሆኑ መፈክሮችን እያሰሙ የኢትዮጵያንባንዲራ በማውረድ ሁከት በፈጠሩት ሰዎችላይ የኤምባሲውን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እናበአጥፊዎች ላይ ክስ መመስረት እንዳለበት ይጠበቃል፡፡“በሌላ በኩል የወጣ ዘገባም እንደጠቆመውሰላማዊ ሰልፈኞች በአዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትስ ስቴትስኤምባሲ በመሄድ “ሰላማዊሰልፈኞች ለህግ መቅረብ አለባቸው” የሚል ጥያቄ ያቀረቡ መሆናቸውንአሳውቋል፡፡ “ በቪዲዮክሊፑ ላይ እንደሚታየው ሰላማዊ ሰልፈኞች የኢትዮጵያን ብሄር ብሀረሶቦችየሚወክለውን ባንዲራበማውረድ የጥንቱን እና የነጻነታችን አርማ ሆኖ ሲያገለግል የቆየውን አረንጓዴ፣ ቀይእና ብጫቀለም ያለበትን የህዝቦች ነባር ባንዲራ በክብር ወደነበረበት ቦታው መለሱት፣ አከበሩትእንጂአላዋረዱትም፡፡  ሰላማዊ ሰልፉ በወያኔ አገዛዝ የተቀነባበረ የመድረክ ላይ ተውኔት ነው፡፡
ሙፍቲ፣ ቴዎድስ አድሀኖም እና ሌሎች የወያኔ ደናቁርት ምን መመኘት እንዳለባቸው ጥንቃቄማድረግይጠበቅባቸዋል፡፡
መጀመሪያ፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ጥፋተኛ ለማድረግ በሚደረገው የውንጀላ ብያኔ ላይ ግልጽ መሆንአለበት፡፡በአሜሪካ አገር የፌዴራል ወይም የኮሎምቢያ ወረዳ ግዛት ወንጀል ስርዓት ኮድ ላይ“ሻጥር ለመስራት”የሚል የወንጀል ጥቅስ አይታወቅም፡፡ ምናባዊ የሆነ የወንጀል ክስ በመፈብረክክስ እንዲመሰረት ቢያስቡእና ህዝቡን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉ የእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስበምን ያህል ጥልቀት እንደወረደ እናስለአሜሪካ ህግ ያላቸውን ድንቁርና የሚያመላክት ነው፡፡(በእንደዚህ ዓይነት ፍጹም ድንቁርናየተጠናወታቸው ፍጡሮች “ኢትዮጵያ የምትመራ” መሆኗንስመለከት በጣም ተሸማቀቅሁ፣ አዘንሁም!)
ሁለተኛ፡ የወያኔ ደናቁርት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አገር ማንኛውንም ዓይነት ባንዲራ የኮከብእናነጠብጣብ ምልክት ያለባትን የአሜሪካን ባንዲራም ቢሆን ማውረድ ወይም ማዋረድ ወንጀልአለመሆኑንሊያውቁ ይገባል፡፡ እ.ኤ.አ በ1989 በቴክሳስ ግዛት ጆንሰን የዩኤስ አሜሪካንንባንዲራ እ.ኤ.አ በ1984የሬፐብሊካን ብሄራዊ ጉበኤ በዳህላስ፣ በቴክሳስ) ባቃጠለበት ወቅትጀስቲስ ዊሊያም ብሪናን በአጠቃላይሀሳብ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍረው ነበር፣ “በሀሳብመለያየትን የማስተናገድ መብት ማረጋገጥየአሜሪካ የመጀመሪያው የህግ ነጻነት ማሻሻያችንየመሰረት ድንጋይ ነው፣ መንግስት በዜጎቹ መካከልአንድነትን የሚያጠፋ ነገር በመፈብረክ የዘፈቀደትዕዛዝ በመስጠት ተግባራዊ ማድረግ አይችልም፡፡“ይላል፡፡ ስለሆነም ያ አንድ ዓይነት ባህሪ እናመርህ ያለው መንግስት የአንድነት መገለጫ የሆነውን ምልክትበመጣስ ከዚያ መርህ ጋር የሚጣረስትዕዛዝን ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡ በቀላል አነጋገር እንኳንስ ይህንንበሸፍጥ የተዘጋጀ የብሄርብሄረሰቦች የሸፍጥ ባንዲራ ከተሰቀለበት ማዕዘን ማውረድ ይቅርና ጥንታዊውን እናየተከበረውንያሜሪካ ባንዲራም በእሳት ማቃጠል ህገመንግስታዊ መብት ነው፡፡
ሦሰተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት በጋዜጦች እና በድረ ገጾች የሚለቀቅ የዲፕሎማሲስራንእንደማይሰራ የወያኔ አገዛዝ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ እነዚህ ደናቁርት የዩናይትድስቴትስ መንግስትየሚፈልጉትን ነገር እንዲያደርግላቸው ከተፈለገ በመጀመሪያ ደረጃ የፕሮቶኮልስነስርዓትን ማክበርይጠበቅባቸዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ከውጭ መንግስታትየዲፕሎማቶች የተቃውሞጥያቄ ሲቀርብለት የውጭ መንግስታቱ የሚፈልጉትን ለማግኘት ሲፈልጉእነዚህ ቅሬታ ለማቅረብ የሚፈልጉመንግስታት መከተል ያለባቸውን ህጎች እና የአካሄድስነስርዓቶች በመከተል እንዴት ምላሽ መስጠትእንደሚችል በጣም ዝርዝር በሆነ መልኩአስቀምጧል፡፡ የወያኔ ደናቁርት በቀጣይነት የሚደርስባቸውንውርደት እና መሸማቀቅ ለማስቀረትበማሰብ ለእነርሱ ወገናዊነት እገዛን ለማድረግ የዩኤስ አሜሪካንንየመንግስት መምሪያ የውጭ ጉዳይሰነድ ቮሊዩም 5 የእጅ መጽሐፍ ቁጥር 1ን እንዲመለከቱ እጋብዛለሁ፡፡(በነገራችን ላይስለዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብት መነሳት ጉዳይን በማስመልከት ጥያቄ አቅርባችሁልኝለነበራችሁአንባቢዎቸ በግንባር በመገኘት ምላሽ ባለመስጠቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን ለዚህስራይጠቅማችኋል በሚል እሳቤ “Diplomatic and Consular Immunity: Guidance for Law Enforcement and Judicial Authorities“በሚል ርዕስየተዘጋጀውን በመረጃ የበለጸገ ሰነድ እንድታነቡት እጋብዛለሁ፡፡
አራተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤቶች እንደ ወያኔው የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶችሳይሆኑተከላካዮች የተሟላ ህገመንግስታዊ መብት ያላቸው እና አስገድዶ ቃል ያለመቀበልን፣ያለመደብደብእና በሰውነት ላይ የሚፈጸሙ የጥቃት ማስረጃዎችን ጭምር በማካተት አዘጋጅቶ ያስቀመጠመሆኑንየወያኔ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ የወያኔ ደናቁርት እነዚህን የነጻነት ታጋይ ወገኖቻችንንበህግፊት አስቀርበው ለማስቀጣት ከልብ ፈልገው ከሆነ በዚህ በአሜሪካ የህግ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትንእናየታጨቁትን ህጎች በሙሉ ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አምስተኛ፡  የህግ ስርዓት ቢኖር ኖሮ ግርማ ብሩ እና ሌሎች የኤምባሲው ሰራተኞች እንዳደረጉትሁሉገብረስላሴም በታላቁ የፍርድ ቤት ችሎት ቀርቦ ቃሉን መስጠት እና የማስተባበያ ማስረጃመስጠትየነበረበት መሆኑን የወያኔ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ በችሎት ፊት ቴዎድሮሰአድሃኖም እና የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረቦቻቸው ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ቃል መስጠትየጽሁፍ ማስረጃዎች ማቅረብይጠበቅባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ተከላካይ በግርማ ብሩ፣ በገብረስላሴ፣በአድሃኖም እና በሌሎች ቀሪ ሰዎች ላይመስቀልኛ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በመስቀለኛጥያቄዎች ሲጠበሱ ምነው ጫካ ገብተን ደርግንበተዋጋን በለው ሳይመኙ አይቀሩም።
ስድስት፡ ሶሎሞን ገብረስላሴ በጣም አስቸጋሪ ፈተና ሊያጋጥመው እንደሚችል መጠበቅይኖርበታል፡፡ማስረጃ ለመስጠት ወደአሜሪካ የሚመለስ ከሆነ የዲፕሎማት ያለመከሰስ መብትእንደሌለው ማወቅይኖርበታል፡፡ በጣም ከባድ በሆነ ወንጀል ክስ ምክንያት ምንም አይነትአስተያየት በዩናይትድ ስቴትስአሜሪካ አቃቤ ህግ በኩል አያገኝም። ያለመከሰስ መብቱእንደማይሰራ እና ክስ ተመስርቶበት ወደ ፍትህአካል ከመቅረብ እንደማያመልጥ ሊታወቅ ይገባል፡፡ገብረስላሴ አንድ ጊዜ በዩኤስ አሜሪካ ከተገኘ እናያለመከሰስ መብቱ ተነስቶ ጉዳዩ ፍርድ ቤትየሚታይ ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት ችሎት ከመቅረቡ በፊትወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውሎ ካለምንምዋስትና በቀጥታ ወደ ዘብጥያ ሊወርድ እንደሚችል ሊገነዘብይገባል፡፡
ሶሎሞን ገብረስላሴ እና የወያኔ አለቆቹ ከፍተኛ የሆነ የሲቪል ህግ ያለበትን እና አስከ አሁንድረስበህይወታቸው አይተውት በማያውቁት የፍትህ ችሎት ላይ ይገለገላሉ የሚል ከጥርጣሬ የዘለለእምነትአለኝ፡፡ በገብረስላሴ ድርጊት ምክንያት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ይደርስ የነበረውንጉዳት ከግምትውስጥ በማስገባት የወያኔ ኤምባሲ እና ገዥ አካል ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችልየረዥም ጊዜ የፍርድ ሂደትሊኖር ይችላል፡፡ በዩኤስ አሜሪካ በሲቪል ጉዳዮች ላይ የሚታየው እናየሚሰጠው ብይን የመረጃ መለኪያመስፈርቱነ ባገናዘበ መልኩ በአብዛኛው በሚቀርቡትማስረጃዎች ላይ መሰረት ተደርጎ ሲሆን ይህንንምለማሳካት ከባድ አይደለም፡፡
አብዛኞቹ አገሮች የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማድረግ ስምምነት አድርገው ዲፕሎማት ልከውበመተባበርከሚሰሩባት ሀገር ላይ የተላከው ዲፕሎማት ወንጀል ሰርቶ ከዚያች ሀገር በመሸሽአምልጦ ወደ ሀገሩየመጣን ዲፕሎማት በሀገራቸው ህግ መሰረት የሚቀጡ መሆኑን ማስተዋልአስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሶሎሞንገብረስላሴ በኢትዮጵያ ባሉት የወያኔ አለቆቹ ቅጣት ሊጣልበትእንደማይችል ጥርጥር የለውም፡፡ ይልቁንምየወያኔን ኤምባሲ ከጠላት ለመከላከል ባደረገውጀግንነት በወሮበላ ጓደኞቹ የበለጠ እንደሚወደስ እና ጀግናእንደሚባል መገመት ይቻላል፡፡
አገሮች እነርሱን በውጭ አገር ሄዶ ሊወክላቸው የሚችለውን ዲፕሎማት ለመምረጥ በአገሪቱካሉትየመንግስት ሰራተኞች መካከል በደረጃው እና በትምህርት ዝግጅቱ እና ብቃቱ ላይበመመስረትእንዴት እንደሚመርጡ እና ለምንም የማይሆን የወሮበላ ዲፕሎማት ለምን መርጠውእንደማይልኩየእራሳቸው የሆነ ምክንያት አላቸው፡፡ እነዚህ የመንግስት ሰራተኞች በዲፕሎማትነትተወክለውሲሄዱ ምን መስራት እንደሚጠበቅባቸው እና የሄዱበትን ሀገር ህጎች እና ደንቦች ማክበርብቻምሳይሆን የእራሳቸውን አገር ክብር ሊያዋርዱ ከሚችሉ ነገሮች እራስን ንጹህ በማድረግበጥንቃቄመራመድ እና በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ህዝቡ የእራሱን ፍርድ መስጠት እንዲችል መሰረትእንዲያዝዕድሉን መስጠት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
ዲፕሎማቶች ወንጀለኛ ከሆኑ የወሮበላ አፋኝ ስርዓቱ ታማኝ ሎሌዎች የሚመረጡ ከሆነገብረስላሴየሰራውን የመሰለ እኩይ ምግባር የተንጸባረቀበት ዓይነት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ስለሆነምወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱንልታላቀቀውአትችልም።
ገብረስላሴ በመግደል ሙከራ ምክንያት የተባረረ መሆኑ እውነት ነው፡፡ ሆኖም ግን ህጉ ብቻ ነውእርሱን ነጻሊያደርገው የሚችለው፡፡ በአገሮች መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነትበማስመልከትየ1961ዱ የቬና ስምምነት አንቀጽ 31 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፣ ”አንድየዲፕሎማት ወኪል የሆነሰው ከሚቀበለው አገር የወንጀለኛ ህግ ያለመከሰስ መብቱን ተጎናጽፏል“ይላል፡፡ ወደድንም ጠላንም የህግየበላይነት ማለት ሌላ ሳይሆን እንደዚህ ነው፡፡
አንደው በነገራችን ላይ….
“በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በሶማሌ ሚሊሻዎች ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችልአስጠነቀቀ“
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 15/2014 ሬውተርስ የተባለው የዜና አገልግሎት የዩናይትድ ስቴትስኤምባሲየሚስጠንቂያ መግለጫ ሰጥቷል በሚል የሚከተለውን ዘገባ አስነብቧል፣ “በቦሌ በሚገኙየምግብ ቤቶች፣ሆቴሎች፣ ቡና ቤቶች፣ የእምነት ቦታዎች፣ የገበያ አዳራሾች እና ታላላቅ የመገበያያቦታዎች ሌላ ማስታወቂያእስካልተሰጠ ድረስ የአሜሪካ ዜጎች እንዳይደርሱ መራቅ አለባቸውምክንያቱም እነዚህ ቦታዎች ሊከሰቱበሚችሉ በአሸባሪ ቡድኖች የጥቃት ኢላማ ውስጥ ናቸው“ይላል፡፡ ሬውተርስ በተጨማሪም እንዲህ የሚልጥቆማ ሰንዝሯል፣ “የኢትዮጵያ ባለስልጣኖችባለፈው ዓመት መጫረሻ አካባቢ አልሻባብ በአዲስ አበባከተማ ጥቃት ለመሰንዘር የአውጠነጠነውአስከፊ የሆነ የአጥፍቶ መጥፋት የሽብር አደጋ እንዳለ መረጃከደረሰው በኋላ የደህንነት ኃይሉበተጠንቀቅ ላይ መሆኑን“ ጠቁሞ ነበር፡፡
ይቅርታ አርጉለኝና ፣ ይኸ አስደንጋጭ ዜና ከተሰማ በኋላ የወያኔ ገዥ አካል እንደገና ሶማሊያንለመውረርእያደረገ ያለው ዝግጅት አለ ማለት ነውነው? እብደት ወይስ ብልሀት!? የዩኤስ ኤምባሲማስታወቂያኢትዮጵያ እንደገና ሶማሊያን እንድትወር የቀረበ ሀሳብን የመሞከረያ/መገምገሚያየዳግም ወረራ ወሬማናፈሻ ዘዴ ነውን? ዓላማው ይህ ከሆነ ሁሉም ነገር ሁሉ ፍጹም ውድቀትመሆኑን መገንዘብይኖርባቸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ ባለፈው ሴፕቴምበር 23/2014 ከወያኔ ባለስልጣን ጋር በመሆን ከመጠንያለፈክብካቤ ሲያደርጉ መታየታቸው እና በቪዲዮ ክሊፕ መለቀቁ ስለታሰበው ወረራ በትክክልእንድጠረጥርአድጎኛል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እንዲህ ሲሉተደምጠዋል፣ “…እኛ[ከወያኔ የልኡካን ቡድን አባላት ጋር] ሰላም ማስከበር እና በሰላማዊመንገድ የግጭት አፈታትንበሚመለከት አሰራሮቻችንን በማሻሻል እንዴት ውጤታማ በሆነ መልኩመፍታት እንዳለብን ተወያይተናል፡፡ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ከዓለም ከማንኛውም ሀገር የተሻለችትሆናለች – ሰላምን ከማስከበር አንጻርከብዙዎቹ አንዷ ናት፣ በጣም መጥፎ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜእና ግጭትን በማስወገድ ረገድ ከዓለምውጤታማ የሆነ የውጊያ ኃይል ያላት ናት…“ በቅርብ ጊዜየተደረገው ማስታወቂያ የማይቀር የአሸባሪዎችጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል እና ሌላኛው ጫማየወደቀ መሆኑን የሚያመላክት ነገር ነውን?
ወደ ኋላ መለስ በማለት እ.ኤ.አ በ2006 አጋማሽ መለስ ዜናዊ በሶማሊያ ህዝብ ላይ ሙሉአስደንጋጭእና አስከፊ የጦርነት ጥሪ ከማስተላለፉ እና ታንኮቹ የሞቃዲሾን ከተማ ከመውረራቸውእናከመርመርመርሳቸው ሁለት ወራት ቀደም ብሎ አልሻባብ እና ጂሀዲስቶች በኢትዮያ ላይ ጥቃትለመሰንዘርእየተባለ ብዙ ዲስኩሮች ተደርገው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 “ጂሀዲስቶች እየመጡነው/Jihadists are coming“ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ ጦርነቱ ከመካሄዱበፊት ይደረግ የነበረው የፕሮፓጋንዳስራ በጣም የሚያስደንቅ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር14/2006 የዩኤስ አሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች የቀድሞእረዳት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ጃንዳይፍሬዘር እንዲህ የሚል ውንጀላ ሰጥተው ነበር፣ “የዲፕሎማቲክ እናየደህንነት ባለስልጣኖችየእስልምና ህብረት ተዋጊዎች ከሌላው ወገን እገዛ ለማግኘት እና ከእነርሱ ጎንመሰለፍ እንዲችሉበኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ“ የሚል ውንጀላ አሰምተው ነበር፡፡ እ.ኤ.አዴሴምበር27/2006 በስተሰሜን በኩል በ90 ማይሎች ርቀት ላይ የምትገኘውንሰትራቴጂካዊየሆነችውን የጆሀርን ከተማ ከተቆጣጠሩ በኋላ የመለስ ዜናዊ ተዋጊ ኃይሎች ወደሞቃዲሾየሚያቃርበውን በረሀ መውረር ጀምረው ነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያየእስላማዊህብረት ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ “ተጨባጭነት ያለው የደህንነት አደጋ ደቅነዋል”በማለትየወረራውን አስፈላጊነት እና ፍትሀዊነት አጸደቀች፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት የዩናይትድስቴትስየመንግስት መምሪያ ቃልአቀባይ የነበሩት ጎንዛሎ ጋሌጎስ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኢትዮጵያበሶማሊያእየተደረገ ባለው የመሻሻል እድገት ላይ በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ የደህንነት ስጋትተደቅኖ እንዳለ እናህጋዊ እውቅና ያለው የሶማሊያ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት በጠየቀው እርዳታመሰረት ኢትዮጵያ ድጋፏንእየሰጠች ነው፡፡“
ሶማሊያን የመውረር ዕቅድ በተግባር ለማዋል እየተሰራ ስለመሆኑ የማውቀው ነገር የለም፡፡ እውነትለመናገርይህ አካሄድ አሁንም ቢሆን የሚፈይደው ነገር ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ እ.ኤ.አኦክቶበር8/2008 “በሶማሊያ የመለስ ዜናዊ የሰላም አስከባሪነት ሸፍጥ ፍጻሜ/The End of Pax Zenawi in Somalia” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት ላይ እንዲህ የሚልጽሑፍ አስነብቤ ነበር፣“እውነተኛው ጉዳይ ሲታይ ሶማሌዎች በመለስ ዜናዊ ወይም በሌላ በማንምግለሰብ ወይም ቡድን በኃይልበሚደረግ ተጽዕኖ ሰላም ማምጣት አይችሉም ፍላጎትም የላቸውም፡፡ ሶማሊዎች እና ሶማሊዎች ብቻናቸው የእራሳቸውን ችግሮች መፍታት የሚችሉት፣እናም ይህንን በሚጻረር መልኩ የሚደረጉጣልቃገብነቶች ሁሉ አንድም የለየላቸው ውሸቶችናቸው፣ አለያም ደግሞ ምንም ባለማወቅ የሚደረግአሳዘኝ የሆነ የዋህነት ነው፡፡“
ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱንልታላቀቀውአትችልም።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
Oct 23, 2014
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Wednesday, October 22, 2014

ሰበር ዜና፣ ህውሃት “የመለስ ትሩፋቶች” መጽሃፍን ለስለላ እየተጠቀመበት መሆኑ ታወቀ

በቀድሞው የመንግስት ኮሚውንከሽን ጉዳዮች ሚንስትር ድኤታ አቶ ኤርምያስ ለገሰ የተጻፈውን እና በብዙ በአለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተነባቢ የሆነው “የመለስ ትሩፋቶች” የተስኘው መጽሃፍ የኢህአዴግን መንግስት በተለይም ደግሞ የህውሃትን የጥፋት ዘመቻ በሰፊው  ያጋለጠ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም መጽሃፉ ወደ PDF File  ተቀይሮ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ በኢሜይል ሲሰራጭ ቆይቷል።
መጽሃፉ በተለይ በዲሞክራሲ አክቲቪስቶች ዘንድ ተፈለኣጊነት እንደሚኖረው በማወቅ
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የደህንነት ምንጮቻችን በዛሬው እለት እንዳስረዱን የህውሃት ኢህአዴግ የስለላ ማእከል ይህንን ፋይል ፊን ፊሸር ከተባለ የስለላ ቫይረስ ጋር በማጣመር በአሁኑ ሰአት በከፍተኛ ፍጥነት በኢሜይል በማሰራጨት ላይ ይገኛል።
ይህ ቫይረስ ከ“የመለስ ትሩፋቶች” ፍይል ጋር ተጣብቆ ወደ ኮምፒውተር ዳውንሎድ ከተደረገ፣ ኮምፒውተሮት ላይ ያለውን የግል ፍይሎች ወድ ህውሃት የስለላ ማእከል ከመላክ እልፎ  የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፥
1)  የህውሃት ይስለላ ኤጀንቶች በኮምፒውተሮት ላይ ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ያደርጋል
2)  ይህ ማለት በፈለጉት ሰዕት የኮምፒውተሮትን ካሜራ እና ማይክሮፎን በመጠቀም የግል እንቅስቃሴዎን መከታተል እንዲችሉ ያደርጋል
3) በኮምፒውተሮት ላይ በኢንተርኔት  የሚስገቧቸውን እንደ ክሬዲት ካርድ እና ሶሻል ሴኵሪቲ ያሉ ሚስጥራዊ ቁጥሮችን  በቀላሉ ማግኘት ያስችላቸዋል
4) በኢንተርኔት ላይ የሚጎበኟቸውን ድረ ገጾች እንዲሁም  በግልዎ የሚሳተፉባቸውን የማህበርዊ ሚድያ አካውንቶች እስከ ዩዘር ስም እና ፓስዎርዳቸው በቀላሉ ማግኘት ያስችላቸዋል
5)  ከቤተሰብዎ እና ከጏደኞችዎ ጋር የሚያደርጉትን የኢሜይል እና የስካይፒ ግንኙነት በቀላሉ ማንበብ እና ማዳመጥ እንዲሁም አካውንቶቹን ሌላ ጥቅም ላይ ማዋል ያስችላቸዋል
6)  በድርጅት ውስጥም ሆነ በግልዎ ለስብአዊ መብትዎ ወይም ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የሚሟገቱ ከሆነ፣ እርስዎን በሃሰት ወንጅሎ ለእስር አና ለስቃይ ለመዳረገ መንገድ ይከፍትላቸዋል


    ስለዚህ ይህ “የመለስ ትሩፋቶች” የሚል የPDF ፍይል በኢሜይል ከተላከልዎ የኢሜይል መልእክቱን ሳይከፍቱ ዲሊት በማድረግ እራስዎን ከጥቃት ያድኑ።
    አባይ ሚድያ/ ጥቅምት 2፣ 2007

    Tuesday, October 21, 2014

    ጋጠ ወጡ ማን ነው?

    የህወሃት ጉጅሌና ሎሌዎቹ መቼም ራሳቸውን የሚያይ አይንም መስታዎትም ያላቸው አይመስሉም። ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባሉ ነገሮች በአጠገባቸው የዘሩ የማይመስሉት ለዚህ ሳይሆን ይቀራል። ምናልባትም ብልግና፣ ጭካኔ፣ ግፍ፣ አውሪያዊ ስብእና፣ ወገን ካለህግ መግደልና ማዋረድ፣ የህዝብ ሃብት በጠራራ ጸሃይ መዝረፍ ለእነሱ የተፈቀደና የተሰጠ ጸጋ አድርገው ሳይቆጥሩት ይቀራሉ?
    ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰለጠነና የዳበረ ስርዓት አከባበር በሰፈነበት ከተማ ውስጥ ባልታጠቁ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩሱና ሲያስተኩሱ በመዋላቸው ለደረሰባቸው ትዝብት የነውረኝነት ሀፍረት እንደማፈር ሰላማዊዎቹንና በሰላማዊ መንገድ እስከ ሲቪላዊ አልታዘዝም ባይነት መብት ያላቸውን ጠንቅቀው አወቀው የተንቀሳቀሱትን ዜጎች ጋጠ ወጥና ባለጌዎች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ትንሽ ሲቀዠብርባቸው ደግሞ ኦባማ ስላነጋገረን የቀኑ ተቃዋሚዎች፣ ይህ አልበቃ ሲል ደግሞ የሻእቢያ ተላላኪዎች ሲሉም ተደምጠዋል። ከአውሬነት ብዙ ያልተለዩት ደጋፊዎቻቸው ተኩሱን ሲያንጣጣ የነበረው የቀድሞ የስዩም መስፍን የግል አሽከርና ሹፌር የነበረው ወዲ ወይኒ ግደይ ስለተባረረ ንዴታቸውን ከአደባባይ እንኳን መደበቅ አልቻሉም። እናስ እዚህ ውስጥ ጋጠወጡ ማነው? ሀገሩን የሚያስተዳድርበትን አራዊታዊና ህግ አልባ ስርአት በሰለጠነ ህዝብ ሀገር በአደባባይ ለኤግዚብሽን የሚያቀርብ መደዴ ወይስ እስከ ሲቪል እምቢተኝነት ድረስ ሊደርስ የሚችል መብታቸውን ጥንቅቀው የሚያውቁና በግፍ ስርአት ለሚኖረው ወገናቸው ድምጽ ያሰሙ የህዝብ ልጆች?
    በዘሩ ታማኝነት ተመርጦ ከስዩም መስፍን ሾፌርነት ውጪ ቅንጣት የዲፕሎማሲ እውቀት የሌለውን ደንቆሮ የዲፕሎማት ማእረግና ሽጉጥ አስታጥቆ ዋሽንግተን ከሚልክ መንግስት በላይ ጋጠወጥና አጉራ ዘለል ከየት ይገኛል።
    እውነቱ ግን ወዲህ ነው ያለው። ቢያንስ በነጻው አለምየሚኖሩ የኢትዮጵያ ልጆች በሀገራቸውና በወገናቸው ላይ በሚደርሰው ስቃይ ውርደትና ግፍ ተንገፍግፈዋል። የወያኔ ሹማምንት ግፋቸውን እንዲያቆሙ ያሰሩዋቸውን እንዲፈቱና ሀገር ዝርፊያ እስኪያቆሙ ድረስ በገቡበት እየገባ ቁም ስቅላቸውን ማሳየትና ጋጠወጥና የነውረኛ ስርአት አገልጋዮች መሆናቸውን ማጋለጡን ይገፉበታል። በሰሩት ወንጀል አለምአቀፍ ፍርድቤቶች መድረክ ላይ እየጎተተ የሚያቀርብበት ጊዜም ሩቅ አይደለም።
    የወጋ ይርሳ እንደሆነ እንጂ የተወጋ አይረሳም። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሰላማዊ ተቃዋሚውን ድርጅት አባል በብረት ሶዶማዊ ምግባር የፈጸሙትን ጋጠ ወጥ የወያኔ ተላላኪዎች ማን ይረሳል። በየቤቱና በየጎዳናው በዱላ የሚቀጠቀጡትና ደማቸውን ሲጎርፍ ያየናቸው አዛውንት ሙስሊም ወገኖቻችን ደም እንዴት እንረሳለን። ሬሳቸው እንኳን ክብር አጥቶ የጋጠወጥ ወያኔ መጫወቻ የሆኑትን የኦጋዴን ወገኖቻችንን ማን ይረሳል። ጋምቤላ ጫካ ውስጥ እንደደኑ ተጨፍጭፈው የተቆለሉትን አኙዋኮች ማን ይረሳል። ከየኖሩበት ቦታ በግፍ እየተፈናቀሉ የሚንከራተቱትን እና የሚሞቱትን አማሮች ማን ይረሳል። በቆራጥነት ብቻ በሰላም መንገድ እንታገላለን ብለው በተነሱ ወህኒ የተወረወሩትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የታሰሩትንና የተሰደዱትን ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች የምንረሳቸው ስንሞት ብቻ ነው። ከየጎረቤት ሀገሩ እየታፈኑ የሚሰቃዩትን እነ አንዳርጋቸውን እና ሌሎች የሞቱትን ማን ይረሳል።
    ህዝባችንን ወደ ሰላማዊ አመጽም ሆነ ወታደራዊ አመጽ እየገፋው ያለው ይህ የወያኔ ባህሪ ነው።
    ግንቦት 7 ከዚህ አራዊታዊ ስርአት ጋር ሆናችሁ በተለያየ ምክንያት በህዝባችሁ ስቃይ ላይ የምትተባበሩ ወገኖች ሁሉ በአገኛችሁት አጋጣሚ ከእዚህ እኩይ ስርአት ተግባራት ራሳችሁን እንድታወጡ፣ ከቻላችሁ በውስጥም ሆናችሁ ወገናችሁን ሳትበድሉ ትግሉን እንድትቀላቀሉ ይመክራል።
    መላው ህዝባችን በያለህበት ራስህን በራስህ እያደራጀህ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎችን ጀምር። በመላው አለም ዙሪያ ተሰደህ የምትኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለወገንህ ለራስህም ትንሳኤ ተነስ!!
    ትግላችን የመጨረሻውን መጀመሪያ እየተያያዘ ነው። የትልቅ ሀገርና ትልቅ ህዝብ ባለቤቶች ስለሆንን ከወያኔ ወሮበላ ጉጅሌ በበለጠ የሚገባን ህዝብ ነን!!

    ኢንሳ በኢሳትና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

    የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሰሞኑን አሻሽሎ ያዘጋጀውና የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት እንዲወያዩበት የተዘጋጀው  ሰነድ ለኢሳት የደረሰ ሲሆን፣ ሰነዱ የመንግስት የመረጃና የደህንነት መስሪያ ቤት ወይም ኢንሳ በኢሳት በአሜሪካ እና በጀርመን ድምጾች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ከመማጸን ጀምሮ መንግስት በሴቶች፣ በወጣቶችና በምሁራን ስም የሃይማኖት ማህበራትን እንዲቋቋሙ እገዛ እንዲደርግ፣ በሰርተፍኬትና በዲግሪ ደረጃ የሃይማኖት ትምህርት የሚሰጡ ተቋማት እንዲቋቋሙ እገዛ እንዲያደርግ ይመክራል።
    የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጥቅምት 2007 ለኢህአዴግ የምክር ቤት አባላት ያዘጋጀው ሰነድ 16 ገጾች ሲኖሩት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ተከፋፍሎ፣ ለመንግስት ህልውና ስጋት ደቅኗል ባለው የሃይማኖት አክራሪነት ዙሪያ የተለያዩ የመፍትሄ ሃሳቦችን ይሰነዝራል።
    ሰነዱ ወጣቱን ከስራ አጥነት ችግር መታደግ በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ” በአገራችን በተለይ ከ97 ዓም ድህረ ምርጫ ቀውስ በመማር የወጣቱ የልማትና ተጠቃሚነት፣ የመልካም አስተዳደርና የተሳትፎ ጥያቄዎች ለመመለስ ያደረግነውና ያልተሳካ ውጤት ያገኘነውም በመሰረቱ ለስራ አጥነትና ለተስፋ መቁረጥ የተጋለጠ ወጣት ሊኖርበት የሚችለውን ተጋላጭነት በመኖሩ ነው አሁንም ይህ ስጋት በተማረው እና መሬት በሌላው ወጣት ዘንድ በስፋት አለ። በዚህ ረገድ ባለፉት ሰባትና ስምንት አመታት እጅግ የሚያስመካ ስራ ሰርተናል ማለት አይቻልም። ” ይልና ” በገጠርም በከተማም የትምህርት እድልን በማስፋፋት፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጡ በግብርናና ከግብርና ውጭ የሚከናወኑ የልማት እድሎችን በመፍጠርና በማስፋት የወጣቱን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተሻለ ደረጃ ለማስቀጠል የመሬት እጥረት ከስደተኛ ወጣቱ ጋር ተዳብሎ ከፍተኛ የፖለቲካ ስጋት ነው ለዚህም እስካሁን በጥቃቅንና አነስተኛ የሰጠነው በቢልዮን የሚጠጋ ብር መመለስ አልተቻለም። ” ብሎአል።
    ሰነዱ ” በሃገራችን የሚንቀሳቀሱ የሃይማኖት አክራሪ ቡድን መሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑንም” ይጠቅሳል። “በመላ አገሪቱ በቀጣይ ለፓርቲያችን አስቸጋሪ ሁኔታ እና ለአላስፈላጊ ውድቀት የሚዳርገው በክርስትናም ሆነ በእስልምና እምነት ላይ ያለው አክራሪነት ነው” የሚለው ሰነዱ” ሁለቱ ሃይማኖት እርስ በርስ የሚያደርጉት መገፋፋት ለፖለቲካው መሪነት አማራጭ እና ከእርምጃ መንግስትን የሚታደገው ሆኖ ይገኛል ” ብለአል።
    በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ ሃይሎችን በቀጣይነት ማጋለጥና መሰረት ማሳጣት በሚልው ክፍል ደግሞ ” የመንግስትን እቅዶችና አፈጻጸም እንዲሁም በአፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎችን የሚለከት መረጃ ለህዝቡ በፍጥነትና በግልጽ ማቅረብ እንደሚገባ” ይመክራል። የክልል እና የፌደራል ሚዲያዎችንም በይዘት ቁጥጥሩ ሊጠብቅ እንደሚገባ ከገለጸ በሁዋላ ” የጥፋት ሃይሎች የሚነዙዋቸውን የሃሰት ፈጠራዎች በሙሉ እየተከታተልንና ምላሽ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እየለየን በብቁ መልእክቶች መመከት ይገባል” ሲል ያስቀምጣል።
    ኢሳት፣ ቪኦኤ፣ የጀርመን ድምጽ የሬዲዮ ስርዓቶች በኢንሳ ቁጥጥር ስር ማዋል ያስፈልጋል፣ የሚለው ሰነዱ እያንዳንዱን የፈጠራ ድርሰት በዝርዝር ማንሳትና ይህንኑ ለመመከት የሚያስችል መልዕክት ለመቅረጽ ከመሞከር ተቆጥበን በየወቅቱ በሃይማኖት ሽፋን የፖለቲካ ንግድ ላይ የተሰማሩ ወገኖች የሚያነሷቸውን ነጥቦች መነሻ በማድረግ ጠንካራ የምከታ ስራ መስራት ተገቢ ነው ብለአል። በተለይ በሀገር ውስጥ ያሉ አባሎቻቸው ላይ የማያቆራርጥ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው ሲል ይመክራል።
    የሃይማኖት ተቋማትን መደገፍ በመደገፍ በተናጠልና በጋር የውስጥ ተጋላጭነታቸውን እንዲያስወግዱ ማበረታታት በሚለው ተራ ቁጥር አንድ ስድስት ላይ ደግሞ ” ሃይማኖታዊ የወጣት፣ የሴቶች፣ የምሁራን አደረጃጀቶች ተፈጥረው ራሳቸውንና ሌላውን ተከታይ በተደራጀ ሁኔታ የተሟላ ሃይማኖታዊ እውቀት እንዲኖረው ከአሉባልታዎች እንዲጠበቅና የአክራሪነት አመለካከትና ተግባር የሚታገል አቅም ሆኖ እንዲደራጅ መደገፍ ያስፈልጋል። ተጠሪነታቸውን በየራሳቸው ሃይማኖት ተቋም በማድረግ ህገመንግስታዊ ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆኑ መደገፍ ይቻላል። ” ሲል ይተነትናል።
    ” እያንዳንዱ የሃይማኖትና የእምነት ተቋም መሪዎች ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ከህገመንግስታዊ ስርአቱ ጋር የሚጋጩ እንዳልሆኑና ከዚህ ወጣ የሚል አካል ሲኖር በአባታዊ ምክር የመመለስና የማስታገስ፣ የማይታረም ከሆነም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የህግ የበላይነትን ማስከበት ” እንደሚጠበቅባቸው የሚገልጸው ሰነዱ፣ ” የሰባኪያን/ዳኢዎች ሚና የበለጠ ለማጎልበትና የተጠያቂነት ስርአት ለመትከል እያንዳንዱ የሃይማኖት ተቋም የራሱን መምህራን የሚለይበትን የመታውቂያ ስርአት ሊያበጅና በዚህም የክትትል ስራ እንዲሰሩ መደገፍ ይቻላል” ይላል።
    ከሁሉም በላይ የአክራሪነት ተጋላጭነት እየመጣ ያለው የሃይማኖታዊ እውቀት ክፍተት የሚሞላ የተማረ የሰው ሃይል እየተሟጠጠ በመሄዱ” በመሆኑ ፣ በአጫጭር ኮርሶችም ይሁን በመደበኛ ፕሮግራም ከሰርትፍኬት አንስቶ እስከ ዲግሪ ፕሮግራሞች የሚያስተምር የትምህርት ተቋም አስፈላጊ ይሆናል” ብሎአል።
    ኢሳት ዜና