ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ "ኮ/ል አለበል አማረ የድርጅቱ መስራችና ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን፣ ውጭ አገር ከሄዱም በሁዋላ ድርጀቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን" ካወሳ በሁዋላ፣ ድርጅቱ መስዋትነት እየከፈለበት ያለው የነጻነት ትግል በቶሎ ግቡን እንዲመታ መሬት ላይ ወርዶ መታገሉ የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ተብሎ ስላሚታመን በተደጋጋሚ እንዲመጡ ቢነገራቸው ሊመጡ ባለመቻላቸውና አሁን ባለንበት ጊዜ ድርጅቱን ውጭ ሃገር ተቀምጦ መምራት ስለማይቻል ከድርጅቱ ሊ/መንበርነት ወርደው በአባልነት እንዲቀጥሉ በሙሉ ድምጽ ወስነናል "ብለዋል።
ድርጅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ እንዲሰጠውም ጠይቋል። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና ግንቦት 7 በቅርቡ ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።
Thursday, September 4, 2014
Thursday, July 31, 2014
አገራዊ ጥሪ ለመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት
ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላትን ከአለቆቻቸው ለይቶ ይመለከታል።
የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ከፍተኛ ሹማምንት ከህወሓት የተቀዱ፣ ለህወሓት ሥልጣን የቆሙ፣ ዘረኞች፣ ፋሽስቶችና ሙሰኖች መሆናቸው በገሃድ የሚታወቅና በተደጋጋሚ ጥናቶችም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። በዘመነ ወያኔ የሠራዊት አዛዥነት ሹመት መሥፈርቶች ዘር፣ የፓለቲካ አመለካከትና ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት ነው። በዚህም ምክንያት ሁሉም ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች የተያዙት ሙሉ በሙሉ የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ነው። እነዚህ የጦርና የፓሊስ ሹማምንት ኢትዮጵያን ወረው እንደያዙት አገር ሲዘርፉ፣ ሕዝቧንም ሲገሉና ሲገርፉ እንሆ 23 ዓመታት አልፈዋል። በእነዚህ 23 ዓመታት ትግራይን ጨምሮ በደል ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ግዛት እና የኅብረተሰብ ክፍል የለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእነዚህ ፋሽስቶች ተረግጧል፣ ተዋርዷል፣ ተግዟል። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በእነዚህ እኩይ የሠራዊቱና የፓሊስ አዛዦች ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። የወያኔ የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች አገራችን እያደሙ፤ ሕዝባችንን እያስለቀሱ ነው። በወያኔ ፋሽስት የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች ጥምረት ሰቆቃ የሚፈፀምበት የኅብረተሰብ ክፍል በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል። የወያኔ ማሰቃያዎችን የሞሉት የፓለቲካና የሀይማኖት መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች መሆናቸው ለዚህ አንድ ማሳያ ነው።
የሠራዊቱ የበታች ሹማምንትና ተራ አባላት ጥንቅር ግን ከአዛዦቹ ፈጽም የተለየ ነው። የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ከመላው የኢትዮጵያ ግዛቶች የተውጣጡ፤ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በነፃነት እጦት፣ በመብቶች መገፈፍ እና በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩ ዜጎች ናቸው። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዦቹ እየታዘዘ ወገኑን የሚበድል ቢሆንም ራሱ ከመበደል ግን አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዡ ታዞ ሌላኛውን ወገኑን ቢያስርም ሹሙ ፊቱን ባዞረበት ጊዜ እራሱ ደግሞ ከመታሰር አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር ወያኔ አዞት ምስኪኖችን ይደበድባል፤ ራሱ ደግሞ በወያኔ ይደበደባል። የኢትዮጵያ ፓሊስ በወያኔ ትዕዛዝ ንጹሀን ዜጎችን ያስራል፣ ያሰቃያል፤ እራሱ ደግሞ በወያኔ ይታሰራል፣ ይሰቃያል። ይህ ምን የሚሉት ባርነት ነው? የወያኔ ሹማምንቶች በሚመሩት የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በህወሓት የሚደርስባቸው በደል ሌላው ኢትዮጵያዊ ከሚደርስበት ይብስ እንደሆን እንጂ የሚያንስ አይደለም።
ግፍ መብቃት አለበት። በጥቂት የህወሓት ሹመኖች ትዕዛዝ በኢትዮጵያዊው ወታደር ላይ የሚደርሰው ውርደት ማብቃት አለበት። ሠራዊቱ የኢትዮጵያ እንጂ የህወሓት ሠራዊት አይደለም፤ ሊሆንም አይገባውም። ሠራዊቱ ለራሱ ነፃነት ብቻ ሳይሆን ለአገርና ለሕዝብ ደህንነት ዘብ የመቆም ኃላፊነት አለበት። የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት የባንዳ ሠራዊት ሆኖ ሕዝብን በማሰቃየትና ሀገርን በመበደል ተግባር ላይ ተሠማርቶ ማየት አንሻም። ይህንን ለራሱ ክብር ያለው፤ አገሩንና ሕዝቡን የሚወድ የሠራዊቱ አባልም የሚፈቅደው ጉዳይ አይደለም።
ስለሆነም ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚከተለው ሀገራዊ ጥሪ ለመላው የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ያቀርባል።
ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያ ወይም የፓሊስ ሠራዊት አባል! በጥቂት የህወሓት ፋሽስቶች መዳፍ ውስጥ ሆነህ የገዛ ራስህን፣ የቤተሰቦችህን፣ የወገንህን እና የአገርህን ስቃይ ማራዘምህን አቁም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ እንጂ የጥቂት ጎጠኞች ሎሌ ልትሆን አይገባም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታ እንጂ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ስጋት መሆን የለብህም። አንተ የመጪው ትውልድ አርዐያ እንጂ ሕፃናትንና ወጣቶችን ማስፈራሪያ መሆን የለብህም።
የኢትዮጵያ ወታደር ሆይ! ራስህን ተመልከት! ራስህን ታዘብ! ዛሬ ያለህበት ሁኔታ አሳፋሪ ነው። አዛዦችህ አገርን፣ ትውልድንና ታሪክን ለማጥፋት የተነሱ ናቸው። አንተን ተጠቅመው ነው ይህንን ዓላማቸውን የሚያስፈጽሙት። ይህ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለልጅ ልጆችህ ውርደት ነው። ከወያኔ ባርነት ራስህን ነፃ አውጣና የነፃነት ታጋዮችን ተቀላቀል። ወያኔ መጥፋቱ አይቀርም። ወያኔ የቀድሞውን ጦር እንደበተነው አንተን ለመበተን የሚሻ የለም። አንተ ዛሬ ከወገን ጋር ወገንተኛነትህን ካሳየህ ከአገዛዙ ጋር እጠፋለሁ ብለህ አትስጋ። ለዚህም ነው አንተ ዛሬ በግልም ሆነ በቡድን የምትወስደው እርምጃ የአገራችንን ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱን እጣ ፈንታ ይወስናል ብለን ወገናዊ ጥሪ የምናቀርብልህ።
ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ወገናችን!ከበዳዮች ጎን ሳይሆን ከተበዳዮች ጎን ቁም። ከገራፊዎችና ገዳዮች ጎን ሳይሆን ከነፃነት ታጋዮች ጎን ሁን። ዛሬውኑ ወስን። አሁን የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል ቀላል ሆኗል። ያሉበትን ታውቃለህ፤ ተቀላቀል። አልያም የጠመንጃህን አፈሙዝ በፋሽስት አለቆችህ ላይ አዙር። ይህንን እርምጃ በመውሰድ ከታሪክ ተወቃሽነት እራስህን በመታደግ ለአገርህና ለወገንህ አለኝታህን አረጋግጥ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
Saturday, July 12, 2014
ወያኔ አንዳርጋቸው ያፈነበት እለት የሚረግምበት ቀን ሩቅ አይደለም!
የ
ህወሃት ጉጅሌ እንደማንኛውም አምባገነን ከፊት ከነበሩ አምባገነኖች ቅንጣት ትምህርት አልተማረም። ወያኔዎች በእብሪት የያዙት ስልጣንና ከህዝብ የዘረፉትን ንብረት የሚያጡት እየመሰላቸው በባነኑ ቁጥር የነጻነት አርበኞችን በማፈን በመግደልና በማሰቃየት ፍርሃታቸው የተወገደ ይመስላቸዋል።
ወያኔ የእኛ መሪና የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት አርበኛ በሆነው አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ያካሄደው አፈና ከአፈናውም በሆላ በሚያደርሱበት አካላዊ ስቃይ ፍርሃታቸው የሚወገድ ወይም ስርአታቸው ከሞት የሚተርፍ መስሏቸው ከሆነ በእጅጉ ተሳስተዋል። አንዳርጋቸው ዛሬ በእጃቸው ሆኖ በነጻነት ይኖር ከነበረበት በበለጠ የሚለበልባቸው የውስጥ እግር እሳት ይሆናል።
አንዳርጋቸው ሰበአዊ ምቾቱንና ለራሱና ለቤተሰቡ መኖርን አቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻነት በህይወቱ ሊጋፈጥ ከቆረጠ ቆይቷል። እኛ የትግል ጓዶቹና ለህዝብ ነጻነት የቆሙ ሃይሎች ሁሉ አንዳርጋቸውን እናውቀዋለን። ወያኔ በአካሉ ላይ የለመደውን ስቃይ ጀምሮበታል፣ ከዚህ የበለጠም ጉዳት እንደሚያደርስበትም እናውቃለን። የአንዳርጋቸውን ታላቅ የነጻነት ሰውነትና ክብረ ህሊናውን፣ በአርበኝነቱ የሚሰማውን የኩራት ስሜቱን ለግፈኞች ያለውን ንቀትና መጸየፍ ሊለውጡ እንደማይችሉ አስረግጠን እናውቃለን።
አንዳርጋቸው እንደሁላችን ሰው ነውና በፈሪዎች በትር የሚደርስበት አካላዊ ስቃይ ግን ለህዝባችን የገባነውን ቃል ውሳኒያችንን እና አቋማችንን እንደብረት ያጠነክረዋል እንጂ አያላላውም።ይልቁንም በአንዳርጋቸው መታፈን ምክንያት ከመላ ሀገራችን በአለም ዙሪያ ከተበተነው ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች የነፃነት ሃይሎች የምንሰማውና እየሰማን ያለነው የሚያስገመግም ህብረ ድምጽ ከብረት የሚያጠነክር ሃይል ሆኖኗል።
አንዳርጋቸው የዘራው የነጻነት የአርበኝነት ዘር ከመብቀል አልፎ እየጎመራ በመሄድ ላይ ነው። አንዳርጋቸው ሺ አንዳርጋቸውን ተክቷል። ወያኔ አንዳርጋቸውን በማፈንና በእጁ አስገብቶ በራሱ መስኮት ቲቪ ስቃዩን እንግልቱን በማሳየት ሊያላምጠው የማይችል የብረት እንክብል ነው የነከሰው። ይህንንም ሳይውል ሳያድር ያየዋል፡፡
መላው ህዝባችን በእልህና በቁጭት ላይ ያለህ ወገናችን ና የሀገራችን የነፃትና የዴሞክራሲ ሃይሎች በሙሉ፡- በአንዳርጋቸው ላይ ወያኔ የፈጸመው የአሸባሪዎች ውንብድና በየአንዳንዳችን ላይ የተፈጸመ በደል ግፍ ነው።
ይህንን የሽብርና የውንብድና ስርአት ለማስወገድ አብረን ከመነሳት ውጪ አማራጪ የለንም። የልዩነታችንን አጥር አፍርሰን የወየኔን እድሜ እንድናሳጥር ግንቦት 7 ለሁላችንም ጥሪውን ያቀርባል።
አንድ ሆነን የአንዳርጋቸውን ስምና ምግባር እንሁን!
አንዳርጋቸው የዘራው እና እየጎመራ ያለው የአርበኝነት ንቅናቄ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ወያኔ አንዳርጋቸውን ያፈነበት ቀን የሚረግምበት ጊዜ ከዚህ በኋላ ሩቅ አይሆንም፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
Friday, July 11, 2014
ለኢትዮጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥን ቦርድ ቅሬታን ስለማሳወቅ፣ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
በድርጅታችሁ ድረገፅ በግልፅ እንደሠፈረው፦
“ESAT was established on April 24, 2010 to present accurate and balanced news, analysis and information, as well as entertainment, talk shows, documentaries, sports and cultural programming pertaining to Ethiopia and the rest of the world.”ይህንን ቃላችሁን ታከብራላችሁ ብሎ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምን ነበር። ድርጅታችንዚህ እምነቱም ባሻገር አባሎቻችንለኢሣት ዕድገት እና ሥራ መቃናት የቻሉትን ሁሉ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የቦርዱ አመራር ያውቃሉ ብለን እናምናለን። የዜና አገልግሎቱም እንዲያድግ እና ዓላማው ይበልጥ የሠመረ እንዲሆን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ከፍተኛ ፍላጎቱ ነበር። MWAO_0029_14_To-ESAT-RequestingCorrectiveAction…..read in pdf.
“ESAT was established on April 24, 2010 to present accurate and balanced news, analysis and information, as well as entertainment, talk shows, documentaries, sports and cultural programming pertaining to Ethiopia and the rest of the world.”ይህንን ቃላችሁን ታከብራላችሁ ብሎ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምን ነበር። ድርጅታችንዚህ እምነቱም ባሻገር አባሎቻችንለኢሣት ዕድገት እና ሥራ መቃናት የቻሉትን ሁሉ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የቦርዱ አመራር ያውቃሉ ብለን እናምናለን። የዜና አገልግሎቱም እንዲያድግ እና ዓላማው ይበልጥ የሠመረ እንዲሆን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ከፍተኛ ፍላጎቱ ነበር። MWAO_0029_14_To-ESAT-RequestingCorrectiveAction…..read in pdf.
Wednesday, May 14, 2014
አምነስቲ በኦሮምያ ግድያ የፈጸሙት ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠየቀ
-አለምአቀፉየሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። በመዳ ወላቡ ዩኒቨርስቲ 3፣ በጉደርና በአምቦ ከ15 በላይ ሰዎች መገደላቸውን አውስቷል::አብዛኞቹ ሟቾች ተማሪዎች እና መምህራን መሆናቸውን የተለያዩ የአይን እማኞችን በማነጔገር በሪፓርቱ ያሰፈረውአምነስቲየሟቾች ቁጥር በገለልተኛ ወገኖች ቢጣራ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችልም ገልጿል።
ከሟቾች መካከል የ11 አመት ህጻናት እንደሚገኙበት የገለጸው አምነስቲ፣ መንግስት ከሚገባው በላይ ሃይል መጠቀሙንም ጠቁሟል።
በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች የታሰሩት ሰዎች ቁጥር በሺዎች እንደሚቆጠር የኦሮሞ ፌደራሊስት ንቅናቄን በዋቢነት ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ አካባቢዎችና በዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጸጥታ ሃይሎችን ማሰማራታቸውን አምነስቲ አክሎ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት_የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት ከልክ ያለፈ የሃይል እርምጃ በገለልተኛ ወገኖች እንዲጣራ እንዲያደርግ አንዲሁምአጥፊዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡና የታሰሩት እንዲፈቱ ድርጅቱ ጠይቋል።
ኢሳት ዜና
Thursday, May 8, 2014
ተዋርዶ መገዛት ይብቃን!
የወያኔ ሹማምንትና አደርባይ ሎሌዎቻቸው አንገቱን አስደፍተው የሚገዙትንና የሚዘርፉትን ህዝብ ይበልጥ ስብእናውን አዋርደው ሊገዙት ለምን እንደሚፈልጉ የማይገባን ጥቂቶች አይደለንም። እነዚህን ግፈኞች ቀረብ ብሎ ላያቸው ግን ይህ ድርጊታቸው እንቆቅልሽ አይደለም።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝብ አይሰማንም ብለው በር ዘግተው ከሚያካሂዷቸው ጉባኤዎች እያፈተለኩ የሚወጡ የቪዲዮና የድምጽ መረጃዎች የነዚህን ግፈኞች ስነ ህሊና ግልጽ አድርገው ያሳያሉ።
ከወራት በፊት የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሀገር ሽማግሌ ሰብስቦ የወያኔ አላማ ከእሱ ጎሳ ጋር ተባብሮ ሌላውን ብሄረሰብ የበታች አድርጎ መግዛት መሆኑን ሲናገር የሚያሳይ ቪዲዮ ተመልክተን ነበር። የክልሉን ህዝብ የሚጨፈጭፈው ለዚህ ሲባል መሆኑን ለማሳመን ነበር በሩን ዘግቶ የተናገረው።
ሰሞኑን ደግሞ አንድ የአማራ ክልል የወያኔ ሹምና ሎሌ ልከአንደ እንደሶማሌው ሹም ካድሬዎቹን ሰብስቦ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቀ፤ ለ እግራቸው ጫማ የላቸውም በሚላቸው የአማራው ተወላጅ ላይ ለሰሚ በሚሰቀጥጥ ቋንቋ ያወርደው የነበረ ስድብ የሚነግረን ተጨማሪ ነገር ተመሳሳይ የወያኔን ምንነትን ነው።
እነዚህ ግፈኞች በህዝብ ላይ የሚሰሩትን አዋርዶ የመግዛት ግፍና ዝርፊያ አሳምረው ያውቃሉ። ከዚህበላይ ደግሞ የዚህ ሁሉ ንቀትና ጥላቻ ሰለባ የሆነው ህዝብ እንደሚጠላቸውና ቀን እንደሚጠብቅላቸው ያውቃሉ። ስለዚህም ህዝቡን ይፈሩታል። ከፍርሃታቸው የሚያስታግስላቸው ህዝቡን ይበልጥ ቅስሙን ለመስበር ከቻሉ ስለሚመስላቸው በተዘጋ ቤት ውስጥ እየተሳለቁ ያስጨበጭባሉ።
የወያኔ ሹማምንት የህዝብ ብሶትና እሮሮ ማየሉን ሲሰሙ መልሰው ህዝቡን የሚሰድቡትና የሚያጠቁት፣ እንዲሁም ግንቦት 7 ሲጠነክርባቸውና የመውደቂያ ቀናቸው ሲያስቡ አሸባሪ ብለው የሚሸበሩትም ለዚህ ነው።
ህዝቡ ቅስሙ ከተሰበረ ሰላም ያገኙ ይመስላቸዋል። ወያኔዎችና የሲቪል ሰርቪስ ሎሌዎቻቸው በር ዘግተው በተሰበሰቡ ቁጥር ይህንን ፍራቻቸውን የሚያስታምሙት ህዝቡን ቅስሙን መስበራቸውን ለማረጋገጥ በሚያካሄዱት ወይይት ነው። ለዚህ ነው ህዝባችን እርስ በርሱ የሚባላበትን፤ እርስ በርሱ የጎሪጥ የሚተያይበትን መንገድ ሲቀይሱ የሚውሉት በዚህ ምክንያት ነው።
ወያኔዎች በየክልሉ እንደ አለምነው መኮነን አይነት ከጭንቅላታቸው፣ከህሊናቸው ይልቅ አፋቸው የሚቀድም ጥራዝ ነጠቅ ሎሌዎችን የሚያሰማሩትም የህዝብን ቅስም የሰበሩ አየመስላችዉ ነው::
ወያኔና ሎሌዎቹ ህዝብንየሚያታልሉበት ካርድ ከእንግዲህ አልቋል። አዋርደውናል፣ ገድለውናል፣ አስረውናል፣ አስርበውናል፣ ለስደት ዳርገዉናል፣ አለያይተውናል። ከዚህ በላይ ምን ሊያደርጉን ይችላሉ? ስለዚህ ቀኑ መሽቶባቸዋል እናበፍጥነት ሊወገዱ ይገባል።
በዚህ ወሳኝወቅት ሁሉምየኢትዮጵያዊእንደ አንድ ህዝብ በአንድ ላይ በመነሳት የወያኔ ጉጅሌና አጎብጓቢ ሎሌዎቻቸው ያዘጋጁልንን ወጥመድ መስበርና ክብራችንን ማስመለስ ይኖርብናል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተዘጋው የወያኔ በር እየተዋረደ፣ እየተገረፈ ነውና።
ግንቦት 7 እንደሁልግዜው ዘላቂ መፍትሄ የሆነው ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን እንዲጎለብት፣ ማንነታችን ክብራችን እንጂ መሳለቂያ እንዳይሆን በተባበረ ሃይላችን የክብራችን ባለቤት እንድንሆን ጥሪውን ያቀርባል።
በተባበረ ሃይላችን ክብረ-ስብእናችንን እናስመልስ! ተዋርዶ መኖር ይብቃን! በቃ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የዞን ዘጠኝ ጀግኖች ብረሳችሁ ታሪክ ይርሳኝ” በውቀቱ ስዩም
ነጻነትና ፍትህ በሌሉበት አገር ውስጥ የልማት አውታሮችን መገንባት የት ለመድረስ ነው?የባቡር ሀዲድ ግንባታ ሳይ፣ የሚመጣብኝ እንደ አይሁድ በባቡር ታጭቀው ወደ መግደያ ጣቢያ የሚጓጓዙ ዜጎችን ነው። የኤሌክትሪክ ግንባታ ሳይ የሚመጣብኝ የኤሌክትሪክ መግደያ ወንበር ነው። የሚቆፈር ነገር ሳይ ድቅን የሚልብኝ የጅምላ መቃብር ነው።
የዞን ዘጠኝ ጀግኖች ብረሳችሁ ታሪክ ይርሳኝ። ባንድ በኩል የዘመናችሁ ተካፋይ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል። በሌላ በኩል፣ የመከራችሁ ተካፋይ ባለመሆኔ ሐፍረቱን አልችለውም። ያም ሆኖ ‹‹በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዛው ነው። ወትሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው›› የሚለው የዓለሙ አጋ የበገና እንጉርጉሮ ባጸደ-ነፍስ ላሉት ብቻ ሳይሆን ባጸደ-ወህኒ ላሉትም ይሆናል። ስሜቴን እንዴት መግለጽ እንዳለብኝ አላቅም። የገላውድዮስ ዜና- መዋእል ጸሐፊ በዚህ ሰዓት የሚሰማኝ ስሜት ከምእተ አመታት በፊት ተሰምቶት ነበር።
መዓልትኒ ኮነ ሌሊተ፣ዘኢነአምሮ ወጽልመት ዘኢልማድ መጽአ
ወደፈነ እንስሳ ወሰብአ
ወደፈነ እንስሳ ወሰብአ
(ቀኑ ሌሊት ሆነና፣ ወጋገኑ ተሰደደ
እንግዳ ጨለማ መጣ፣ጠባዩ ያልተለመደ
ሰውን፣ እንስሳን ጋረደ) በውቀቱ ስዩም (በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)
እንግዳ ጨለማ መጣ፣ጠባዩ ያልተለመደ
ሰውን፣ እንስሳን ጋረደ) በውቀቱ ስዩም (በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)
Subscribe to:
Posts (Atom)