Monday, July 20, 2015

ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ

ሐምሌ 12 2007 ዓ.ም.
ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።
ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።
አርበኞች ግንቦት 7 አመራሩን ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን እና ትግሉ በሚጠይቀው ቦታ እንዲገኙ የሚያደርግ መሆኑ ሲገልጽ ቆይቷል። አሁን ትግሉ በደረሰበት ደረጃ የአመራሩ በትግሉ ሜዳ ውስጥ መገኘት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ሊቀመንበሩን ጨምሮ አመራሩን ወደ ትግሉ ሜዳ አንቀሳቅሷል። በዚህም መሠረት የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግል ሜዳ ወርዷል።
ትግሉ መሯል። ወሳኝ የሆነ ትግል ውስጥ ገብተናል። የትግሉ መሪዎች የሕይወት መስዋዕትነት እሚከፈልበት ቦታ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት የንቅናቄው አመራር በተሟላ ሁኔታ በትግሉ ሜዳ ውስጥ እንዲገኝ ማድረግ ተችሏል። ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ዘረኛው የህወሓት አገዛዝን ከጫንቃችን ለማስወገድ ቆርጠን እንድንነሳ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
ኢትዮጵያን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ የሚያወጣው አርበኞች ግንቦት 7 ብቻ አይደለም። ስለሆነም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚደረገው ትብብር ቀዳሚ ትኩረት ከተሰጣቸው ሥራዎች አንዱ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ለድል እንዲበቃ ይታገላል። ኢትዮጵያዊያንም በያሉበትም በተመሳሳይ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ላይ ክንዳቸውን እንዲያነሱ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
እነሆ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በአካል ትግል ሜዳ ውስጥ ይገኛል። የሚችል ሁሉ እንዲከተል፤ መከተል የማይችል በያለበት ሁኖ ሁለገብ ትግሉን እንዲያጧጥፍ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ


Thursday, July 9, 2015

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ከእስር ተፈታች፡፡

በሽብር ወንጀል ተከሳ የአምስት አመት እስራት ተፈርዶባት የነበረችው ጋዜጠኛ ርዮት የ4 አመት አመክሮ ጊዜዋን አጠናቃ ትናንት ከእስር ተፈታለች፡፡
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በሽብርተኝነት ወንጀል 14 አመት እስራት ተቀጥታ የነበር ሲሆን ባደረገችው የይግባኝ ክርክር ሙያዋን በመጠቀም የሽብርተኛ ቡድንን ረድታለች በሚል ወንጀል ብቻ ቅጣቱ ወደ 5 አመት ሊወርድላት ችሎ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ከእስር ተፈታች፡፡ በሽብር ወንጀል ተከሳ የአምስት አመት እስራት ተፈርዶባት የነበረችው ጋዜጠኛ ርዮት የ4 አመት አመክሮ ጊዜዋን አጠናቃ ትናንት ከእስር ተፈታለች፡፡
DIRETUBE.COM

Sunday, July 5, 2015

በዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት ጦርነቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፥ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44812#sthash.Pf92nKVE.dpuf

የ44ኛውን ክፍለ ጦር በማንቀሳቀስ በወልቃይት ዓካባቢ በሰፈረው የቀደምት ወያኔ ታጋይ ሰራዊት ታጅቦ በመጣ የወያኔ ሰራዊት እና በዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰራዊት መካከል፥ ዳንሻ ዓካባቢ፣ ጓንጓ ሳግላ እና ማይንቧ በሚሉ ሁለት ቦታዎች በትላንትናው ምሽት ከፍተኛና መረር ያለ ውጊያ ተደርጓል፥ ተኩሱ ዓሁንም እንደቀጠለ ነው፥
zemene Kassieዓመጣጣቸው የሰራዊታችንን እንቅስቃሴና የተነሳውን ሕዝባዊ የዓመጽ ማዕበል ለመግታት ታስቦ እንደሆነ ይታያል፥ በዓውደ ውጊያው የወያኔ ነባር ታጋዮችና ከፍተኛ መኮንኖች እንደተገደሉ በስም ዝርዝር ከግንባሩ ደርሶናል፥
የትግል ስልታቻንና ውጊያችን የወቅቱን ሁኔታ ያገናዘበ፥ በሰራዊታችን ቆስቋሽነት ሕዝባዊ ዓመጽ በማቀጣጠል፥ ብሶት ያበሰለውን ሕዝብ ያካተተና በዓካባቢው ሕዝብ የታቀፈ እንጂ ቦታ በመያዝና በማፈግፈግ የሚካሄድ የተራዘመ ጦርነት ዓይደለም፥
ከወያኔ ጋር ትንቅንቁ ይቀጥላል! ከሕዝቡ ከፍተኛ ድጋፍ እያገኘን ነው፥
እኛም እግራችን የረገጠውን መሬትና ያለፍንበትን ሁሉ በሕዝቡ እጅ እያስገባን ሕዝብ ዓብሮን እንዲዋደቅ ማድረግ ነው ዓሰራራችን፥
የዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ቃል ዓቀባይ ታጋይ ዘመነ ካሴ
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44812#sthash.Pf92nKVE.dpuf

Tuesday, June 2, 2015

ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት በገዢው መንግስት እንዲቃጠል ተደረገ

የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ቦንጋ አካባቢ የነበረ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት እንዲቃጠል ማድረጋቸውን የትህዴን ድምጽ ዘገበ::
Zehabesha News
የትህዴን ምንጭ የዜና ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡብ ክልል ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ ሰፊ የተፈጥሮ ጫካ በአካባቢው ህዝብ ለዘመናት ጠብቆት የኖረ ሃብት ሲሆን የገዢውን ስርአት በመቃወም እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ነው ብለው ስጋት ላይ የወደቁት የስርአቱ ካድሬዎች እሳት ለኩሰው እንዲቃጠል ማድረጋቸውና ይህን እኩይ ተግባር የታዘበው የአካካባቢው ህዝብም በስርአቱ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳስነሳ ለማወቅ ተችሏል።
የአካባቢው ህዝብ እየተቃዎመ በነበረበት ሰዓት እንደገለፀው በአፋችሁ ልማት አልሙ፤ ድህነት አጥፉ እያላችሁ በተግባር ግን መተኪያ የሌላቸውን የተፈጥሮ ሃብቶችን እያቃጠላችሁ ነው በማለት ሃይለኛ ተቃውሞ ማንሳታቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለማስታረቅ ሱዳንና ኳታር እቅድ መያዛቸውን ተሰምተዋል

የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑማር ልበሽር የአገሪቱን ምርጫ በማሸነፋቸው በነገው ዕለት የቃለመሃላ ሥነ ሥርዓት ያካሂዳሉ።
በዚህ በዓል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ ፊት
ለፊት ይገናኛሉ።
የሱዳንና የኳታር መሪዎች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከረረ ጥላቻ የሚገኙት ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማስታረቅ ሙከራ
ያደርጋሉ ተብሏል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ጥል በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በምሥራቅ አፍሪካ ሠላም ለማስፈን ማነቆ መሆኑን የተረዱት
መሪዎቹ ችግሩን ለመፍታት በቁርጠኝነት የማስታረቁ ሥራ እንደሚሞክሩት ይጠበቃል።
ፕሬዝደንት አልበሽር በሚያደርጉት የቃለመሃላ ሥነስርዓት ከኤርትራን ኢትዮጵያ በተጨማሪ የኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣
ግብጽ፣ ቻድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያንና የሌሎች አገሮች በርካታ መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የ91 ዓመት ዕድሜ አዛውንት የ ዚምባብዌንፕረዚደንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሮበርት ሙጋቤ በሥነሥርዓቱ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ze Habesha.com

Thursday, May 21, 2015

“በመመካከር ከራሷ ጋር የታረቀች አገር ጥንስስ እኛው ውስጥ እንፍጠር” -አርበኞች ግንቦት 7 - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41535#sthash.KCnABAJ4.dpuf

አርበኞች ግንቦት 7 በመርህ ላይ በተመሠረተ ትብብር ወያኔን በጋራ ታግሎ ማሸነፍ እና በየደረጃው የሚገኝ የመንግሥት ስልጣን ነፃ፣ ፍትሀዊና ተዓማኒን በሆነ የሕዝብ ምርጫ ብቻ የሚያዝበት የፓለቲካ ሥርዓት መገንባት የአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ተልዕኮ ነው። በዚህም መሠረት አርበኞች ግንቦት 7፣ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ከሚገኙት ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ ከጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ እና ከአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ ጋር በመርህ ላይ በተመሠረተ ትብብር በጋራ ለመታገል የሚያስችለውን ስምምነት ላይ እየደረሰ ነው። ይህ የትብብር ጥረት ብዙ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠንካራ ድጋፍ ይሻል። ህወሓትን ከስልጣን የማባረር ኃላፊነት የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ኃላፊነት ነው። ይህ ትልቅ ኃላፊነት በአንድ ወይም በጥቂት ድርጅቶች ላይ መጣል የለበትም። ይህ ትብብር ይህንን የጋራ ኃላፊነትን በጋራ ለመወጣት የተደረገ በዓይነቱ አዲስ የሆነ ተግባራዊ ትብብር ነው። ህወሓት በትግራይ ውስጥ መቶ በመቶ ተቀባይነት ያለው አስመስሎ ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ ቆይቷል። ህወሓት፣ የትግራይና የአማራ ሕዝብ በጠላትነት እንዲተያዩ፤ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጥሎ እንዲያይ የረዥም ግዜ እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው። ይህን እኩይ ሴራ ማክሸፍ የምንችለው በፀረ-ወያኔ ተግባራዊ ትግል በጋራ ስንቆም ነው። ይህ ትብብር ለአገራችን አንድነትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ የሆነው በፀረ ህወሓት አቋሙ የጠነከረ የትግራይ ሕዝብ እንዲኖር ወሳኝ ሚና ይኖረናል ብለን እናምናለን። በአሁኑ ሰዓት የህወሓት አገዛዝ የቆመው ዘረኛ በሆነ መንገድ ባደራጀው ጦር፣ በስለላ ድርጅቱ እና ኃያላን መንግሥታት ለጥቅማቸው ሲሉ በሚያደርጉለት ሁለተናዊ ድጋፍ ነው። እነዚህ ህወሓትን ደግፈው የያዙ ኃይሎች ጠባቸው ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መሆኑን በተግባር የምናሳያቸው ተግባርን መሠረት ያደረገ ጠንካራ ኅብረት ፈጥረን ስንገኝ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነባራዊ ማኅበራዊ ሀቅ ምክንያት ከፓለቲካ አመለካከት ይልቅ በወል ማንነት ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች የሚበዙበት ሆኗል። የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ሁለቱን አመለካከቶች መሠረት አድርገው በተደራጁ ድርጅቶች መካከል ትብብር መፍጠር ወሳኝ ነው። አርበኞች ግንቦት 7፣ ከላይ በአጭሩ በተዘረዘሩት ምክንያቶች እየተፈጠረ ያለው ትብብር የኢትዮጵያን የፓለቲካ መልካምድር ወደተሻለ ሁኔታ ለመቀየር የራሱ አስተዋጽዖ ይኖረዋል የሚል እምነት አለው። በዚህም ምክንያት መጠናቀቅ የሚገባቸው ነገሮች ተጠናቀው ትብብሩ በይፋ እንዲመሠረት የበኩሉን ጥረት ያደርጋል። ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሳቢያ የትብብር አድማሳችን ከዚህም መስፋት አለበት ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። ስለሆነም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለጊዜው የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ ያልገቡ የፓለቲካ ድርጅቶች ወደ ትብብሩ እንዲመጡ፤ ለሀገራችን እና ለሕዝብ በጋራ መሥራት በምንችላቸው ጉዳዮች ላይ እንድመክር ጥሪውን ያስተላልፋል። በመመካከር ህወሓትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ለሁላችን የሚበጅ የተሻለ ሥርዓት በአገራችን ላይ እንዲመሠረት መሠረት መጣል እንችላለን ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። ስለሆነም እንነጋገር፤ ለሁላችን የሚበጀንን መንገድ በጋራ እንፈልግ፤ የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝን በጋራ እንታገል፤ ከራሷ ጋር የታረቀች አገር ጥንስስ እኛው ውስጥ እንፍጠር ይላል። ለውጤታማ ትግል እንተባበር! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41535#sthash.KCnABAJ4.dpuf

Monday, May 11, 2015

ከሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ! የስም ማጥፋት ዘመቻው ከጀመርነው ትግል ፍፁም አያንበረክከንም!

ሰሞኑን በህውሓት/ኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ባሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘመተ ያለውን የስም ማጥፋት ፕሮፓጋንዳ በአትኩሮት ሲከታተለው ቆይቷል፡፡ በዚህም የህዝብ ንብረት የሆኑ ሚዲያዎች፤ ለህዝብ አገልግሎትና በህዝብ ግብር በሚሰበሰብ ገንዘብ የሚተዳደሩ የማህበረሰቡ የአገልግሎት ተቋማት ጭልጥ ብለው የሰማያዊ ፓርቲ ስም በማጉደፍ እና በማብጠልጠል ላይ ተሰማርተው መገኘታቸውን በትዝብት ተመልክተናል፡፡Semayawi party to welcome Andinet members
ሰማያዊ ከተቋቋመ ጀምሮ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ በደሎችን በሀገርም ሆኖ በውጪ ሲፈፀም ዝም ብሎ የመመልከት ትዕግስት ኖሮት አያውቅም፡፡ ይህ በዋነኝነት ፓርቲው የተቋቋመለት መርህ ነው፡፡ በግራዚያኒ ስም ለሚሰራ ሃውልት ተቃውሞ ለማሰማት አስፈላጊውን የህግ መስፈርት አሟልተን ባለበት ሁኔታ በገዢው ፓርቲ ትእዛዝ አባላቶቻችን ተደበደቡ፡፡ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው ኢሰብአዊ በደል ሰቆቃቸውን ለማሰማት በጠራነው ሰልፍ እንደገና በመንግስት ትእዛዝ አባላቶቻችን ላይ ድብደባና እስር ተፈጸመባቸው፡፡ በቅርብ በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በየመን በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን እጅግ ሰቅጣጭ እና በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ብሔራዊ ውርደት ሰማያዊ ፓርቲ አስቆጭቶታል፡፡ በዚህም የተነሣ እነዚህ በደሎች መድረሳቸው ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በንቃት እየተከታተለ መረጃው ለህዝብ እንዲደርስ እያደረገ ጎን ለጎን መንግስት ለወገኖቻችን የድረሱልኝ ጥሪ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ፓርቲያችን ሲያሳስብ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡
ሆኖም ይኸንን ዘግናኝ እና አረመኔያዊ ድርጊት ማውገዛችን እና መቃወማችን ከዛም አልፎ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመ ተግባር መከታተላችን ፓርቲው ሊያስመሰግነው ሲገባ ይልቁንም ገዥው ፓርቲ በተለያዩ የመንግሰት ሚዲያዎች የሰማያዊ ፓርቲ ስም ለማጠልሸት ሲሯሯጡ ማየት ትዝብት ውስጥ የሚጥል ብቻ ሳይሆን በህግም የሚያስጠይቅ ጭምር ነው፡፡ መንግስት ሃላፊነቱን እና ተግባሩን በመመርመር በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ብሔራዊ ውርደት ዳግመኛ እንዳይፈጸም ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ገዢው ፓርቲ ከሃገር ብሄራዊ ጥቅም ይልቅ የድርጅቱ ኢኮኖሚያዊ ትርፍ በልጦበት ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም፡፡
ከዛም አልፎ ተርፎ ዜጎች በሀገራቸው በሚደርስባቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ ተነጋግሮ ለመፍታት ጥረት ማድረግ እየተሳናቸው በየበረሃው ሲሰደዱ የሚደርስባቸው ስቃይ አልበቃ ብሎ አይኤስ አይኤስ በሚባል አሸባሪ ቡድን የደረሰባቸውን ዘግናኝ በደል ሃዘኑ ገና ከልባችን ሳይጠፋ በሃገር ውስጥ በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ ብቻ የሚንቀሳቀስ ሰማያዊ ፓርቲን ከእንደዚህ አይነት ነውረኛ እና ሰይጣናዊ ተግባር ከሚፈጽመው ድርጅት ጋር ህብረት እንዳለን ለማሣየት መሞከሩ እጅግ ጸያፍና ለዜጎቹ ያለውን ንቀት ማሳያ ጭምር ነው፡፡
ሰማያዊ በዜጎቻችን ላይ ከ1ዓመት ከ6 ወር በፊት በሳውዲ አረቢያ እንዲሁም በተለያዩ አገራት አገራቸውን በመንግስት የአስተዳዳር ደካማነት በተፈጠረው ችግር ምክንያት ጥለው በመሰደዳቸው፤ ለተለያየ ችግር እና ብሔራዊ ውርደት የሚዳረጉ ወገኖቻችንን ችግር ለመፍታት ጥሪ ለመንግስት አድርገን የአንድ ሠሞን ጫጫታ ከመሆን አልፎ ለዘለቄታው ችግሩን ለመፍታት ባለመቻሉ ለዳግመኛ ዘግናኝና አረመኔያዊ ስቃይ ዜጎቻችንን መዳረጉ በገሀድ የሚታይ እውነታ ሆኗል፡፡
ስለዚህ መንግስት ሰማያዊን በመውቀስ ፋንታ ለድርጊቱ ቀጥተኛ ተጠያቂ የሆነውን የድርጊቱ ፈፃሚ አይኤስ አይኤስ ተጨባጭ አፀፋዊ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል አቅም እንደሌለው ጭምር አስመስክሯል፡፡ ዜጎች በሀገራቸው የሚደርስባቸው የተለያዩ ችግሮች ምክንያት እንዲሰደዱ የዳረጋቸው የተሣሣተ አመራር የያዘው ህወሓት/ኢህአዴግ መሆኑን ተረድቶ ነገ ከታሪክ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይቻል ሰማያዊ ፓርቲ ያስገነዝባል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በአዋጅ የተሰጠውና ስልጣን ወደጎን በመተው ሰማያዊ ፓርቲ የስራ እንቅስቃሴውን ለመተለም የሚያደርገውን ተግባር በህወሓት/ኢህአዴግ እና በሌሎች የሚደረግበት ጣልቃ ገብነትን በዝምታ ማለፉ ፓርቲያችንን እጅግ ያስቆጣ ነው፡፡ ከምንም በላይ ግን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕጋዊነት እውቅና የሰጠውን ተቋም ህወሓት/ኢህአዴግ እና ደጋፊዎች በአሸባሪነት ሲፈርጁ ምንም ለማለት አለመፈለጉ ሰማያዊ ፓርቲ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለልተኝነቱ ላይ ለሚያነሳው ጥያቄ ዋንኛ ማሳያ ነው፡፡
ሰማያዊ በአገራችን ጠንካራ አማራጭ ፓርቲ እንደሆነ አምነው ከጎኑ የቁሙትን በሙሉ እያመሰገነ፤ ፓርቲው የህዝብ አማራጭነቱን ለማጥፋት በከፍተኛ ጥረት የተሰማራው ህወሓት/ኢህአዴግ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ እያስጠነቀቀ፣ ህወሓት/ኢህአዴግ እየፈፀመበት ያለው የስም ማጥፋት ውንጀላ ሰማያዊ ፓርቲ ከጀመረው ትግል ፈፅሞ እንደማይገታው በፅኑ ያሳውቃል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ