Wednesday, April 23, 2014

ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ ገንዘብ መኖሩን የመንግስት ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አስታወቀ

የፌድራል ዋናኦዲተር ለተወካዮች ምክር ቤት የ2005 በጀት አመት ሪፖርትን ባቀረረበት ወቅት በ77 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ 8 መቶ 87 ሚሊዮን 45 ሺ 264 ብር  ከ60 ሳንቲም ያልተወራረደ ገንዘብ መኖሩን ይፋ አድርጓል።
የገንዘብ አያያዝን በተመለከተ በአምስት መስሪያቤቶች ውስጥ በተደረገ የናሙና ጥናት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ጉድለት መገኘቱም ተገልጿል።
አምና መከላከያን ጨምሮ በተደረገው ምርመራ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ጉድለት መገኘቱ ይታወቃል። አብዛኛው የገንዘብ ጉድለት የተገኘው ከመከላከያ ሚኒስቴር ነው። ይህ የገንዘብ ጉድለት በምን መንገድ እንደተፈታ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

No comments:

Post a Comment