Thursday, November 27, 2014

ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ የገንዘብ ገበያ ለመበደር ድርድር ጀመረች

መንግስት የጀመራቸውን የሃይል፣ የመንገድ፣ የባቡርና የስኳር ፋብሪካዎችን ለመጨረስ የሚያስችለውን ገንዘብ ከአለማቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር የሚያስችለውን ድርድር ከሁለት የአውሮፓ እና ከአንድ የአሜሪካ ባንክ ጋር ጀምሯል። መንግስት ገንዘቡን ለመበደር የሚያስችለውን ቦንድ ለገበያ የሚያቀርብ ሲሆን፣ አለማቀፍ አበዳሪ ተቋማትም የመንግስትን የመክፈል አቅም በማየት ብድሩን ይፈቅዳሉ።
መንግስት ከአለማቀፍ የግል አበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ ለመበደር ወደ አለማቀፍ የካፒታል ገበያ ሲገባ ይህ የመጀመሪያው ነው። ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከመንግስታት እንዲሁም ከአለማቀፉ የገንዘብ ተቋምና ከአለም ባንክ በአነስተኛ ወለድ ብድር ስታገኝ ቆይታለች። ይሁን እንጅ ከእነዚህ ተቋማትም ሆነ ከኤክስፖርት  የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ  አነስተኛ መሆን የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች ለማስፈጸም ባለማስቻሉ መንግስት ከአለማቀፍ የግል አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር በመወሰን ድርድር ጀምሯል።
መንግስት ወደ አለም የገንዘብ ገበያ ለመግባት መወሰኑን ተከትሎ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ይሰጣሉ። በአንድ በኩል መንግስት የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች ለመጨረስ ብድሩ አስፈላጊ መሆኑን የሚከራከሩ ወገኖች ያሉትን ያክል፣ ብድሩ ኢትዮጵያን ልትወጣው በማትችል እዳ ውስጥ ይከታትና የሁላ ሁላ ችግር ያመጣባታል ብለው የሚሰጉም አሉ።
ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ የሆኑት ፕ/ር ሰኢድ ሃሰን፣  ሚንጋ ነጋሽ፣ ተስፋየ ለማና አቡ ግርማ ሞገስ በጋራ ባወጡት ጥናታዊ ጽሁፍ የመንግስት ውሳኔ ችግሮችን ሊያመጣ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የኢትዮጵያ እዳ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ አገሪቱ ወደ ውጭ ልካ ከምታገኘው ገቢ ጋር የማይጣጣም መሆኑ ሊያሳስብ እንደሚገባ የኢኮኖሚ ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።መንግስት የሚወስደውን ገንዘብ ለየትኛው ፕሮጀክት በትክክል ማዋል እንዳለበት እንዲሁም ተጨባጭ የሆነ የፋይናንስ እቅድ ማዘጋጀት እንደሚኖርበት ባለሙያዎች ምክራቸውን ለግሰዋል።
ኢትዮጵያ ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ እዳ እንዳለባት መረጃዎች ያሳያሉ።
 ኢሳት ዜና

የህወሃቱን ፖለቲካ የአዋጁን በጀሮ!

ህወሃት በተፈጥሮው የፖለቲካ ብዙህነት ወይም ብዝሃነትን ማቻቻል የሚባል ነገር አያውቅም። ሌላው ቀርቶ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ የሚነሱ የተለዩ ሃሳቦችን ሁሉ እንደጠላት ሃሳብ ፈርጆ ሰዎችን ደብዛቸውን ማጥፋት የተለመደ የህወሃት አሰራር ነው። ይህን የህወሃት ባህርይ በቅጡ ለመረዳት በቅርቡ የቀድሞው የህወሃት አመራር አባል የነበረው አቶ ገብሩ አስራት የጻፈው መጽሃፍ ጥቂት ገጾች በማየት መረዳት ይቻላል። ተቃዋሚ ፓርቲ ሰላማዊም ሆነ አልሆነ በህወሃት እንደጠላት ነው የሚቆጠረው።
ሰሞኑን ከትግራይ የህዝብና የመንግስት ግንኙነት ቢሮ ከሚባለው መስሪያ ቤት በትግረኛ ተጽፎ ለአባለት በሚስጥር የተሰራጨ ደብዳቤ ማንኛውምንም ተቃዋሚና ከህወሃት ውጭ የሚያስብና ህወሃትን የማይከተል ሁሉ “ፀላኢቲ” ጠላቶች ሲል ይፈርጃል። በዚህ ባለ 5 ገጽ ደብዳቤ ውስጥ እነዚህን “ፀላኢቲ” እንዴት እንደሚያሳድዱ፣ እንዴት እንደሚያዋክቡና እንደሚያጠፉ የሚመክር መመሪያ የሚሰጡ ሃሳቦች ተቀምጠዋል። በደብዳቤው ላይ ከአናቱ ሆነው የሚያስተዳደሩትን ወገናቸውን እንኳን አይለይም። በአጭሩ እኛ እንዳንመርጥ የሚፈልግ፣ የሚቀናቀንና ሌሎች ሰላማዊ ፓርቲወችን የሚመራና የሚደግፍ ሁሉ ፀላኢቲ ነው።
ይህ ለ2007 ዓ.ም የክትትል ስራ የተመደበው የህወሃት ቡድን ስራውን የሚያከናውነው ከታክስ ከፋዩ በሚገኝ የመንግስት ገንዘብ መሆኑ ይታወቃል።
ዘንድሮ የምርጫ አመት መሆኑን ተከትሎ የፀላኢቲ ክትትልና አፈና ከአሁን ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ መሆኑም እየታየ ነው። ጠንካራ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ በየክልሉ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ሁሉ በመታፈንና ወህኒ በመውረድ ላይ ናቸው።
የህወሃት ኢህአዴግ መሪዎች በአለም ዙሪያ ነጻነቴን የሚል የህዝብ ድምጽ በሰሙ ቁጥር የሚሰማቸውን ድንጋጤ የሚቀንሱት ዜጎችን በማፈን፣ በመግደል፣ በማሰቃየትና በማሰር ብቻ ነው።
ለህወሃት ምርጫና መድብለ ፓርቲ መልክን አሳምሮ ተቀባይነት ወደ ምእራባውያን ለልመና ለመውጫ እምጅ ዴሞክራሲያዊ ምርጫና የህዝብ ልእልና የሚባል ነገር ባጠገባቸው እንዲያልፍ ስለሚፈልጉ የሚያደርጉት አለመሆኑን በብዙ መንገዶች አሳይተውናል።
ከህወሃት ውጭ ያልህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አንተ ለወያኔ/ህወሃት ፀላኢቲ ጠላት ነህ። ወገኖቼ ብለህ የምታስብ ሁሉ ይህን የሚስጥር ደብዳቤያቸውን በማየት ብቻ ሳይሆን በተግባር አይተሃልና።
ያለህ ምርጫ እንደአባቶችህ፡-
እልም እንጅ ውሃ አይላመጥም፣
ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም።
ብለህ መነሳይ ይኖርብሃል።
ትእግስት፣ አስተዋይነትና የፍቅር መንገድ መመኘት ከህወሃት ፀላኢቲነት አያላቅቅም። ህወሃትን ማስወገድ በጠላትነት ፈርጆ ሊውጥህ የመጣ ጠላትን ማስወገድ ማለት ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህ በጠላትነት ከፈረጀህ የዘርፎ አደሮች ቡድን እንድትላቀቅ አቅሙን በመገንባት ለወሳኝ ፍልሚያ እተዘጋጀ ነው። መላው ወገናችን ወያኔ የፈጠረልህን የክፍፍልና የልዩነት አጥር እያፈራረስክ አንድነትን አጠንክር። በያለህበት ለነጻነትህ ተነሳ። ኑሮን ለማሸነፍም ሆነ መረጃ በማጣት በወያኔ ስር ተደራጅተህ በሎሌነት እንድታገለግል የተፈረደብህ ወገን ሁሉ ወያኔ ጠላት ብሎ እንደሚቆጥርህ አትዘንጋ። የነፃነታችን ቀን ቅርብ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Wednesday, November 26, 2014

የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በፖስታ የተላከውን የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ደብዳቤ አልቀበልም አለ

ነገረ ኢትዮጵያ
blue partyየአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል 9ኙ ፓርቲዎች ህዳር 21 ለሚያደርጉት የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በፖስታ ቤት የተላከለትን ደብዳቤ አልቀበልም ማለቱን የስብሰባው አስተባባሪ የሆነው የመኢዴፓ ፀሀፊ አቶ ዘመኑ ሞላ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 21/2007 ዓ.ም ለሚያደርጉትና መኢዴፓ ለሚያስተባብረው ስብሰባ ረቡዕ ህዳር 10 የመኢዴፓ አመራሮች ደብዳቤውን ለማስገባት ሄደው የነበር ቢሆንም አቶ ማርቆስ ብዙነህ እና እሳቸውን ተክተው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ፈለቀ ታመዋል በሚል የከንቲባ ጉዳይ የካቢኔዎች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ማሳወቂያ ደብዳቤውን አንቀበልም ማለታቸው ይታወቃል፡፡
በተመሳሳይ ህዳር 12 ወደ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ያቀኑት የትብብሩ አመራሮች ደብዳቤውን የሚቀበላቸው ሲያጡ ጠረጴዛ ላይ ጥለውት የመጡ ሲሆን በፖስታ ቤት በሪኮመንዴ eg156846735et እንደላኩ የትብብሩን ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ለአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በፖስታ የተላከውን ደብዳቤ ቢደርስም አመራሮቹና ሰራተኞቹ ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ፖስታ ቤት ድረስ በመሄድ እንዳረጋገጡ አቶ ዘመኑ ሞላ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ሰራተኞችና አመራሮች ፖስተኛው ደብዳቤው የሚሰጥበትን ቢሮ ሲጠይቅ ለማሳየት ፈቃደና እንዳልሆኑና በስተመጨረሻም ‹‹ተቀባይ የለውም ብለህ መለስ፡፡›› እንደተባሉት አቶ ዘመኑ ሞላ ገልጸዋል፡፡

Monday, November 24, 2014

ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በቁጥር ‘S/2014/727’፣ በ ‘October 13, 20141 የወጣውን ሪፖርት በተመለከታል፤ ከሞረሽ ወገኔ ዐማራ የሲቪክ ድርጅት የተሰጠ መልስ

ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት
Security Council Report One Dag Hammarskjöld Plaza 885 Second Avenue at 48th Street, 21st Floor New York, NY 10017
Telephone: 212-759-9429 Fax: 212-759-4038 Email: contact@securitycouncilreport.org
ኒውዮርክ፤
ከሞረሽ ወገኔ ዐማራ የሲቪክ ድርጅት
ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ 20910
ዩ.ኤስ. አሜሪካ
ጉዳዩ፦ በቁጥር ‘S/2014/727’፣ በ ‘October 13, 20141 የወጣውን ሪፖርት ይመለከታል፤
  1. ሞረሽ ወገኔ ዐማራ የሲቪክ ድርጅት (ሞወዐድ)፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩት ፹፩ (ሰማንያ አንድ) ያህል ነገዶች እና ጎሣዎች (ብሔር/ብሔረሰቦች) መካከል በቁጥሩ ከጠቅላላው የአገሪቱ ሕዝብ ፴፭(ሰላሣ አምሥት) በመቶ ያህሉን ለሚይዘው እና ለሚደርስበት በደል የሚሟገትለት ቋሚ ጠበቃ ለሌለው የዐማራው ነገድ (ብሔር) ድምፅ ለመሆን የተቋቋመ የሲቪክ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ከመስከረም ወር ፪ሺህ፭ ዓም (Sep 2012) ጀምሮ በተባበሩት የአሜሪካ ግዛቶች፣ በሜሪላንድ ግዛት ሕጋዊነት አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ይህን ደብዳቤ ለተከበረው የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ለመጻፍ ያነሣሣንም፣ ከላይ በርዕሰ-ጉዳዩ ሥር በተጠቀሰው መግለጫ በገፅ ፴፩(ሰላሣ አንድ)፣ በአንቀፅ ፸፰(ሰባ ስምንት) የተገለፁት አረፍተነገሮች ፍፁም ከተሳሳተ መረጃ የተነሱ እና መሠረት የሌላቸው በመሆናቸው፣ በዘገባው የቀረቡትን አብዛኞቹን ዝርዝር ጉዳዮች ወደተዛባ አጠቃላይ ድምዳሜ ወስዷል የሚል ዕምነት ስላለን ነው።
  2. በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የትግሬ-ወያኔ (ሕወሓት) አገዛዝ የዐማራን ነገድ በአጠቃላይ በዘር ጠላትን ፈርጆ በመተዳደሪያ መርኃግብሩ ላይ ያሠፈረ ድርጅት ነው (አባሪ ፩ን ይመልከቱ)። ይህ ድርጅት ለ፲፯ (አሥራሰባት) ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ደግሞ በሥልጣን ላይ በቆየባቸው ጊዜያት በዐማራው ሕዝብ ላይ ያደረሰው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት የወንጀል መጠን ሊስተካከለው የሚችለው በ፪ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ ጀርመኖች በአይሁዳውያን ላይ የፈፀሙት ‘Holocaust’ ብቻ ነው። የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ዓለም በምትገኝበት ለሰብአዊነት ትልቅ ከበሬታ በተሰጠበት ዘመን፣ የወያኔ አገዛዝ ዐማራን በደመኛ ጠላትነት ፈርጆ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ሁሉ አቀፍ የጥፋት ዘመቻ በከፈተበትና እያንዳንዱን ተቃዋሚውን «ዐማራ ነው» እያለ በሚያሳድድበት ወቅት፤ ‘ግንቦት7’ ተብሎ የሚጠራው ድርጅት ዋና መሪዎች የዐማራው ሊሂቃን ናቸው ተብሎ በሪፖርቱ በዋናነት መጠቀሱ ነገዱን ለማጥፋት ቆርጦ ለተነሳው አገዛዝ «ድርጊትህ ትክክል ነው፣ ቀጥል ግፋበት» የሚል እንደምታ የሚያስተላልፍ መልዕክት የያዘ ሆኖ ስላገኘነው ድርጊቱ ከማሳሰብ አልፎ አሳዝኖናል።  ……  (ሙሉውን ከዚህ ላይ ያንብቡ, pdf )

የሰንደቅ አላማችን ጠላት ወያኔና ወያኔ ብቻ ነዉ!

ሰንደቅ አላማ ለአንድ አገር ህዝብ የኩራት፤ የአልበገር ባይነት፤ የአንድነትና የታሪክ ተከታታይነት ምልክት ነዉ። ሰንደቅ አላማ በአንድ በኩል የወደፊቱን ብሩህ ተስፋ ክወዲሁ እያሳየን እየዟችሁ የሚለን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በምናብ ወደኋላ እየወሰደን የድልና የመስዋዕትነት ታሪላችንን የሚያስታዉሰን የነጻነት፤ የሠላምና የብሩህ ተስፋ ማህደር ነዉ። የአገራቸን የኢትዮጵያ አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ አላማ ትናንትናና ከትናንት ወዲያ በተስፋፊዎች አለመደፈራችንን ብቻ ሳይሆን ዛሬም ዘረኞች የጫኑብንን የመከራ ቀንበር በቆራጥነት ሰብረን ነገና ከነገ ወዲያ የነፃነት አየር እንድንተነፍስ አስረግጦ የሚነግረን የአንድነታችን፤ የተገጋድሏችንና የድላችን ልዩ ምልክት ነዉ። አንድን ኢትዮጵያዊ ሰንደቅ አላማ ላንተ ምንህ ነዉ ብለን ብንጠይቀዉ ጥያቄዉን ዕድሜህ ስንት ነዉ ተብሎ እንደሚጠየቅ አንድና ሁለት ቃል ብቻ ተናግሮ አይመልስም። ሰንደቅ አላማም በአንድና በሁለት ቃላት ምንነቱ የሚገለጽ ተራ ቃል አይደለም። ኢትዮጵያዉያን ተማሩ አልተማሩ፤ ደሃ ሆኑ ኃብታም ፤ወንጀለኛ ሆኑ ወይም ሠላማዊ ለአገራቸዉ ሰንደቅ አላማ የተለየ ቦታ አላቸዉ። ሰዎች የአገራቸዉን ሰንደቅ አላማ የሚወዱትና ለሰንደቅ አላማዉ በክብር መዉለብለብ የህይወት መስዋዕትነት የሚከፍሉት ስለታዘዙ ወይም ስለ ሰንደቅ አላማዉ ተነግሯቸዉ አይደለም። በእርግጥም የሰንደቅ አላማ ክብርና የአገር ፍቅር ለሰዎች ሰንደቅ አላማዉን አክብሩ፤ አገራችሁን አፍቅሩ እየተባለ የሚነገር ነገር አይደለም። አገርንና ወገንን ማክበርና መዉደድ ሰንደቅ አላማን ከማክበርና ከማፍቀር ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነዉ።የሰንደቅ አላማ ልዪ ክብርና የአገር ፍቅር ሰዎች ተወልደዉ ከሚያድጉበት ማህበረሰብ፤ ከቤተሰብ፤ ከጎረቤትና ከጓደኛ እንደ ምግብና እንደ ዉኃ እየበሉና እየጠጡ የሚያገኙት የሰዉነትና የዜግነት መገለጫ ታላቅ እሴት ነዉ።
ለዚህም ነዉ የማንም አገር ዜጋ አገሩ ዉስጥ ቢኖር ወይም ካገሩ ዉጭ፤ ቢታሰር ባይታሰር፤ ሀብታም ቢሆን ወይም ደሃ፤ የኔ ነዉ የሚለዉን የእናት አገሩን ሰንደቅ አላማ በፍጹም የማይረሳዉ። ከአገራቸዉ ዉጭ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በተለይም ኢትዮጵያዉያን በተለያዩ ምክንያቶች የሚኖሩባቸዉን አገር ዜግነት ቢወስዱ እንኳን ሰንደቅ አላማቸዉን ባዩና ባስታወሱ ቁጥር የሚሰማቸዉ አገራዊ ስሜት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነዉ – እንዲያዉም ከአገራቸዉ ተሰድደዉም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከአገራቸዉ ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሰንደቅ አላማቸዉን ባዩ ቁጥር የአገራቸዉ፤ የወንዛቸዉ ፤ ተወልደዉ ያደጉበት መንደርና የልጅነት ትዝታቸዉ ባአይናቸዉ ላይ እየመጣ ዕንባ በዕንባ ይተናነቃሉ። ሰንደቅ አላማ ለአንድ አገር ህዝብ አንድ ነገር ነዉ፤ ብዙ ነገር ነዉ፤ ሁሉም ነገር ነዉ። ሰንደቅ አላማ ህዝብን ያስተባብራል፤ ያከባብራል፤ ያዋድዳል፤ መስዋዕትነትን፤ ፍቅርንና ብልፅግናን ያመለክታል።
ዛሬ የሰንደቅ አላማችንን ጉዳይ አቢይ የመወያያ አርዕት አድርገን የወሰድነዉ አለምክንያት አይደለም። በአገር ጥላቻቸዉና በስንደቅ አላማ ንቀታቸዉ የሚታወቁት የወያኔ ዘረኞች “የአብዬን ወደ እምዩ” እንዲሉ ሰንደቅ አላማቸዉ ተዋርዶ ከሚያዪ የቁም ሞታቸዉን የሚመር ትን ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች ባንዲራዉን አዋረዱበለዉ መናገራቸዉን ስለማን ነዉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮች ተስማምተዉ የሚያከብሩት አለም አቀፉ የሰንደቅ አላማ አያያዝ ፕሮቶኮል በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሁሉም አገሮች ሰንደቅ አላማ በእኩል ደረጃ መቀመጥና መሰቀል አለበት፤ አንድ ላይ መሰቀልና አንድ ላይ መዉረድ አለበት ይላል። ይህንን ፕሮቶኮል ረስቶና ሰንደቅ አላማችንን ንቆ በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ከሌሎች አገሮች መሪዎች ጋር የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንደ አለባሌ ዕቃ ዘቅዝቆ ይዞ ያዋረደዉ ወያኔዎች “ታላቁ መሪ” ብለዉ የሚጠሩት ነገር ግን የለየለት የአገርና የህዝብ ጠላት የሆነዉ ዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ነዉ። የህወሓትን ባንዲራ በየቦታዉ እየሰቀሉ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ተራ ጨርቅ ነዉ ብለዉ የሸቀጥ መጠቅለያ ያደረጉትም መለስ ዜናዊና ጓደኞቹ ናቸዉ። ዛሬ ደማቅ ሰንደቅ አላማዉን አስመልክቶ በወያኔና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ያለዉ ትልቅ ልዩነት ትክክለኛዉና ህዝብ የኔ ነዉ ብሎ የተቀበለዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የትኛዉ ነዉ የሚለዉ ጥያቄ ላይ ነዉ አንጂ ባንዲራዉን ማክበር አለማክበር ወይም ማዋረድ ላይ አይደለም።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የእናት አገራችንን የኢትዮጵያንና የህዝቦቿን ታሪካዊ ተከታታይነትና ዘለዓለማዊነት አጉልቶ የሚያሳየን ከሁላችንም በላይ የገዘፈ ግዙፍ አርማ ነዉ፤ ይህ ማለት ደግሞ ሰንደቅ አላማችን ያቻትና ብሎ እንደሚያሳየን አገር አንደ ኢትዮጵያ ሙሉ ህልዉና ያለዉ ህያዉ አካል ነዉ ማለት ነዉ። ሰንደቅ አላማችንን የምንወደዉና የምናከብረዉም ህያዉ አገራችንን የሚወክል ህያዉ አካል በመሆኑ ነዉ። መለስ ዜናዊንና ስብሀት ነጋን የመሳሰሉ በጣት የሚቆጠሩ የትዉልድ ጭንጋፎች ለራሳቸዉ አገር ሰንደቅ አላማ ደንታ ላይኖራቸዉ ይችላል። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳለ ግን የህልዉናዉና የአንድንቱ መገለጫ የሆነዉን ሰንደቅ አላማ አይንቅም ወይም አያዋርድም፤ አንድ ህዝብ ባንዲራዉን የማይቀበልና የማያከብር ከሆነ ባንዲራዉ አይወክለዉም ማለት ነዉ፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዛሬ ያለዉ እዉነታም ይሄዉ ነዉ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ባዕድ አካል የለጠፈበትን ባንዲራ የኔ ነዉ ብሎ አልተቀበለዉም ወይም ባንዲራዉ ይወክለኛል ብሎ አያምንም።
ዘርዓይ ደረስ በ1937 ዓም ሮም ዉስጥ የፋሺስት ጣሊያኖችን ጭንቅላት በገዛ አገራቸዉ እንደ ቅጠል እየጨረገደ ከጣለ በኋላ በጣሊያኖች ጥይት ቆስሎ ሲያዝ የተናገዉ የመጨረሻ ቃል ይህ የጣሊያኖች ባንዲራ ይዉረድና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይሰቀል የሚል የጀግንነትና የአገር ፍቅር ቃል ነበር። ጀግናዉ አብዲሳ አጋ በጣሊያን በረሃዎች ጣሊያኖችን እያሳደደ ሲገድል የኢትዮጵያ ባንዲራ ከአጠገቡ አልተለየችም። በቀዳማዊ ኃ/ስላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ተማሪዎች ጧት ወደ ክፍል ከመግባታቸዉ በፊት ተሰልፈዉ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በክብር ይሰቅሉ ነበር፤ ማታም ወደ ቤታቸዉ ከመሄዳቸዉ በፊት ጧት በክብር የሰቀሉትን ባንዲራ በክብር አዉርደዉ ነበር ወደየቤታቸዉ የሚሄዱት። ዛሬ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ጨርቅ ነዉ ብለዉ የተሳደቡና በዚህ ሰንደቅ አላማ ከገበያ የገዙትን ሸቀጥ እየጠቀለሉ አስራ ሰባት አመት የከረሙ ምናምንቴዎች ናቸዉ በሰንደቅ አላማ ክብርና በአገር ፍቅር ታንጾ ያደገዉን ኢትዮጵያዊ ሰንደቅ አላማዉን አዋረደ እያሉ የአዞ እምባ የሚያነቡት።
ሰንደቅ አላማ በዜጎች ልብ ዉስጥ አንደ እሳት የሚቀጣጠል የአገር፤ የህዝብና የዜግነት መገለጫ የሆነ ታላቅ አርማ ነዉ። ይህ አርማ ደግሞ ከእኛነታችንና ከህልዉናችን ጋር የተጣበቀ አርማ ነዉና መንግስት በተለዋወጠ ቁጥር አይለዋወጥም። ዛሬ ወያኔ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የገባዉ የማይታረቅ ቅራኔም የሚመነጨዉ ከዚሁ ከወያኔ ግራ የተጋባ እዉነታ ነዉ። የዚህ ዘመን ትዉልድም ሆነ ለዚህ ዘመን ትዉልድ አገርና ሰንደቅ አላማ አስረክቦ ያለፈዉ የቀድሞዉ ትዉልድ ሰንደቅ አላማዬ ብሎ የሚጠራዉና ወያኔ የኢትዮጵያ ባንዲራ እያለ የሚጠራዉ ነገር የተለያዩ ናቸዉ።
ባለፉት 75 አመታት አራት ኪሎ ቤ/መንግስትን የተቆጣጠሩት ሦስት ኃይሎች ማለትም የቀኃስ፤ የደርግና የወያኔ አገዛዞች ሁሉም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከራሳቸዉ ጋር ለማያያዝ ሞክረዋል። በንጉሡና በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የይሁዳ አንበሳና የወታደራዊዉ መንግስት አርማ ነበረበት፤ ሆኖም እነዚህ ሁለት አርማዎች ያረፈበት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በቤተመንግስትና ንጉሡና ፕሬዚዳንቱ በሚጓዙባቸዉ ኦቶሞቢሎች ላይ እንጂ ሌላ ቦታ አይታዩም ነበር። በመላዉ አገሪቱ በየቀኑ ጧት እየወጣ ማታ ሲመሽ የሚወርደዉና በየግለሰቦች ቤት የሚገኛዉ ሌጣዉ አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀዩ ሰንደቅ አላማ ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብም ሰንደቅ አላማዬ ነዉ ብሎ የሚያምነዉና የሚቀበለዉ ይህንኑ ምንም አይነት ባዕድ አካላ የሌለበትን አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ አላማ ነዉ።
ወያኔዎች ጫካ ዉስጥ ሆነዉ የትጥቅ ትግል በሚያካሄዱበት ወቅት ያነገቡትና ነጻ አወጣን ባሉበት ቦታ ሁሉ የሰቀሉት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ሳይሆን የህወሓትን ባንዲራ ነበር። ከብዙ መረጃዎች እንደተረዳነዉ ወያኔዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አንደ ተራ ጨርቅ ቆጥረዉ ዕቃ መጠቅለያ አድርገዉት ነበር፤ ይህ ደግሞ የለየለት የጥላቻና የንቀት ምልክት ነዉ።
በአርግጥም ዋና ዋናዎቹ የወያኔ መሪዎች እነ ነመለስ ዜናዊና እነ ስብሐት ነጋ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ህዝብ ይጠሉ ስለነበር ለነሱ ትልቁ ቁም ነገር ህወሐትና የዘረኝነት ምልክት የሆነዉ የህወሓት ባንዲራ ነዉ እንጂ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አልነበረም። ይህ ፀረ ህዝብና ፀረ አገር ባህሪያቸዉ ደግሞ ጫካ ዉስጥ ብቻ ተወስኖ የቆየ ባህሪ ሳይሆን አዲስ አበባ ገብተዉ ክህዝብ ጋር ሲቀላቀሉም በግልጽ የታየና ምን ግዜም ሊደበቅ የማይችል ባህሪይ ነዉ። የወያኔዉ ቁንጮ መለስ ዜናዊ እኛ ኢትዮጵያዉያን የምናከብዉንና የምንወደዉን ሰንደቅ አላማ “ጨርቅ” ብሎ መጥራቱ አዲስ የጀመረዉ ነገር ሳይሆን ከጫካ ይዞት የመጣዉ የተለመደ አባባል ነዉ። መለስ ዜናዊ ይህንን ጸያፍ ድፍረቱንና ፀረ ሰንደቅ አላማነቱን ለማረሳሳት የባንዲራ ቀን ብሎ ቢያዉጅም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ልጆቹ፤ አባቶቹ፤ አያቶቹና ቅድም አያቶቹ የተሰዉለት ሰንደቅ አላማ በአለባሌ ሰዉ አንደበት “ጨርቅ” ተብሎ የተጠራበትን ቀን ምን ግዜም አይረሳም።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ የወያኔ ዘረኞች ኢትዮጵያዉያንን በተለይም በዉጭ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ባንዲራቸዉን አያከብሩም ወይም ባንዲራዉን አዋረዱ እያሉ መክስስ ጀምረዋል። በነገራችን ላይ ከወያኔዎችና ከጥቂት ሆዳም ተከታዮቻቸዉ ዉጭ የኢትዮጵያ ህዝብ አገር ዉስጥም በዉጭ አገሮችም በሰንደቅ አላማዉ ላይ ያለዉ አቋም ተመሳሳይ ነዉ። ወያኔ ሰንደቅ አላማዉ ላይ ባዕድ አካል ለጥፎ ከዛሬ ጀምሮ ሰንደቅ አላማችሁ ይህ ነዉ ብሎ አዋጅ ሲያወጣ አዋጁን የሰማለት አንድም ሰዉ አልነበረም። እንዲያዉም ህዘብ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ፤ ሰርግ ሲደግስ፤ ኳስ ጨዋታ ሲሄድና በተለያዪ ቦታዎች ደስታዉንና ኃዘኑን ሲገልጽ አንግቦ የሚወጣዉ የወያኔን ባንዲራ ሳይሆን አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ነበር። ወያኔ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የቀየረዉ በጠመንጃ ሀይል እንደሆነ ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የማይወደዉንና በሀይል የተጫነበትን ባንዲራ ተቀብሎ እንዲኖር ያደረገዉም በጠመንጃ ሀይል ነዉ።
ለመሆኑ እነሱ እራሳቸዉ የለየላቸዉ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ጠላት የሆኑት የወያኔ መሪዎች በዉጭ አገሮች የሚኖሩና አክርረዉ የሚቃወሟቸዉን የኢትዮጵያ ልጆች ባንዲራዉን አዋረዱ እያሉ ተደጋጋሚ ክስ የሚያሰሙት ለምንድነዉ? አንዳንድ ከህልዉናቸዉ ይልቅ ለማይጠረቃዉ ሆዳቸዉ ያደሩ ደካማ ግለሰቦችስ ይህንን የወያኔ መሠረተ ቢስ ክስ እየሰሙ አንደ ገደል ማሚቶ ደግመዉ ደጋግመዉ የሚያስተጋቡት ለምንድነዉ? አገራችን ኢትዮጵያ ሁለት የተለያዩ ባንዲራዎች ሊኖራት እንደማይችል ሁላችንም እናዉቃለን። ለመሆኑ ይህ እኛ ሰንደቅ አላማ እነሱ ባንዲራ እያልን የምንጠራዉ ነገር አንድና ተመሳሳይ ነዉ? ወያኔና በየቦታዉ ያስቀመጣቸዉ የገደል ማሚቶዎች ከሁሉም ነገር አስቀድመዉ መመለስ ያለባቸዉ ይህንን ጥያቄ ነዉ። እኛ ኢትዮጵያዉያን ከህጻንነታችን ጀምሮ የኛ ነዉ እያልን ያሳደገንን፤ የመራንን፤ አቅጣጫ ያሳየንነና በተለይ በልጅነታችን ት/ቤት እያለን ጧት በክብር ሰቅለን ማታ ላይ በክብር እያወርድን በክብር እናስቀምጥ የነበረዉን አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ አላማችንን ማክበርና መዉደድ ብቻ ሳይሆን ለዚህ ሰንደቅ አላማ ዘለዓለማዊነት አንድ ህይወታችንን እንሰጣለን። ሰንደቅ አላማዉን የማያከብር ህዝብ የለም፤ እኛም ኢትዮጵያዉያን ሰንደቅ አላማችንን እንወዳለን፤ እናከብራለንም፤ የምንወደዉና የምናከብረዉ ሰንደቅ አላማ ግን ባዕድ አካል የተለጠፈበትን የወያኔን ባንዲራ ሳይሆን የነፃነታችን፤ የእንድነታችን፤ የሰላማችንና የመዋዕትነታችን ምልክት የሆነዉን አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ነዉ። ይህንን ሰንደቅ አላማ ደግሞ እኛ ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳንሆን ይህንን የጥቁር ህዝብ የነጻነትና የመስዋዕትነት ታሪክ ምልክት የሆነ ደማቅ ሰንደቅ አላማ አያሌ አፍሪካዉያንም ያከብሩታል። ለምሳሌ የስምንት የአፍሪካ አገሮች ባንዲራ አቀማመጡ ይለያያል አንጂ ቀለሙ አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ነዉ፤ ከዚህ በተጨማሪ የሌሎች 23 አፍሪካ አገሮች ባንዲራ ደግሞ ቀዩና አረንጓዴዉ ቀለም አለበት። ይህ ሁሉ የሚያሳየን ሰንደቅ አላማችን የፓን አፍሪካ ባንዲራ እየተባለ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮችም የሚከበርና የብዙ አፍሪካ አገሮች ሰንደቅ አላማ መሰረት መሆኑን ነዉ።
የወያኔ ዘረኞች ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበሩትንና በዉጭ አገሮች የሚገኙ አማራጭ የመረጃ ምንጮች ሁሉ ጥርቅም አድርገዉ ዘግተዉ እንደቤት ዉስጥ ዕቃቸዉ በሚቆጣጠሩት ቴሌቪዥን፤ ሬዲዮና ጋዜጣ “በሬ ወለደ” አይነት ዉሸታቸዉን ጧትና ማታ በተደጋጋሚ አየተናገሩ ለግዜዉም ቢሆን ህዝብን ማደናገር ይችሉ ይሆናል። ሰንደቅ አላማዉን የሚወደዉንና የሚያከብረዉን ኢትዮጵያዊም እነሱን ስለተቃወመ ብቻ ባንዲራዉን አዋረደ እያሉ ህዝብን ሊያታልሉ አንዳንድ ወደ ገባዎችንና ጥቂት የዋሆችን ሊያሳምኑ ይችሉ ይሆናል። ሆኖም የኢትዮጵያን ህዝብ እንወዳለን ፤ ለኢትዮጵያ አንድነት እንቆማለን፤ የዚህ አንድነት ምልክት የሆነዉን ሰንደቅ አላማም እናከብራለን አያሉ ታቦት ተሸክመዉ ቢምሉም የሚያምናቸዉ ቀርቶ ከጉዳይ ቆጥሮ የሚሰማቸዉ አንድም ዜጋ የለም። የወያኔ ዘረኞችና ቡችሎቻቸዉ የሚባቸዉ ቢሆን ኖሮ ዉስጣችን ያለዉን ከፍተኛ የአገር፤ የወገን፤ የባንዲራና የሉዓላዊነት ስሜት ደግመን ደጋግመን እንነግራቸዉ ነበር፡ ሀኖም እነሱን ከማስወገድ ጀምሮ አገራችንን እስከማረጋጋት ድረስ ብዙ አስቸኳይ የሆነ አገራዊ አደራና አገራዊ ስራ ይጠብቀናልና ለዛሬዉ እዚህ ላይ እናብቃ።
Ginbot 7
የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ያሸንፋል!

Sunday, November 23, 2014

አንድነት አሁንም ቀሪ ሒሣብ አለበት !

በ ይድነቃቸው ከበደ  November 22, 2014 

አያገባኽም፣ማን ደረሰብህ፣የራስህን ስራ ሥራ” እና የመሳሰሉ ምክሮች ከትችት ማምለጫ የሞኙ-አሞኝ ቀፋፊ አካሄድ ነው፡፡ሁሉ ነገር በእጄ ነው የሚለው ገዥው የወያኔ መንግሳት ከመተቸት እና ከማጋለጥ ከፍ ሲልም ከስልጣኑ ለማውረድ ሞራል አለኝ የሚል ሰው ፣ማንኛውንም ፓርቲ እና ግለሰብን ለመተቸት እና ለማጋለጥ የሚያፈገፍግ እንደማይሆን እርግጥ ነው፡፡
እኔም ከዚህ የተለየ እምነት የለኝም፡፡ በማልስማማበት እና ቅር በተሰኘሁበት ጉዳይ አስተያየት የመስጠት ልምዴን እያዳበርኩ የምገኝ ፣ለመተቸት እና ለመማር እራሴን የዘጋጀው ነኝ፡፡ ሌላው ቀርቶ እኔ በሃላፊነት ያለሁበት ፓርቲ የተሳሳተ ሃሳብ እና አቋም የያዘ ሲመስለኝ በግሌ ትችት አዘል አስተያየት በጋዜጣ፣በመፅሔት እና በተለያዩ ዌብሳይቶች ላይ በፁሑፍ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካክለ “ወደፊት ቆሞ ወደ ኋላ መመልከት”፣ “ጥያቄው ሃይመኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ ” እና “ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ ”የመሳሰሉት የገኝበታል፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ አንድነት ፓርቲ “በምርጫ እሳተፈላው” በማለት ያወጣው መግለጫ ከሰሞኑ የመነጋገሪ ዕርስ እንደነሆነ ለማናችንም ግልፅ ነው፡፡ ይሄን ተከትሎ “በምርጫ ለመሳተፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ለምን ?” በማለት የግል ዕይታዬ ገልጫለው፡፡ በዚህም ምንያት ትችት እና አስተማሪ የሆነ አስተያየት በፊስቡክ ገፄ እና ሣጥኔ በግል መልዕክት እንዲሁም ባመቻቸው መንገድ የሰጡኝ አስተያየት ደርሶኛል፡፡
ለዚህም አስተያየታችሁ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነውና በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡
እኔም ሆንክ ሌሎቻችን በሰጠነው ትችት እና አስተያየት አንድነት ፓርቲ ጉዳዩን ለማጥረት በዛሬው ዕለት “አንድነት የፀረ ሽብር አዋጁ ተቀብሎትም አያውቅም፤ አይቀበለውም!” በማለት ያዋጣው መግለጨ የሚበረታታ እና የሚደነቅ ነው፡፡ በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ አንደነት የሰጠው ማብራሪያ የሚደግፍ ቢሆንም በምርጫ ላይ ያለው አቋም ግን የፀና መሆኑ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በማህበራዊ-ድረ ገፃቸው እንዲሁም በተለያየ መንገድ አረጋግጠዋል፡፡ይህን አቋማቸው እና የትግል ስልታቸውን አከብራለው ፡፡ የሚያዋጣቸውም ከሆነ ወደፊት በጋራ የምናየው ይሆናል፡፡
አሁን ላይ አስቀድሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ፣ ለዛውም አቋምን ለመግለፅ አስገዳጅ ሁኔታ ባልተፈጠረበት፣ “ምርጫ እሳተፋለው” ማለት ለቀጣይ የትግል ስልት ለፓርቲው(ለአንድነት) የስልጣን ባለቤትነት የሚያበቃው ከሆነ መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት፡፡ለመረጃ ያኸል አንድነት አወጣ የተባለው መግለጫ ሾልኮ የወጣ እንጂ የታሰበበት እንዳልነበር እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆነው “የአንድነት የምርጫ ጉዳይ ግብረ ሃይል” በጉዳዩ ዙሪያ የሚያወቀው ነገር እንደሌለ እና በዚህም ምክንያት በአንድነት ቤት ውጥረት እንደሰፈነ፣በተጨማሪ በአቶ ግርማ ወቅታዊ አቋም ከጥርጣሬ ባለፈ “ጫጫታ” እንዳለ የአንድነት ፓርቲ ወፍ ነግራኛለች፡፡ወፏ ደግሞ ለእኔ ታማኝ ናት፡፡
ሌላው እና ዋናው ጉዳይ አቶ ግርማ በተመለከተ ነው ፡፡ አቶ ግርማ የአንድነት ፓርቲ ም/ት ሊቀመንበር መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ይሁን እንጂ እነደሳቸው አገላለፅ የግሌ ሣይሆን የፓርቲየ አቋም ነው በማላት ስለሚናገሯቸው ነገሮች እና ስለሚፁፏቸው ጹሑፍ መጠነኛ ምልከታዬን ለመግለፅ እወዳለው፡፡አንድነትም ያላወራረደው ቀሪ ሒሣብ ያለበት እዚህ ላይ ነው፡፡ እዴት ለሚለው ይህን እንመልከት፡፡
1ኛ. በድረ-ገፃቸው በ “ፀረ ሽብር ህግ” ተከሰው ቅጣት ከተጣለባቸው ውስጥ ቅጣት የሚገባቸው ተከሳሾች የሉም የሚል ጭፍን ዕየታ የለኝም፡፡ እነዚህ ሰዎች በወንጀል ህጉ ሊቀጡ የሚችሉ እንደሆነ ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡”ማለታቸው ከምን የመነጨ ነው ! በ “ፀረ ሽብር ህግ” ተከሰው ቅጣት የተጣለባቸው እና ቅጣታቸውን የሚጠብቁ 1ኛ.ናትናኤል መኮንን 2ኛ.አበበ ቀስቶ 3ኛ.አንዱአለም አራጌ 4ኛ.እስክንድር ነጋ 5ኛ.ርእዮት ዓለሙ 6ኛ.በቀለ ገርባ በተጨማሪ ሌሎች ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ጦማሪያን፣ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች፡፡ በአቶ ግርማ አገላለፅ እነዚህ ሽብርተኞች በወንጀል ህጉ ሊቀጡ የሚችሉ መሆናቸው መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
2ኛ.ሌላው ደግሞ አቶ ግርማ በድምፅ ከተናገሩት “……ሁሉ ጊዜ ከመንግስት ጋር “እንትን” የምንለው በኢትዮጵያ ሰላም እና ፀጥታ፣ ችግር ይፈጥራሉ ብሎ የሚባል ነገር ካለ እኛም የበለጠ ያጋባንል….” ይቺ ናት ጨዋታ! የት ነበር ይሄን ዘፈን የሰማሁት ? አቶ ግርማ ስለሚናገሩት ነግር ምን ያህል እርግጠኛ ስለሞሆናቸው እጠራጠራለው፣ይሄን ንግግር የተናገሩት ከ“ፀረ ሽብር ህግ” ጋር በተያያዘ ነው፡፡
መንግሰት ደግሞ እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከገዥው መንግሰት የተለየ ሃሳብ ያለውን በሙሉ “የሕዝብን ሰለምና ፀጥታ፣ለማደፍረስ” በሚል የሽብር ክስ የሚመሰርተው እና የሚያስረው እንዲሁም የሚያሰቃየው ፡፡እንደ አቶ ግርማ አገላለፅ ከመንግስት እኩል ፓርቲያቸው እንደሚያስጨንቀው የገለፁት፡፡
ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ “የአ.አ አሰተዳደር ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እርምጃ እወስዳለው” ማለቱ የሚታወቅ ነው፡፡ አስተዳደሩ ይሄን ያለበት ምክንያት ደግሞ ለማንም ግልፅ ነው፡፡ በአቶ ግርማ ቀመር መሠረት ከምንግሰት እኩል ጉዳዩ አግብቷቸው እሳቸው እና ፓርቲያቸው እርምጃ ሊወስድ ነው ማለት ነው ? እንዴን ግምት አቶ ግርማ ሊያደርጉት ይችላሉ፣ፓርቲያቸው ግን ይሄን የሚያደርግ አይመስለኝም ፣ከአይመስለኝም ወደ እርግጠኝነት የሚያሸጋግረኝ፤ አንድነት ፓርቲ በዚህ ላይ ያለውን አቋም ለክ እንደ ፀረ ሽብር አዋጁ በግልፅ ካሳውቅ ነው፡፡ለዚህም ነው “አንድነት አሁንም ቀሪ ሒሣብ አለበት” !ያልኩት፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

Friday, November 21, 2014

መምጫውን የማያውቅ መድረሻውን ያጣል

ታሪክ ለሰው ልጅ ስሩና መሠረቱ ነው።ታሪኩንና መምጫውን የማያውቅ ህዝብ መድርሻውን የማያውቅና ራሱንም ለባርነት አሳልፎ የሰጠ
ይሆናል፡፡ ለክብሩ ለእርሱነቱ ለህብረቱና ለነፃነቱ ፀንቶ መቆየት እና የጥንካሬውና ተሳስሮ የመዝለቂያው ሰንሰለት ታሪኩ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የአሜሪካ ባርያ ፈንጋዮች ትናንት በገፍ ከአፍሪካ በባርነት ያመጡዋቸው አፍሪካውያን አንድ ቀን በአንድ ቆመውና በህብረታቸው ጠንክረው ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት እንዳይነሱ ሀ ብለው የነጠቋቸው ማንነታቸውን፤ ታሪካቸውንና መገኛቸውን ነበር፡፡ እንደ እቅዳቸውም እነሆ ዛሬ አብዛኛው ጥቁር አሜሪካዊ እኔ ማን ነኝ? መምጫዬስ ከወደየት ነው? በሚሉና በመሳሰሉ ጥያቄዎች ተተብትቦ ለምላሹ ሲውተረተር መገኘቱ፤ እንዲሁም ዛሬም ከተገዢነት መንፈስ ራሱን አላቆ በሁለት እግሩ ለመቆም ሲታትር ይገኛል፡፡
ሌላው የኢጣልያ ወራሪን ሀይል ቅስም የሰበረውና በአለም አቀፍ ደረጃ ቅሌት ያከናነበው የአድዋ ጦርነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ቅሌት በደም አጥቦ ሀያልነቱን ለአለም ለማሳየት በሞከረበት ሁለተኛው ወረራ ወቅት ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ የአድዋ ጦርነት የመሩት የአፄ ሚንሊክ ሀውልትን ከጥልቅ ጉድጓድ መቅበር እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ባጠቃላይ አንድ ህዝብ እንደ ህዝብና ሀገር ጠንክሮና በነፃነት ኮርቶ ለመኖር ብሎም ከትውልድ ትውልድ መሸጋገር መቻል ከማረጋገጫው አንዱ የትናንት ማንነቱና የመገኛ ታሪኩ መሆኑን ከላይ በምሳሌነት ያነሳናቸው ነጥቦች ያረጋግጣሉ፡፡
ታሪክ ለአንድ ህዝብ የማንነቱ መገኛ፤ የመገኛው ምንጩና መምጫውን የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን የነገ መዳረሻውን የመመልከቻ መነፅርና ጠንክሮ የመንቀሳቀሻው ጉልበቱ ሆኖ የሚያገለግል ትልቅ መሳሪያ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አንድ ህዝብ ታሪኩ ከጠፋ ሊገጥመው የሚችለው ችግርና ፈተና እንዲህ በቀላሉ የሚገመት ያለመሆኑንና እንደ ህዝብ እንደ ሀገር ቀጣይነቱን በቀላሉ መፍትሄ ከማይገኝለት ፈተና ውስጥ ይከተዋል ማለት ነው፡፡
ኢትዮጵያችን ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ህልውናዋ አደጋ ላይ የወደቀበት መሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ባለፉት 23 አመታት በዘረኞቹ የወያኔ ጉጅሌዎች እጅ ከወደቀችበት እለት ጀምሮ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆኑ የታሪካችንና የባህልችን ዋና ዋና እሴቶች ዋነኛ ኢላማ ሆነዋል፡፡ ይህንንም በተደጋጋሚና በግልፅ ከወያኔው መሪ እስከ ተራ ደጋፊው የሚወረወረው በትር ያረጋግጣል፡፡ ጉጅሌዎቹ የነፃነት ምልክት የሆነውንና በዕልፍ አዕላፋት ደም መሥዋዕትነት ፀንቶ የቆየውን ሰንደቅ ዓላማ በሶ መጠቅለያ ጨርቅ ከማድረግ ጀምረው ዛሬ በምሁራን ጥረትና በእያንዳንዱ ዜጋ ድጋፍ የተሰባሰቡት የታሪኮቻችን መዛግብት በጥንቃቄ ከተቀመጡበት (ቤተ-መዛግብት) እያወጡ ከማውደምና ለስኳር መጠቅለያነት እስከ መሸጥ ደርሰዋል፡፡
ታሪካዊ ገዳማት ፈርሰዋል፤ ታሪካዊ ቅርሶች ለባእዳን አልፈው ተሽጠዋል፤ የነፃነት ታሪካችን እየተደለዘ በወያኔያዊ ዘረኛ የፈጠራ ታሪክ መተካቱ ቀጥሏል፤ ታሪካዊ ጀግኖቻችንን ማዋረድና ማውገዝ የእለት ተእለት ስራቸው ሁኗል። ወ ያኔዎች ኢትዮጵያዊነት ቅዝት ሆኖባቸዋል፤ ስለዚህም ቀንደኛ ጠላታቸው አድርገው ፈርጀውታል፡፡ ይህ የዘረኝነትና የዘረፋ ስርዓታቸው ውሎ ማደር የሚረጋገጠው ኢትዮጵያዊነት መመታት ሲችል ብቻ ነው ብለውም በፅኑ ያምናሉ፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊነታችንን ሊያዳክም ብሎም ሊያጠፋ ይችላል ብለው የገመቱትን ሁሉ ከመፈፀም የማይመለሱት፡፡ ለዚህም ነው በስንት ጥረትና በብዙዎች ድካም ተሰባስቦና ተደራጅቶ የቆየውን የታሪክ መዛግብትና መፅሀፍት ከቤተ-መዘክር አውጥቶ በኪሎ ለመቸብቸብ የበቁት፡፡
ታዲያ ኢትዮጵዊ ነን የምንል ሁሉ ዘሬም እንደትናንቱ ይህን በማንነታችን ላይ የሚደረግ የጥፋት ዘመቻ ለማስቆም መነሳት ግድ ይለናል። እየተፈፀመ ያለው የታሪክ ማጥፋት ዘመቻ ለነፃነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ከምናደርገው ትግል እኩል ጎን ለጎን ለታሪካዊ ቅርሶቻችንና መዛግብቶቻችን ከጥፋት የመከላከልና የማዳን ስራ የመስራት የትውልድ ኃላፊነት አለብን፡፡ አለበለዚያ መምጫውን የማያውቅ መድረሻውን አያውቅምና የምናደርገው የነፃነት ትግል የተሟላ ውጤት ማስገኘቱ ጥያቄ ውስጥ መግባቱ አይቀሬ መሆኑን መገንዘብ ይገባናል፡፡ ተገንዝበንም ወያኔን በቃህ ልንለው ይገባል፡፡
በመጨረሻም ጂኦርጅ ኦርዌል ‘The most effective way to destroy people is to deny and obliterate their understanding of their own history” ብሎ ጽፎ ነበር። ህወሃቶች የዚህ ፍልስፍና ተከታዮች መሆንን በመምረጥ ለራሳቸው ውረደትን ፤ለአገራቸውም ውደቀትን ተመኝተዋል። ኢትዮጵያችን መንግስት በጠላትነት ተሰልፎ ከአገራችን ከህዝብና ለአገሪቷ እሴቶች ጋር የሚዋጋበት አገር ሁናለች። ህወሃት በብዙ መልኩ ሲታይ የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት መሆንን የመረጠ ቡድን ነው። የህወሃት በኢትዮጵያ ላይ በጠላትነት መቆሙ ያስቆጣቸው ወጣቶች እምቢ ለአገሬ፤ እምቢ ለክብሬ ብለው ተነስተው ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት ተሠማርተዋል።ግዜው ከእነዚህ ወጣቶች ጎን የምንቆምበትም ጭምር ነውና ተነሱና ለነፃነታችንና ለአገራችን ዝና ለህዝባችን ክብር አብረን ታግለን ጠላትን የመረጠውን ህወሃትን እናስወግድ እና ንፁህ አገር እንፍጠር።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ከ400 በላይ ህዝብ የተፈናቀለበት መሬት በሙስና ተቸበቸበ

በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 11 በተለምዶ ጋሪሳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 470 ሰዎች ቦታው ለኢንቨስትመንት ይፈለጋል ተብሎ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲፈናቀሉ ከተደረገ በሁዋላ፣ በካሬ ሜትር 1 ብር ከ46 ሳንቲም መሬታቸው እንዲጨጥ ተደርጓል።
ጉዳዩ የህዝብ መነጋገሪያ ሆኖ ከቆየ በሁዋላ ሰሞኑን ከህዝቡ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ በተደረገ ህዝባዊና የካቢኔ አባላት ስብሰባ፣ የወረዳው አዛዦች ከተፈናቃዩ ደሃ ህዝብ የወሰዱትን መሬት በሙስና መቸብቸባቸውን እርስ በርስ እየተገላለጡ ይፋ አድርገዋል።
የወረዳው ላይዘን ኦፊሰር አቶ ሃብቶም የተባሉ ግለሰብ፣ አስተዳዳሪውን አቶ አበራ አበረን በአዲስ አበባና በባህርዳር መሬት ገዝተው ቤት መስራታቸውንና ቡልዶዘሮችን ገዝተው እያከራዩ መሆኑን ሲያጋልጡ፣ ምክትል ከንቲባው ደግሞ በባንክ ሂሳባቸው 8 ሚሊዮን ብር እንደተገኘባቸውና  በተለያዩ አካባቢዎች ቤቶችን
መገንባታቸውን አጋልጠዋል። አጋላጩ አቶ ሀብቶምም እራሳቻው በከተማዋ ሁለት ቦታ ገዝተው ቤት መስራታቸውና መቀሌ ላይ ተጨማሪ ቦታ መግዛታቸው በሌሎች ባልደረቦቻቸው ተጋልጧል።
ሶስቱም ባለስልጣኖች ለጊዜው ከስራቸው ቢታገዱም እስካሁን የተወሰደባቸው እርምጃ የለም። አንዳንድ ተፈናቃይ አርሶደአሮች  አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ በማጣታቸው ለስደትና ለረሃብ መዳረጋቸውን ለኢሳት ገልጸዋል ። ሰዎቹ ከስራ ቢሰናበቱም ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረው መስራታቸው አይቀርም የሚል  ጥርጣሬ እንዳላቸውም አክለዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ ከ100 በላይ አርሶደሮች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። አርሶ አደሮቹ የመሬት ዋስትና ወረቀት እንዲሰጣችሁ በነፍስ ወከፍ 4 ሺ 500 ብር ክፈሉ ተብለው የተጠየቁ ቢሆንም፣ እነርሱ ግን እስከዛሬ ግብር እየከፈልን ኖረናል፣ አሁን ተጨማሪ አንከፍልም በማለት ተቃውመዋል። ይህ ተከትሎ መሬታቸውን እየተቀሙ ይዞታቸው ለኢንቨስተር በሚል ሽፋን እየተቸበቸበ ነው። አብዛኞቹ ባለስልጣኖች ከኢንቨስተሮች ጋር አክሲዎን እንዳላቸው የገለጹት መንጮች በአካባቢው የሚታየው ተደጋጋሚ ግጭት ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን  ይናገራሉ።
ኢሳት ዜና

Thursday, November 20, 2014

በዲላ የአንድ የቤተሰብ አባላት ባልታወቀ ሁኔታ መሞታቸው ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጠረ

ማክሰኞ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ኮቸሬ ከሚባል አካባቢ የመጡ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 4 ሰዎች ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ፣ በሆስፒታሉ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። ድንጋጤው የተፈጠረው ሰዎቹ በኢቦላ በሽታ ተይዘዋል በሚል እምነት ነው።  ዛሬ ረቡዕ ደግሞ 4ቱም ሰዎች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ባለስልጣናት ሰዎቹ በኢቦላ ሳይሆን በምግብ መመረዝ መሞታቸውን በመግለጽ የሆስፒታሉ ሰራተኞች እንዲረጋጉ መክረዋል።
ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የሆስፒታሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር በተደጋጋሚ ቢሞክርም አልተሳካለትም። መንግስት የኢቦላ በሽታ በአገሪቱ አለመታየቱን በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወቃል።
ኢሳት ዜና

Tuesday, November 18, 2014

ሁሉም የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው በምርጫው ለኢህአዴግ በሚያዘጋጁት የድጋፍ ሃይል መጠን ነው ተባለ

ትምህርት ሚኒስቴር ” የከፍተኛ ትምህርት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጃት ማንዋል፣ ለምርጫ 2007 የተሻሻለ” በሚል ርእስ ያዘጋጀውና ለኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የቀረበው ሰነድ እንደሚለው በአገሪቱ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው በምርጫው ለኢህአዴግ በሚያዘጋጁት የተማሪዎች የድጋፍ ሃይል መጠን ነው።
ሰነዱ የትምህርት ልማት ሰራዊትን በዩኒቨርስቲዎች ለማስፋፋት የተደረገው ስራ ብዙም ውጤት እንዳላስገኘ ጠቅሶ፣ ለዚህም ዋናው ምክንያት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በአደረጃጃቱ ላይ አመኔታ  በመጣታቸው ነው ብሎአል። የትምህርት ልማት ሰራዊትን ማደራጀት የፖለቲካ እንጅ የቴክኒክ ጉዳይ ባለመሆኑ ፣ በትምህርት ልማት የሚታቀፉ መሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች የትምህርት ሴክተሩን እቅድ መተግበር ብቻ ሳይሆን፣ በፖለቲካ ስእብናቸው የተገነቡና  ኢህአዴግን የሚቀበሉ ተማሪዎች አድርጎ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ሲል ሰነዱ ያመለክታል።
ማንዋሉ የትምህርት ልማት ሰራዊቱ 3 ክንፎች እንዳሉት ይጠቅሳል። ለምርጫ 2007 ዓም የምርጫ አሸናፊነት የሚያዘጋጁ ሁለቱ ክንፎች ማለትም የመንግስትና የህዝብ ክንፎች የሚባሉት ብቻ እንዲዳሰሱ መደረጉን ሰነዱ አመልክቶ፣ የልማት ሰራዊቱ እንቅስቃሴ ከፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ ተያይዞ ከጫፍ ጫፍ የሚንቀሳቀስ ሃይል እንደሚሆን ገልጿል።
ሰነዱ ” በተለይም በአሁኑ ሰአት ፈተና ላይ የጣለን የምርጫ ጉዳይ እንደምናሸንፍ ቃል የተያዘበት ቢሆንም፣ ፈተናዎች የሚፈጠሩት በህዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግስት ክንፍ በሚባሉት መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች አይቀለበስም ብሎ ማሰብ ስለማይቻል፣ በዚህም ቀድሞ መዘጋጀት ያለበትና  ለሁከት እና ለብጥብጥ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው የህዝብ ክንፍ የሚባለው  የተማረው ሃይል ሊሆን ስለሚችል ሊታሰብበት ይገባል ብሎአል።
ተማሪዎች በኢህአዴግ ላይ ያላቸው አቋም የወረደ መሆኑን ሰነዱ ይገልጻል። በማንኛውም ታቃውሞ ላይ በመገኘት ሰልፍ በማድመቅና ተቃውሞውን ከግብ ለማድረስ ተማሪዎች ሁነኛ መሳሪያ ናቸው የሚለው ሰነዱ፣ በየትኛውም ሀገር እንደታየው አደባባይን የመያዝ ህዝብን አስተባብረው ለተቃውሞ የማሳደም እድላቸው የሰፋ ብቻ ሳይሆን፣ ከዚህም አልፎ የኢህአዴግን የምከታ እርምጃ በመቃወም ለጠላት ጎራ ተሰልፈው የመታጠቅ እድላቸው ከፍተኛ ነው ብለአል።
 ኢሳት ዜና

Friday, November 14, 2014

ጊዜው የሕዝባዊ እምቢተኝነት ነው!!!

በአሁኑ ወቅት በአገራችን በከተሞችና በገጠሮች እየታዩ ያሉ ምልክቶችን በጥንቃቄ የመረመረ ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን መታዘቡ አይቀርም።
በአንድ በኩል፣ ወያኔ የተወገደባት፣ ፍትህ የሰፈነባትና የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን ሆና የማየት ተስፋችን እየለመለመ ነው። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለረጂም ዓመታት በሕዝብ ላይ ሰፍኖ የነበረው የፍርሀት ደመና እየገለጠ በመሆኑ ተዘግተው የቆዩ አንደበቶች መናገርና “ይኸ ሁሉ ግፍ ለምን?” ብለው መጠየቅ ጀምረዋል። ይህንን መነቃቃት በአስተሳሰብም፣ በተግባርም፣ በኪነጥበብም እያየነው ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ለውጥ በአገራችን ሊመጣ እንደሚችል ከማመን አልፎ ራሳቸውን በለውጥ አምጭ ኃይልነት መመልከት ጀምረዋል። በርካታ ወጣቶች ወያኔን በትጥቅ ለመገዳደር የወሰኑ ወገኖቻችንን እየተቀላቀሉ በዚህም ምክንያት ጉልበታቸውን እያፈረጠሙ ነው። የለውጡ እርሾ ከሲቪሉ አልፎ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በኢሕአዴግ ድርጅቶች ውስጥም እየተብሰለሰለ ነው። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት፣ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚጠቀምበት ኃይል መሆኑ እያበቃ በአንፃሩ የትግሉ አጋር የሚሆንባቸው ሁኔታዎች እየታዩ ነው። በሁሉም የሠራዊቱ ክፍሎች ጉምጉምታው ወደ ጩኸት እየተቀየረ በመሆኑ ሠራዊቱ በአለቆቹ ላይ የሚነሳበት ጊዜ እሩቅ አይደለም። በተለያዩ ምክንያቶች ህወሓትን ወይም ህወሓት የፈጠራቸውን ድርጅቶች የተጠጉ በአጠቃላይ ኢሕአዴግ በሚባለው ስብስብ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንም “ለመሆኑ ማንን ነው እያገለገልን ያለነው?” ብለው በመጠየቅ ላይ ናቸው። በዚህም ምክንያት ወያኔ ውስጡ እየተረበሸ ነው። ከኢትዮጵያም ውጭ በሚገኘው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ያለው ቁጣና ዝግጁነት ከወትሮው እጅግ የላቀ ነው። በአጭሩ፣ በሁሉም አቅጣጫ፣ ደረጃ በደረጃ የሕዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።
በአንፃሩ ደግሞ፣ የጨለማ ንጉሥ የሆነው ወያኔ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን ወደ ፍርሀት ቆፈን ለመመለስ እስሩን ከመቸውም በላይ ያጧጧፈበት ጊዜ ነው። በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር በሶማሊ … በመላው ኢትዮጵያ ብሩህ ራዕይ የሰነቁ ወጣቶችና አዛውንት ታድነው እየታሰሩ ናቸው። የወያኔ እስር ቤቶች በአርቆ አስተዋይ ዜጎቻችን ተሞልተዋል። ወትሮም ከፍተኛ የነበረው ስደት ብሶበታል፤ ለእውነት በጽናት የቆሙ ጋዜጠኞች ወይ ታስረው፣ አልያም ተሰደው አልቀዋል። የወያኔ የግዴታ ስልጠና አገሩን እያመሰው ነው። የኢትዮጵያዊያን ኑሮ በእጦቶች የታጀበ ሆኗል። የነፃነት እጦት፣ የፍትህ እጦት፣ የመብራት እጦት፣ የስኳር እጦት፣ የዘይት እጦት፣ የታክሲ እጦት፣ የመኖሪያ ቤት እጦት፣ እጦት፣ …. እጦት።
እነዚህ ሁለት ተፃራሪ እውነታዎች ሁለት ተፃራሪ ኃይሎች ለወሳኝ ፍልሚያ ፊት ለፊት መፋጠጣቸዉን በግልጽ ያሳያሉ። ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃነትና ባርነት፣ ፍትህና ጭቆና፣ ደስታና ሀዘን፣ ተስፋና ተስፋ መቁረጥ፣ ብልጽግናና ድህነት፣ እውቀትና ድንቁርና፣ ብርሃንና ጨለማ፣ ለወሳኝ ግጥሚያ ተፋጠዋል። ይህ ፍጥጫ የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታን በመወሰን ረገድ አቢይ ሚና የሚኖረው ወሳኙ ግጥሚያ – ሕዝባዊ እምቢተኝነት – መጀመሩን አብሳሪ ነው። የነፃነት፣ የፍትህ፣ የተስፋ፣ የብልጽግና፣ የእውቀትና የብርሃን ወገኖች ነን የምንል ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ይህንን ፍልሚያ በድል መወጣት ግዴታችን ነው።
ወያኔ ታጋዮችን ቢያስር ትግሉን አያስርም። በእጦት ኑሮዓችን በማመሰቃቀል በድህነት ሊያንበረክከን ቢሻም፣ በፍጹም አንበረከክለትም። በተዘረፈ የድሆች ድካም ህንፃዎችን ቢገነቡም የራስ ባልሆነ ጌጥ አንኮራም። የወያኔ የሆነ የኛ አይደለም፤ የእነሱ መክበር የኛ መክበር አይደለም። ወያኔ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ገዢና ተገዢ፤ በዳይና ተበዳይ፣ ገፊና ተገፊ ናቸው።
ተበዳይና ተገፊ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘረኞች፣ ሙሰኞችና ከፋፋዮች የህወሓት ባለሥልጣኖቻቸውና ሎሌዎቻቸው ላይ ይነሳሉ። የተጀመረው ሕዝባዊ እምቢተኝነት አመቺ በሆኑ መንገዶች ሁሉ ይጧጧፋል።
የወያኔ ትዕዛዛትን መሻር፤ በሥራ ላይ መለገም፤ ግብር አለመክፈል፤ አድማ መምታት፤ የወያኔ ካድሬዎችን ማግለልና ማዋረድ፤ የነፃነት ኃይሎችን መደገፍ፤ የፓሊስና የጦር ሠራዊት አባላትን ማቅረብ እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እነሱም የትግሉ አካል እንዲሆኑ ማበረታታት፤ ህሊና ያላቸው የኢሕአዴግ አባላት የሕዝቡን ትግል እንዲያግዙ ማበረታታት … – እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ በርካታ የትግል ስልቶች ከአሁን ጀምሮ በተከታታይ በሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል። የወያኔን የጭቆና ምሽግ ከውስጥ መሸርሸር፤ ከውጭ መደርመስ ይኖርበታል። የመሸርሸርና የመደርመስ ሥራዎች ተደጋግፈው እንዲሄዱ ማድረግ ይገባል። ጊዜው የእምቢተኝነት ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የነፃነት ንቅናቄ የኢትዮጵያ ሕዝብ አጠገቡ ባሉት መሪዎቹ አስተባባሪነት በአንድነት እንዲነሳ ጥሪ ያቀርባል፤ በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው ሁለገብ ትግል በጽናት እንዲደግፉ ያሳስባል። ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው፤ እንወጣዋለንም!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ የአሜሪካ ኮንግረስ የውይይት መድረክ አዘጋጀ

 አለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብቶች የተባለው ድርጅት ለኢሳት በላከው መግለጫ የቶም ላንሶቶስ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ታዋቂ ሰዎች ሃሳባቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዟል።
ተናጋሪዎቹ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ በመገምገም የአሜሪካ መንግስት የዲፕሎማቲክና የገንዘብ ድጋፉን ተጠቅሞ በኢትዮጵያ የሚታየው የተበላሸ የሰብአዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻል ግፊት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል መግለጫው አመልክቷል።
ዝግጀቱ አርብ ኖቬምበር 14፣ 2014 ከሰአት 1፡ 30 ፒኤም ላይ ይካሄዳል።
ኢሳት ዜና