Thursday, November 20, 2014

በዲላ የአንድ የቤተሰብ አባላት ባልታወቀ ሁኔታ መሞታቸው ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጠረ

ማክሰኞ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ኮቸሬ ከሚባል አካባቢ የመጡ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 4 ሰዎች ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ፣ በሆስፒታሉ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። ድንጋጤው የተፈጠረው ሰዎቹ በኢቦላ በሽታ ተይዘዋል በሚል እምነት ነው።  ዛሬ ረቡዕ ደግሞ 4ቱም ሰዎች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ባለስልጣናት ሰዎቹ በኢቦላ ሳይሆን በምግብ መመረዝ መሞታቸውን በመግለጽ የሆስፒታሉ ሰራተኞች እንዲረጋጉ መክረዋል።
ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የሆስፒታሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር በተደጋጋሚ ቢሞክርም አልተሳካለትም። መንግስት የኢቦላ በሽታ በአገሪቱ አለመታየቱን በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወቃል።
ኢሳት ዜና

No comments:

Post a Comment