Wednesday, April 22, 2015

በአዲስ አበባ አንድ ኢትዮጵያዊ ራሱን አቃጠለ

ሚያዝያ ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሚያዚያ 12 ፣ 2007ዓም ኡራኤል አካባቢ አንድ ኢትዮጵያዊ ቤንዚን በራሱ ላይ አርከፍክፎ የተወሰነ የሰውነት ክፍሉ ከተቃጠለ በሁዋላ በህዝብና በፖሊስ እርዳታ ሊተርፍ ችሎአል።
የአይን እማኞች ግለሰቡ ሙሉ ልብስ የለበሰ እና ጥሩ የሰውነት ቁመና  ያለው መሆኑን ተናግረዋል።  ፖሊሶችም ግለሰቡን ወደ ስድሰተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውታል
ዘግይቶ በመጣው መረጃ ደግሞ ግለሰቡ የመንግስት ሰራተኛና ከስራ ከወጣ በሁዋላ ድርጊቱን መፈጸሙ ታውቋል።

Tuesday, April 21, 2015

“[ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ ስለተሰውት ሰማዕታት ያወጣው መግለጫ] የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት
የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው ነው የዜግነት ጉዳይ ያሳሰባት? ምንም ኢትዮጵያዊነታቸው የማያጠራጥር ቢሆንም፣ ጠላታቸው እንኳን የመሰከረላቸው ቢሆንም፣ ዓለም ያወቃቸው ቢሆንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ግን ሱዳኖችም ሆኑ ሩዋንዳዎች፣ ሶማልያዎችም ሆኑ ጅቡቲዎች የተሠውትኮ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን የሰማዕትነት ክብሩ የሞተለት ክርስቲያናዊ ምክንያት ነው፡፡ የሞቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ በቃ፡፡
daniel
ደግሞስ ‹የዜግነትና የማንነት መረጃውን በተመለከተ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው› የሚሉን ማነው ጥረት እያደረገ ያለው? መንግሥት ነው ካላችሁ ‹መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው› በሉ እናንተም ጥረት እያደረጋችሁ ከሆነ ንገሩን፡፡ ቤተሰቦቻቸውኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፡፡ ለምን ለየሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመስጠት ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ከበዳችሁ? እረኛ በጎቹን በሪሞት ይጠብቃል እንዴ?
እጅግ ያስገረመኝና ያሳዘነኝ ነገር ደግሞ ክርስቲያን በመሆናቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉ ወንድሞች ከቤተ ክርስቲያን የምጠብቀውን ሦስት ነገር ከመግለጫው ማጣቴ ነው፡፡ የመጀመሪያው የመታሰቢያ ጸሎት ሊደረግ ይገባው ነበር፡፡ በምንም ለማናውቃቸውና ለማያውቁን የኢንዶኔዥያ ዜጎች ሱናሚ መታቸው ብለን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ያደረግን ሰዎች ለሚያውቁንና ለምናውቃቸው ክርስቲያን ወገኖች ጸሎት ለማድረግ ለምን እንደከበደን እንጃ፡፡ ለመሆኑ ከአንድ አባት ከጸሎት በላይ ምን ሊገኝ ይገባ ነበር?
‹ማንነታቸው ተረድተን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት አስፈላጊውን እናድርጋለን› ይላል መግለጫው፡፡ ለመሆኑ ከክርስትና በላይ ምን ማንነት አለ? የብሔር፣ የብሔረሰብ ማንነት ነው የምታጣሩት? ከዚያ ይልቅ ሁኔታውን የሚከታተል፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኝና ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊም ቀኖናዊም ተግባር ነገሮችን የሚያመቻች ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋማል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ምነው በአንድ አጥቢያ ገንዘብ ተወሰደ ሲባል ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋም የለምን?
ሦስተኛው ያሳዘነኝ ነገር ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ የሚደርሰውን ኀዘን የምትገልጥበት ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሥነ ሥርዓት የሌላት ይመስል ኀዘንን በሴኩላር መንገድ ስትገልጥ ማየቴ ነው፡፡ እኔ የጠበቅኩት ለአንዳንድ ክርስቲያን ላልሆኑ ‹ታላላቅ ሰዎች› ቀብር እንኳን የሚከፈተው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከፍቶ፣ ለቢዮንሴ እንኳን ያልተነፈጋት ማኅሌት ተቁሞ፣ በፓትርያርኩ የሚመራ ጳጳሳቱ የሚገኙበት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተደርጎ፣ መግለጫው በጸሎቱ ፍጻሜ ይሰጣል ብዬ ነበር፡፡ የመግለጫው አሰጣጥ ግን የዕለት ተዕለት ተግባርን በተመለከተ የሚሰጥ ሳምንታዊ መግለጫ ነበር የሚመስለው፡፡ ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስ አይሸትም፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት እንኳን የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ሊያውጅ መሆኑን ሲገልጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን የጸሎት ሳምንት አለማወጇ የታሪክ ትዝብት ውስጥ የሚከታት ነው፡፡
እኔ የሲኖዶሱ መግለጫና አገላለጡ ወርዶብኛል፡፡ ሲኖዶሳዊም መስሎ አልታየኝም፡፡ ሊቃውንቱ ያዩት፣ ጳጳሳቱ የተወያዩበት፣ ቅዱሳት መጻሕፍቱ ያሹት፣ ቀኖናዎቹ የዳሰሱት፣ ትውፊቱ የነካው፣ ባሕሉ ያጠነው አልመስልህ አለኝ፡፡ ‹ወይ እንደ እስክንድ ተዋጋ ወይ የእስክንድርን ስም መልስ› አለ ታላቁ እስክንድር፡፡

Saturday, April 11, 2015

መተማመን በጠፋበት መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሹም ሽሩ ቀጥሏል * ኮረኔል ጋይም እና ኮረኔል እሸቴ ከስልጣናቸው ዝቅ ተደረጉ

በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ስርዓት በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ላይ እምነት በማጣቱ ምክንያት እንዱን በማውረድ ሌላኛውን በመሾም ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ምንጮቹን ጠቅሶ ደህሚት ዘገበ:: ዜናው እንደወረደ እንደሚከተለው ተስተናግዷል::
Photo File
Photo File

ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ በደረሰን መረጃ መሰረት ውስጣዊ አሰራሩ በስብሶ በሰራዊቱ አዛዦች እምነት አጥቶ የሚገኘው የኢህአዴግ ስርዓት በ31ኛ ክፍለ ጦር ውስጥ እየሰራ የቆየውን ኮነሬል ጋይም የተባለውን አዛዥ በስርዓቱ ላይ እምነት የለውም በሚል ምክንያት ከነበረበት የአዛዥነት ደረጃ በማውረድ። በምትኩ ኮነሬል ዘነበ የተባለውን ከ23ኛ ክፍለጦር በማስመጣት ኮነሬል ጋይም ምክትል ሆኖ አዲሰራ መደረጉን የተገኘው መረጃ አስረድቷል::
የኢህአዴግ ገዢ ስርዓት የአመራር ለውጥ በማድረግ ካጋጠመው ስጋት የሚላቀቅ ስለመሰለው የ7ኛ ሜካናይዝድ አዛዥ የነበረውን ኮረኔል እሸቴ ከነበረበት የአዛዥነት ደረጃ በማውረድ የአመራር ለውጥ እየተደረገላት ባለችው የ31ኛ ክፍለጦር በሦስተኛ ደረጃ አዛዥ ሆኖ እንዲሰራ መመደቡን የገለፀው መረጃው እየተካሄደ ባለው ከሃላፊነት የማውረድና የመሾም ተግባር ያልተደሰቱት አዛዦች በስርዓቱ ላይ የከፋ ጉዳት ማድረስ እንደሚችሉ ከቦታው የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል::

Wednesday, April 8, 2015

በ24ኛው ክፍለጦር ውስጥ የሚገኙ ወታደሮች ትጥቃቸውን እየሸጡ በመጥፋት ላይ ናቸው ተባለ

ትህዲኤን እንደዘገበው በምዕራብ እዝ በ24ኛ ክ/ጦር ውስጥ የሚገኙ የገዢው ኢህአዴግ ጉጅሌ ወታደሮች በየወቅቱ መሳሪያቸውንና ትጥቃቸውን እየሸጡ በመጥፋት ላይ እንዳሉ ተገለፀ::
(ፎቶ ከፋይል)
(ፎቶ ከፋይል)

ትህዴን ከክፍለጦሩ ውስጥ ባገኘነው መረጃ መሰረት ሲል በዘገበው ዘገባው በምዕራብ እዝ 24ኛ ክ/ጦር የገዢው ኢህአደግ ጉጅሌ የሰራዊት አባላት በሚቀጠሩበት ወቅት በስርአቱ የሚገባላቸው ቃል ሰለማይተገበር ካላቸው የማህበራዊ ችግር የተነሳ መሳሪያዎቻቸውንና ትጥቃቸውን እየሸጡ በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ከገለፀ በኋላ። በተለይ ደግሞ የክፍለ ጦሩ አባላት 2ኛ ረጅመንት የሆኑት ሁለት ወታደሮች መጋቢት 20/ 2007 ዓ/ም ክፍላቸውን ትተው ዳንሻ አልፈው በጎንደር መንገድ በመሄድ ላይ እያሉ ለሲቪሉ ማህበረሰብ መሳሪያቸውንና ትጥቃቸውን ግዙን መሳፈሪያ አጥተናል እንዳሏቸው ሊታወቅ ተችሏል::
መረጃው በማከል እንዳስረዳው የክፍለ ጦሩ አዛዦች ለሰራዊቱ የማህበራዊ አገልግሎት ተብሎ የመጣውን ገንዘብ። ከታች እስከ ላይ ተሳስረው ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆናቸውን በሰራዊቱ ተገምግሞ ሲያበቃ። እስከ አሁን ድረስ ግን የተተገበረ ለውጥ እንደሌለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል ሲል ትህዴን ዘግቧል::

Tuesday, April 7, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ማንኛዉም አዲስ የእምነት ተቋም እንዳይገነባ መመርያ ወጣ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40356#sthash.f3i53Glu.dpuf

አቡበከር አህመድ እንደዘገበው:-
መንግስት በሴኩላሪዝም ስም ህብረተሰቡን በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከእምነቱ ለማስወጣት የሚያደርጋቸውን ጥረቶች አጠናከሮ የቀጠለ ሲሆን የዚህ እቅድ አንደ አካል የሆነውን ድርጊቱን ማንኛዉም አይነት የእምነት አዲስ ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳይገነቡ በሚል መመሪያ ማዉጣቱን ምንጮች አስታዉቀዋል።
Ethiopia-Addis-Ababa-2
በየትኛዉ እምነት አማኞች ፈጣሪያቸውን በአንድነት የሚያመልኩበት ቦታና የእምነቶቻቸውን ጥሪ የሚያደርጉበት ቦታ የእምነት የእምነት ተቋማቸዉ ሆኖ እያለ ከተማዋ እጅጉን እያሰፋችበት በሚገኘው በዚህ ወቅት ላይ ይህ አይነቱ ወሳኔ መተላለፉ መንግስት ህብረተሰቡን ከእምነቱ ለማራቅ ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሎ እየተተቸ ነው::
ዉሳኔው ሌላ መመሪያ እስኪመጣ ድረስ እንዲሰራበት የተላለፈ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በቅርቡ በተለያዩ እምነቶች ለእምነት ተቋም መገንቢያ ተብለው የተከለሉ ቦታዎችን መንጠቅ እንደተጀመረም ምንጮች አካተዉ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ማንኛዉም አዲስ የእምነት ተቋም እንዳይገነባ መመርያ ወጣ - Zehabesha Amharic

በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ማንኛዉም አዲስ የእምነት ተቋም እንዳይገነባ መመርያ ወጣ - Zehabesha Amharic