Tuesday, June 2, 2015

ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት በገዢው መንግስት እንዲቃጠል ተደረገ

የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ቦንጋ አካባቢ የነበረ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት እንዲቃጠል ማድረጋቸውን የትህዴን ድምጽ ዘገበ::
Zehabesha News
የትህዴን ምንጭ የዜና ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡብ ክልል ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ ሰፊ የተፈጥሮ ጫካ በአካባቢው ህዝብ ለዘመናት ጠብቆት የኖረ ሃብት ሲሆን የገዢውን ስርአት በመቃወም እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ነው ብለው ስጋት ላይ የወደቁት የስርአቱ ካድሬዎች እሳት ለኩሰው እንዲቃጠል ማድረጋቸውና ይህን እኩይ ተግባር የታዘበው የአካካባቢው ህዝብም በስርአቱ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳስነሳ ለማወቅ ተችሏል።
የአካባቢው ህዝብ እየተቃዎመ በነበረበት ሰዓት እንደገለፀው በአፋችሁ ልማት አልሙ፤ ድህነት አጥፉ እያላችሁ በተግባር ግን መተኪያ የሌላቸውን የተፈጥሮ ሃብቶችን እያቃጠላችሁ ነው በማለት ሃይለኛ ተቃውሞ ማንሳታቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለማስታረቅ ሱዳንና ኳታር እቅድ መያዛቸውን ተሰምተዋል

የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑማር ልበሽር የአገሪቱን ምርጫ በማሸነፋቸው በነገው ዕለት የቃለመሃላ ሥነ ሥርዓት ያካሂዳሉ።
በዚህ በዓል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ ፊት
ለፊት ይገናኛሉ።
የሱዳንና የኳታር መሪዎች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከረረ ጥላቻ የሚገኙት ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማስታረቅ ሙከራ
ያደርጋሉ ተብሏል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ጥል በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በምሥራቅ አፍሪካ ሠላም ለማስፈን ማነቆ መሆኑን የተረዱት
መሪዎቹ ችግሩን ለመፍታት በቁርጠኝነት የማስታረቁ ሥራ እንደሚሞክሩት ይጠበቃል።
ፕሬዝደንት አልበሽር በሚያደርጉት የቃለመሃላ ሥነስርዓት ከኤርትራን ኢትዮጵያ በተጨማሪ የኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣
ግብጽ፣ ቻድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያንና የሌሎች አገሮች በርካታ መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የ91 ዓመት ዕድሜ አዛውንት የ ዚምባብዌንፕረዚደንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሮበርት ሙጋቤ በሥነሥርዓቱ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ze Habesha.com