የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑማር ልበሽር የአገሪቱን ምርጫ በማሸነፋቸው በነገው ዕለት የቃለመሃላ ሥነ ሥርዓት ያካሂዳሉ።
በዚህ በዓል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ ፊት
ለፊት ይገናኛሉ።
የሱዳንና የኳታር መሪዎች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከረረ ጥላቻ የሚገኙት ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማስታረቅ ሙከራ
ያደርጋሉ ተብሏል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ጥል በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በምሥራቅ አፍሪካ ሠላም ለማስፈን ማነቆ መሆኑን የተረዱት
መሪዎቹ ችግሩን ለመፍታት በቁርጠኝነት የማስታረቁ ሥራ እንደሚሞክሩት ይጠበቃል።
ፕሬዝደንት አልበሽር በሚያደርጉት የቃለመሃላ ሥነስርዓት ከኤርትራን ኢትዮጵያ በተጨማሪ የኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣
ግብጽ፣ ቻድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያንና የሌሎች አገሮች በርካታ መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የ91 ዓመት ዕድሜ አዛውንት የ ዚምባብዌንፕረዚደንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሮበርት ሙጋቤ በሥነሥርዓቱ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ze Habesha.com
No comments:
Post a Comment