Monday, July 20, 2015

ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ

ሐምሌ 12 2007 ዓ.ም.
ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።
ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።
አርበኞች ግንቦት 7 አመራሩን ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን እና ትግሉ በሚጠይቀው ቦታ እንዲገኙ የሚያደርግ መሆኑ ሲገልጽ ቆይቷል። አሁን ትግሉ በደረሰበት ደረጃ የአመራሩ በትግሉ ሜዳ ውስጥ መገኘት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ሊቀመንበሩን ጨምሮ አመራሩን ወደ ትግሉ ሜዳ አንቀሳቅሷል። በዚህም መሠረት የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግል ሜዳ ወርዷል።
ትግሉ መሯል። ወሳኝ የሆነ ትግል ውስጥ ገብተናል። የትግሉ መሪዎች የሕይወት መስዋዕትነት እሚከፈልበት ቦታ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት የንቅናቄው አመራር በተሟላ ሁኔታ በትግሉ ሜዳ ውስጥ እንዲገኝ ማድረግ ተችሏል። ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ዘረኛው የህወሓት አገዛዝን ከጫንቃችን ለማስወገድ ቆርጠን እንድንነሳ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
ኢትዮጵያን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ የሚያወጣው አርበኞች ግንቦት 7 ብቻ አይደለም። ስለሆነም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚደረገው ትብብር ቀዳሚ ትኩረት ከተሰጣቸው ሥራዎች አንዱ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ለድል እንዲበቃ ይታገላል። ኢትዮጵያዊያንም በያሉበትም በተመሳሳይ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ላይ ክንዳቸውን እንዲያነሱ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
እነሆ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በአካል ትግል ሜዳ ውስጥ ይገኛል። የሚችል ሁሉ እንዲከተል፤ መከተል የማይችል በያለበት ሁኖ ሁለገብ ትግሉን እንዲያጧጥፍ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ


Thursday, July 9, 2015

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ከእስር ተፈታች፡፡

በሽብር ወንጀል ተከሳ የአምስት አመት እስራት ተፈርዶባት የነበረችው ጋዜጠኛ ርዮት የ4 አመት አመክሮ ጊዜዋን አጠናቃ ትናንት ከእስር ተፈታለች፡፡
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በሽብርተኝነት ወንጀል 14 አመት እስራት ተቀጥታ የነበር ሲሆን ባደረገችው የይግባኝ ክርክር ሙያዋን በመጠቀም የሽብርተኛ ቡድንን ረድታለች በሚል ወንጀል ብቻ ቅጣቱ ወደ 5 አመት ሊወርድላት ችሎ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ከእስር ተፈታች፡፡ በሽብር ወንጀል ተከሳ የአምስት አመት እስራት ተፈርዶባት የነበረችው ጋዜጠኛ ርዮት የ4 አመት አመክሮ ጊዜዋን አጠናቃ ትናንት ከእስር ተፈታለች፡፡
DIRETUBE.COM

Sunday, July 5, 2015

በዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት ጦርነቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፥ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44812#sthash.Pf92nKVE.dpuf

የ44ኛውን ክፍለ ጦር በማንቀሳቀስ በወልቃይት ዓካባቢ በሰፈረው የቀደምት ወያኔ ታጋይ ሰራዊት ታጅቦ በመጣ የወያኔ ሰራዊት እና በዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰራዊት መካከል፥ ዳንሻ ዓካባቢ፣ ጓንጓ ሳግላ እና ማይንቧ በሚሉ ሁለት ቦታዎች በትላንትናው ምሽት ከፍተኛና መረር ያለ ውጊያ ተደርጓል፥ ተኩሱ ዓሁንም እንደቀጠለ ነው፥
zemene Kassieዓመጣጣቸው የሰራዊታችንን እንቅስቃሴና የተነሳውን ሕዝባዊ የዓመጽ ማዕበል ለመግታት ታስቦ እንደሆነ ይታያል፥ በዓውደ ውጊያው የወያኔ ነባር ታጋዮችና ከፍተኛ መኮንኖች እንደተገደሉ በስም ዝርዝር ከግንባሩ ደርሶናል፥
የትግል ስልታቻንና ውጊያችን የወቅቱን ሁኔታ ያገናዘበ፥ በሰራዊታችን ቆስቋሽነት ሕዝባዊ ዓመጽ በማቀጣጠል፥ ብሶት ያበሰለውን ሕዝብ ያካተተና በዓካባቢው ሕዝብ የታቀፈ እንጂ ቦታ በመያዝና በማፈግፈግ የሚካሄድ የተራዘመ ጦርነት ዓይደለም፥
ከወያኔ ጋር ትንቅንቁ ይቀጥላል! ከሕዝቡ ከፍተኛ ድጋፍ እያገኘን ነው፥
እኛም እግራችን የረገጠውን መሬትና ያለፍንበትን ሁሉ በሕዝቡ እጅ እያስገባን ሕዝብ ዓብሮን እንዲዋደቅ ማድረግ ነው ዓሰራራችን፥
የዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ቃል ዓቀባይ ታጋይ ዘመነ ካሴ
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44812#sthash.Pf92nKVE.dpuf