(ዘ-ሐበሻ) የወሊሶ ሉቃስ ሆስፒታል በቁስለኛ ወጣቶች መጥለቅለቁ ተዘገበ:: በሰላማዊ መንገድ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ለመቃወም በወጡ ወጣቶች ላይ አጋዚ ጦር ባዘነበው ጥይት በርካታ ወጣቶች መቁሰላቸው ተዘግቧል::


በወሊሶ ሉቃስ ሆስፒታል እስካሁን የሞተ ተማሪ ያልተመዘገበ ሲሆን የህክምና ባለሙያዎች ግን ከበርካታ ወጣቶች ሰውነት ውስጥ ጥይቶችን በማውጣት ላይ መሆናቸው ታውቋል::
በሌላ በኩል በሆሮ ጉድሩ አሙሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፌደራል ፖሊስ ተኩስ የተነሳ እንዲሁ ሁለት ተማሪዎች ክፉኛ መቁሰላቸውና በርካታ ሰላማዊ ተማሪዎች መደብደባቸው ተዘግቧል;;;
በሆሮ ጉድሩ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተጨማሪ ትናንሽ ተማሪዎች እና የአካባቢው ነዋሪ ሳይቀር አደባባይ በመውጣት ድምጹን ሲያሰማ ቆይቷል:: በመጨረሻም ለዚህ ሰላማዊ ሕዝብ ምላሹ ጥይት መሆኑ የአካባቢውን ሕዝብ እንዳስቆጣው ጨምሮ የደረሰን መረጃ አመልክቷል::
የኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ በቡሎ ቡሼ ምስራቅ ወለጋ; ደቡብ ም ዕራብ ሸዋ ዋንጪ ከተማ; እና በምራብ ሸዋ አባቢ ከተማና ጊንቦ ቀጥሏል:: በተለይም በምስራቅ ሸዋ አባቢ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የአጋዚ ጦር ደርሶ የጥይት ዘናብ በሕዝቡ ላይ ማውረዱ ተሰምቷል:: ምን ያህል ሰው እንደቆሰለ እና እንደሞተ የደረሰን መረጃ ባይኖርም በርካታ ሰዎች ወደ ህክምና እየተወሰዱ መሆኑን የአይን እማኞች ተናግረዋል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በምስራቅ ወለጋ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ተማሪዎች ላይ የአጋዚ ጦር በወሰደው እርምጃ 3 ተማሪዎች መገደላቸው ተሰማ:: የቡርቃ ዋጆ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሆኑት ባንቲ ዱጉማ እና ሉንጫ ገመቹ የተባሉት ተማሪዎች ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዷል ተብሏል:: እንዲሁም በላንጋኖ ከተማ አላዛር ቀልቤሳ የተባለ ወጣትም የአጋዚ ጥይት ራት ሆኗል::
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48902#sthash.gJjEOkd6.dpuf
No comments:
Post a Comment