Friday, November 29, 2013

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንምመከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።
ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።
ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።
እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።
እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።
በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።
የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።
ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።
ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።
እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።
ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!(source www.ginbot7.org)

Thursday, November 28, 2013

ተዋርደን አንቀርም!!!

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን
በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ
በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ
በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት
በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው
ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ
ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡

ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ
እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን
በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ
ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት
ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ
ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ
ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል
አልሰጡንም፡፡

ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ
ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች
መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች
በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ
ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን
ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው
ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ
ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው
ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?

ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር
ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም
አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም
በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም
አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ
ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣
እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን
መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡

አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ
ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ
መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት
ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡

ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ
በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ
የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ
ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡

ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት
ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና
ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡

ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ
ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል?
እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን
ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ
ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ
በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡

ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ
ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች
ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም
ይላሉ?!::
እንዴት!
በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡
የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ
ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው
እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር
መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት
ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት
ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ
ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡

እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን
አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡
አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም
ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ
ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት
እንዲችል ሆኗል፡፡

ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ
ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ
የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው
ነበር፡፡

ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን
መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡

(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)
source ethiomedia.com

[Must Listen] VOA talks with EPPF spokesperson about the attack they claim they made against government forces - Novembe

http://www.ethiotube.net/video/28459/Must-Listen-VOA-talks-with-EPPF-spokesperson-about-the-attack-they-claim-they-made-against-government-forces--Novembe

Major Dawit WoldeGiorgis with Shaka Ssali, Straight Talk Africa on Saudi’s Crackdown Against Ethiopians

http://ecadforum.com/ethiopianvideo/2013/11/27/straight-talk-africa-on-saudis-crackdown-against-ethiopians/

Wednesday, November 27, 2013

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ!!!

የወያኔ ገዢ ጉጅሌ በባህርዩ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አጋጥሟት የማያውቅ ፍጹም ኢሰብዓዊና ነውረኛ ስብስብ እንደሆነ ለመረዳት ኢትዮጵያዊያንን ለማዋረድ የሚጠቀሟቸውን ተግባራትና ቃላትን ማጤን ይበቃል።
በሶማሌ ክልል የኦብነግን ታጣቂዎች ቅስም ለመስበር ልጃገረዶችንና እናቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም ጭምር በቤተሰብ ፊት በደቦ የሚደፍሩ፤ ለዚህ ተግባር የሠለጠኑ የልዩ ጦር አባላት መኖራቸው በስፋት የሚታወቅና በተደጋጋሚም የተዘገበ ጉዳይ ነው። ወያኔ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን በዚህ ጥቃት ተሸማቀው ያነገቡትን መሣሪያ ጥለው ፀጥ-ለጥ ብለው ይገዛሉ ብሎ ተስፋ ያደረገ ቢሆንም እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ዛሬ የሶማሌ ክልል ወንዱም ሴቱም፤ ወጣቱም አዛውንቱም በፀረ-ወያኔ አቋም የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል። በኦጋዴን የወያኔ አስነዋሪ ጥቃት የፈጠረው ምሬት በውጭ አገራትም በሚደረጉ የፀረ ወያኔ ትግሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ተሳትፎ እንዲጎለብት አድርጎታል። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
በአፋር ክልልም ተመሳሳይ ጥቃት የዘወትር ትዕይንት እየሆነ መጥቷል። የአፋር የወል የግጦሽ መሬቶች ለሸኮራ አገዳ ልማት በሚል ሰበብ ሲነጠቁ የተቃወሙ የአገር ሽማግሌዎች ተደብድበዋል፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ተደፍረዋል። በአፋርም ውስጥ ለጾታዊ ጥቃት የሰለጠነ የወያኔ ልዩ ጦር ተሰማርቶ በሴቶች ብቻ ሳይሆን በወንዶችም ላይ አስነዋሪ ጥቃት አድርሷል። በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
በጋምቤላ ውስጥ ወያኔ ወገኖቻችን ከፈጀ በኋላ በሕይወት የተረፉትም ቅስማቸውን ለመስበር ጾታዊ ጥቃት በመሣሪያነት ተጠቅሟል፤ አሁንም እየተጠቀመ ነው። በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
የወያኔ ዝቅጠት ዘግናኝ ነው። ወያኔ ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ጾታዊ ጥቃት ያላደረሰበት የአገራችን ክፍል የለም። ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ቤንሻንጉል … በሁሉም ቦታዎች ያልተነገሩ ጥቃቶች በዜጎታችን ላይ ደርሷል፤ እየደረሰም ነው።
በአንድ ወቅት በመሀል አገር፤ በሰሜን ሸዋ አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት በእብሪተኛ ወያኔ የተገደለውን ባለቤትዋን ብልት ይዛ አስክሬኑን እንድትጎትት መደረጉን ከዓይን እማኞች አንደበት ሰምተናል። በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሰበብ መስዋዕትነት እየተቀበሉ ያሉ ወገኖቻችን “ሽንታም አማራ” እየተባሉ ብልቶቻቸው ይቀጠቀጥ እንደነበር የሰማነው እና የምናውቀው ጉዳይ ነው። በወያኔ መዳፍ ውስጥ ውስጥ ገብተው በእስር ቤቶች በሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ ዘግናኝ ተግባራት እንደሚፈፀሙ መረጃዎች አሉ። በአዲስ አበባ በየቦታው ባሉት ስውር የማሰቃያ ቤቶችም ተመሳሳይ ተግባራት ዘወትር እንደሚፈፀሙ ይታወቃል።
ወያኔ ለጾታዊ ጥቃት ያሰለጠናቸው ሰዎችን በከተሞችም ውስጥ አሰማርቷል። በእነዚህ ጥቃቶች ግለሰቦች ግንባር ቀደም ተጠቂዎች ቢሆንም የተደፈርነው፣ የተዋረድነው ሁላችንም መሆናችን አጽንዖት ሊሰጠው ይገባል። የተደፈርነው እኛ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነን። የተዋረደችው የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያ ነች።
ኢትዮጵያ አገራችን እፍረት ባልፈጠረባቸው ነውረኛ የወያኔ ዋልጌዎች እንድትገዛ እንድትረገጥ በመፍቀዳችን ጥፋቱ የኛም ጭምር ነው። ይህን ነውረኛ ቡድን በሥልጣን ላይ እንዲቆይ በፈቀድንለት መጠን በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያችን ላይ የሚደርሰው በደል እየባሰ እንደሚመጣ በዓይኖቻችን እያየን በጆሮዎቻችን እየሰማን ነው።
ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባል ላይ የደረሰው ጥቃት የዚሁ አካል ነው። እኚህ ወገናችን የደረሰባቸውን ዘርዝሮ ለመናገር የሚከብድ መሆኑ ገልፀዋል። ማፈር የነበረባቸው ጥቃት አድራሾቹ መሆን ይገባቸው ነበር፤ ሆኖም ግን ይሉኝታ አልፈጠረባቸው። ምንም ይሁን ምን በወገናችን ላይ የደረሰው ጥቃት በእሳቸው ላይ ብቻ የደረሰ ሳይሆን በሁላችንም ላይ የደረሰ መስሎ የሚሰማን መሆኑን ልንነግራቸው እንወዳለን። የተዋረደችው ኢትዮጵያ አገራችን ነች።
ይህ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔ ከሥልጣን መወገድ ይኖርበታል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ” ቀዳሚ ሥራችን ነው የሚለው ኢትዮጵያን ለማዳን ከዚህ የሚበልጥ አንገብጋቢና አጣዳፊ ሥራ ስለሌለ ነው። ወያኔን ለማስወገድ እንተባበር።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Dr. Berhanu Nega speaking the media importance and TPLF Photosh

http://www.youtube.com/watch?v=6W_ABK1m6Lg

Tuesday, November 26, 2013

በሳውዲ ለሚገኙ ወገኖቻችን በአፋጣኝ እንድረስ፤ በወያኔ ላይ በጋራ እንነሳ!!!


በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መጠን የለሽ የመብት ጥሰት ለመቃወም በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በየአገራቱ የሚገኙ የሳውዲን ኢምባሲዎችን በተቃውሞ እያጨናነቁ ነው። በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ዘግኛኝ በደል የተሰማቸውን ጥልቅ የመጠቃት ስሜት ኢትዮጵያን በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በሚያሰሟቸው መሪር የሐዘን እንጉሮችና የቁጭት ንግግሮች እየገለፁ ነው። ከሐዘንና ቁጭት ባለፈም ለበደል ለተጋለጡ ወገኖቻችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍን ለማሰባሰብ ዓለም ዓቀፍ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራውን ጀምሯል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን ዓለም ዓቀፍ ጥረት ለመደገፍ በውጭ አገራት የሚገኙ አባላቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል።
ይህ ሁሉ በውጭ አገራት እየተደረገ ያለ ጥረት ነው። ኢትዮጵያዊያን ባሉበት አገራትና ከተማዎች ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድነት መንቀሳቀሳቸው የሚያስደስት ነገር ነው። ሌላው ቀርቶ በሳዉዲ ዋና ከተማ ሪያድ ውስጥ እንኳን ኢትዮጵያውያን የሳውዲን መንግሥት ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል።
የሳውዲ መንግሥት በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ የያዘውን ጨካኝ አቋም እና በመንግሥት እውቅና በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል መቃወም ያልተቻለው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ!!! ይህ እጅግ ያማል፣ ልብን ያደማል።
ወያኔ የሳውዲ የንግድ ሸሪኮቹን ለማስደሰት የፈንሳይን ግማሽ የሚያህል ለም መሬት በነፃ መስጠቱ በቂ አልመሰለውም። በአገራቸው ኢትዮጵያዊያንን ሲጨፈጭፉ፣ ሲገሉና ሲደፍሩ በቸልታ መመልከቱ በቂ የወዳጅነት ስጦታ መስሎ አልተሰማውም። እናም ሸሪኮቹ የበለጠ እንዲደሰቱና ከእስከዛሬ በበለጠ ገንዘብ እንዲደጉሙት ለማበረታታት አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲያቸው ፊት ለፊት ኢትዮጵያንን ደበደበላቸው።
ወያኔ ከሳውዲ ጋር ያለው ግኑኝነት “የቢዝነስ ሽርክና” ነው። ቢዝነሱም ኢትዮጵያዊያንን በቁማቸው መሸጥንም ያጠቃልላል። የወያኔ ሹማምንት እና የሳውዲም ቱጃሮች በዘመናዊ ባርነት ንግድ ውስጥ አቀባይና ተቀባይ ናቸው። ለዚህም ነው እየተነገደበት ያለው ምስኪን ኢትዮጵያዊ እጣ ፈንታ በአዲስ አበባና በሪያድ አንድ ዓይነት የሆነው። እዛ ዱላ፤ እዚህም ዱላ። እዛ እስር፤ እዚህም እስር። እዚያ ስድብ፤ እዚህም ስድብ። እዚያ ቶርቸር፤ እዚህም ቶርቸር። በባርያ ንግድ ውስጥ አቀባዩም ተቀባዩም ባርያዉን መግዛታቸው፣ መስበራቸው፣ መግደላቸው የማይቀር መሆኑ የታወቀ ነው። ginbot7.org

Friday, November 22, 2013

ብዙ ተባዙ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9737

Protests opposing the violence on Ethiopians in Saudi Arabia continue


Ethiopians living in different countries have continued protesting the human rights violations and violence against their compatriots in Saudi Arabia. Ethiopians residing in Bern, Switzerland have staged an ‘emotional protest’ on November 20, 2013.
The protesters were shouting outside the Saudi Embassy in Switzerland by holding slogans that denounced the Ethiopian and Saudi Arabian governments. The protesters also passed the police lines.
Activist Petros Ashenafi and other participants said the protest, held within heavy police presence, was successful.
The Ethiopian government has said that so far 8000 Ethiopians have been repatriated from Saudi Arabia. Although ESAT phoned, Dr. Tewodros Adhanom, the Minister of Foreign Affairs of Ethiopia, to get his responses regarding the numbers and the situations, he had said that he was in a meeting and the information was available on the State Television, ETV.
Although there are over 20,000 Ethiopians in Saudi Arabia who are voluntarily waiting to be deported, Saudi Arabia’s King Abdullah’s new orders for the intensification of the crackdown on migrant workers, is feared to cause another predicament on Ethiopian migrant workers living in different cities.
Information received from the Ethiopian Ministry of Foreign Affairs (MoFA) states that there are at least 180 thousand undocumented Ethiopian immigrants living in Saudi Arabia.
ESAT has learnt that protests opposing the actions of the Saudi securities and people on Ethiopian immigrants and calling for the perpetrators to be taken accountable will continue in the coming days.

Accordingly, protest will be held outside the Saudi Embassy in Berlin, Germany on November 21, 2013.  Esat news november 12 ,2013

Wednesday, November 20, 2013

Zehabesha Breaking News November 19, 2013 Saudi Arabia

http://www.youtube.com/watch?v=4x6bGxL04t8

Anonymous - Keeping It Real for Ethiopia

http://www.youtube.com/watch?v=uNRRfx6lDUQ&feature=share

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል

በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን።
በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን።
ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው።
በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው።
ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!source ginbot7.org

Tuesday, November 19, 2013

Ethiopians demonstrate outside Saudi embassy in London


18 November 2013 Last updated at 18:26 GMT
There's been growing anger among Ethiopians in and outside the country, about the way that some of their compatriots have been treated in Saudi Arabia.
Things came to a head following an ultimatum for illegal migrant workers to leave the country.
And there were clashes in Riyadh which led to several deaths last week.
On Monday, there have been demonstrations at Saudi embassies around the world.
BBC Africa's Kasim Kayira went to the one in London.
For more African news from the BBC, download the Africa Today podcast.

Monday, November 18, 2013

ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን

በንቅናቄዓችን ፀሐፊ እና በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራር አባላት ላይ የተቃጣው ረዥም ጊዜ የወሰደ የግድያ ሴራ መክሸፉ አስደስቶናል። ይህ ሴራ የወያኔ የስለላና የግድያ ኃላፊዎች በሆኑት ጌታቸው አሰፋ እና ጸጋየ በርሄ የቅርብ ክትትል የተመራ፤ የአሻንጉሊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እውቅናና ይሁንታ የተሰጠው፤ ወያኔ ከፍ ያለ ተስፋ የጣለበት ሴራ ነበር።
“ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም” የተሰኘው ይህ በወያኔ የመጨረሻ ከፍተኛው አመራር የተመራው ሴራ ስለወያኔ ውስጣዊ አደረጃጀት ጠቃሚ መረጃዎችን ሰጥቶናል። ከዚህም በተጨማሪ የወያኔ ሹማምንት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት፤ ከአመት በኋላ ስለሚደረገው ምርጫ ውጤት፤ ለሰላዮቻቸው ስለሚሰጡት ጉርሻ መጠን፤ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተስፋ ከጣሉበት ቅጥረኛ ነብሰ ገዳያቸው ጋር ካደረጉት የስልክ ንግግሮች ማድመጥ ይቻላል። ይህ ለበርካታ ጥናቶች በግብዓትነት ሊውል የሚችለውን በድምሩ ከስምንት ሰዓታት በላይ የሚፈጀው የስልክ ንግግር ቅጂ በሕዝባዊ ኃይሉ የመረጃ ክፍል አማካይነት ለሕዝብ በኢንተርኔት በነፃ ተለቋል። በአጋጣሚውም የወያኔ ገበና ተጋልጧል።
በአንፃሩ ደግሞ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተደራጀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢሆንም ምን ያህል ወያኔን እንቅልፍ እንደነሳ ተጨባጭ ማስረጃ ሆኗል። ይህ ለነፃነት ታጋዮች ከፍተኛ የስነልቦና ብርታት የሚሰጥ ነገር ሆኖ ተገኝቷል።
በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተቃጣበትን ጥቃት ከማክሸፍ በተጨማሪ የወያኔን ገበና ማጋለጥ በመቻሉ የመጀመሪያው ሁነኛ ድል ተቀዳጅቷል።
ግንቦት 7 : የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” አፕሬሽንን ላከሸፉ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት ይገልፃል። ለወደፊቱም ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊደርሱ የሚችሉ መሆኑን በመገንዘብ የመከላከል ብሎም የማጥቃት ኃይሉን እንዲያጠናክር ይመክራል።
የንቅናቀዓችን እና የሕዝባዊ ኃይሉ አመራርና አባላት ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ናቸው። “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ትግላችን ይገታ ነበር ማለት አይደለም። ትግላችን መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑን እናውቃለን። ጓዶች ሲወድቁ ሌሎች ሺዎች አርማቸውን አንስተው ትግሉን ይቀጥላሉ።
ትግሉ የሚጠይቀንን መስዋትነት ከፍለን ወያኔን ከሥልጣን አስወግደን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት የሆነባት ኢትዮጵያ እንደምትኖረን እርግጠኞች ነኝ።
ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን።
ድል ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!source ginbot7.org

Immediate release Ethiopian journalists Reeyot Alemu, Woubshet Taye, Eskinder Nega, Yusuf Getachew and Solomon Kebede

http://www.gopetition.com/petitions/ethiopia-immediate-release-ethiopian-journalists-reeyot-alemu-woubshet-taye-eskinder-nega-yusuf-getachew-and-solomon-kebede/sign.html#se

Sunday, November 17, 2013

Rettferdighet i asylpolitikken (RIA)


Herlig folkefest i Stavanger!

På det meste var det 300 til stede på lørdagens demonstrasjon for en rettferdig asylpolitikk. Bredt politisk spekter av Sv, V, Rødt og Krf holdt appeller. Redd Barnas ungdomsorganisasjon Press, støtteforeningen for Ethiopia og for Neda gjorde sammen med RIA en kjempeinnsats for å belyse ulike utfordringer Norge har for å kunne skilte med en rettferdig asylpolitikk. Rapperne Tore Pang og Bevis leverte høykvalitets rap. Det er rett og slett gøy å samles fra så mange hold med en felles sak. Her ser du bilder fra festen:
Vi vil ha NEDA og familien hjem:
DSC_0016
Annuler returavtalen med diktaturstyret i Etiopia:

DSC_0195
20131117-144455.jpg
20131117-144527.jpg
20131117-144906.jpg
20131117-144950.jpg
20131117-145057.jpg

ወያኔ የግንቦት ሰባት መሪዎችን ለመግደል ያሰሬዉ ሴራ በመክሸፉ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስተዉን እየገለጸ ነዉ


በወያኔው መረጃና ደህንነት ሃለፊ ጌታቸው አሰፋ እና በሃይለማሪያም ደሳለኝ
አማካሪ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7
ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ከሚገመተው በላይ ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል የሚያስችል
የሰውም ሆነ የቴክኖሎጂ አቅም ያለው መሆኑን አስመስክሯል የሚሉ
ተበራክተዋል። ይህን ሃሳብ የሚደግፉ ወገኖች ባንድ በኩል የፋሽስት ወያኔ
አመራሮች ምንም እንኳ ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ነው ያለነው ቢሉም ምን
ያህል የተዋረደና የቀለለ ስራ ለመስራት እንደሚደፍሩ በግልጽ በራሳቸው አንደበት
የሰማንበትና ያወቅንበት ነው ሲሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል
ራሱን ለመከላከል የሚያስችለውን ቴክኖሎጂያዊ አቅም መገንባቱንና ይህም
ለሀገራችንና ነጻነት ለጠማው ሕዝባችን ታላቅ ተስፋ ሰጭ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ሌሎች በጉዳዩ የተደሰቱ ወገኖች ደግሞ ፋሽስት ወያኔ ከዚህ በፊትም ለገንዘብና
ለስልጣን የሚጓጋጉ ለሕዝብ ልእልና ደንታ የሌላቸው እና ለማይገኝ ባዶ ምኞት
የሞቱ ሆዳሞችን በመግዛት ስንት የሕዝብ ተሰፋ እንቅስቃሴዎችን እንዳደናቀፉ
አስታውሰው ይህ ግን ልዩ ነበር ካሉ በሗላ ወያኔዎች የት ደረጃ ላይ እንዳሉና
አቅማቸውም እስከምን ድረስ እንደሆነ አወቅንበት ይላሉ። ከዚህ በፊት በተለይ
በ1997 ዓ/ም የነበረውን ምርጫ ቅንጅት ቢያሸንፍም ፋሽስት ወያኔ ገልብጦ ሁሉን
ለራሱ በማድረግ እንዲጫወት እገዛ ያደረጉለት የሕዝብ ወገን ነን እያሉ በመደለል
በሆዳቸውና በሌሎች ጥቅማጥቅሞች የተገዙ ከሃዲዎች እንደነበሩ አይዘነጋም። source ginbot7.org

Friday, November 15, 2013

አንድ አንዳርጋቸውን መግደል የነፃነቱን ትግል ማስቆም አይቻልም

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ በርግዶ ገባ። ግንቦት ሰባትን በተመለከተ እቅዳችንን ልነግርህ ነው የመጣሁት ሲል ነገሩን ጀመረ።
እሺ ምንድ ነው እቅዱ ?
የአንዳርጋቸውን፤ ጓደኞቹንና አንዳንድ የኤርትራ ባለስልጣኖችን ለመግደል ዝግጅቱ ተጠናቋል። ኤርትራ ድረስ ሂዶ “መስዋዕትነት” ለመክፈል የሚችል አንድ ሰው አግኝተን ልከናል። ግዳጁን ፈፅሞ ሲመጣ አንዳንድ ነገሮች እናደርግለታል። እርሱም ተስማምቷል።ጥቅምት 28 የምስራች እንሰማለን። እስከዛው ግን ፍተሻዎች እንዲጠናከሩ ወጥተህ ተናገር።
ሰውየው “already” ተልኳል ማለት ነው ?
አዎን ከተላከ አምስት ወር ሁኖታል።
የሚሳካ ይምስላችኋል ?
አዎን . . በሚገባ! እኛ ሞክረነዉ ያልተሳካ ምን ነገር አለ? . . . ጌታዬ። በደንብ ነው የሚሳካው። ዛሬ እዚህ መጥቼ የማሳስብዎት ይህ ጉዳይ ሲታቀድም ሲፈጸምም አልሰማሁም ብለዉ እንደ እግር ኳሱ እንዳያሳፍሩን ብዬ ነዉ።
አይዟችሁ እናንተም አታሳፍሩኝም እኔም አላሳፍራችሁም። እሺ ሰምቼያለሁ። አለ “አማኝ ነኝ ባዩ” ደሳለኝ ኃ/ማሪያም ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ የአገሪቷ ምርጥ ልጆች ደማቸው በከንቱ እንዲፈስ እየተስማማ።
“ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ንጣት በገደለው “ሲሉ አመሳጠሩ የሃገራችን ሰዎች።
“ቀፎው ነው እንጂ ሲም ካርዱ ከእኛ ነው” የተባለለትና እና በነፍሰ ገዳዮቹ ወንበር የተቀመጠውን የደሳለኝ ኃ/ማሪያምን ጉዳይ በዚህ እናበቃለን።
ህወሃቶች የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ ሲያፈሱ የኖሩ ነብሰ ገዳዮች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። አሁንም ክብሬንና ነፃነቴን የሚሉ ዜጎችን ይዘው ደብዛቸውን ለማጥፋት ብዙ ዓይንና ብዙ ጆሮዎችን በየቦታው አቁመናል እያሉ ያቅራራሉ። ይሄን ሁሉ ዓይንና ጆሮ ይዘንስ የሚያሸንፈን ማን ነው ? ሲሉም ይደመጣሉ። እነርሱ እንደሚሉት ዓይኖቻቸው ማየት፤ጆሮዎቻቸውም መስማት የሚችሉ አይደሉም። የህወሃት ዓይኖች ማየት የተሳናቸው እውራን፤ ጆሮዎቻቸውም ማድመጥ የማያውቁ ደናቁርት እንደሆኑ የታወቀ ነው። ህወሃቶች ይህን የማይሰማ ጆሮና ፤ማየት የተሳነውን ዓይን ይዘው እየተደናበሩ፤ ይህን ለመደበቅ ህይዎት ያላቸው መስለው ይታያሉ። አዎን ህወሃቶች ጭው ባለ በርሃ ላይ ብቻችሁን እንደቆማችሁ እወቁ። የሚነገረው እና የሚሆነው በሙሉ ስለተሰወረባችሁ በብዙ ሚሊየኖች መሃከል ብቻችሁን እርቃናችሁን ቀርታችኋል። ብዙ ሚሊዮን ዓይኖች እና ጆሮዎች በእናንተ ላይ መተከላቸውን ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት የፍትህ፤የነፃነት እና የእኩልነት ንቅናቄ እንደ ህወሃት-ኢህአዴግ ጆሮዉ የተደፈነና አይኑ የታወረ ድርጅት አይደለም። ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚያይ ዓይን፤ የሚሰማ ጆሮና የሚያስተዉል ልቦና ያለው ህያው ንቅናቄ ነው። የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጥያቄ ግልፅ ነው። ነፃነት ! ፍትህ ! እና ዲሞክራሲ ! ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ እንዲያገኙ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ተነስተናል ጉዞ ጀምረናል፤ ሺ አንድአርጋቸውን ፈጥረናል። ልብ ይበሉ ነፃነት ፍትህ እና ዴሞክራሲ ለሰው ልጆች የተሰጡ ክቡር ስጦታዎች ናቸው። ህወሃት እነዚህን ክቡር ስጦታዎች ከዜጎች ላይ ነጥቆና ህዝብን ረግጦ መቀጠል የለበትም። ህወሃት የዜጎችን ነፃነት ነጥቆ ፤ ፍትህን አጓድሎና ህዝብን ረግጦ እንደከዚህ በፊቱ በሠላም እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ተሳስቷል። በህወሃት ቅዥት አገራችን ተጎድታለች። ህዝቧም ለማያባራ ጉስቁልናና ውርደት ተዳርጓል። ብዙዎችም አገር አልባ ሁነው በየሰው አገሩ መፃተኛ ሁነው እንዲኖሩ ተገደዋል። በእኛ እምነት በአገራችን ላይ እየደረሰ ላለው ውርደት በዋናነት ተጠያቂው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ዋነኛው ጠላት ነው የምንለውም ዜጎቻችንን ለጉስቁልናና ለውርደት ስላደረገም ጭምር ነው። እኛ ይህን አገር በቀል ጠላት ከሥሩ ነቅለን ለመጣል ተነስተናል። ከዚህ ትግል የሚያቆመን ምንም ዓይነት ምዳራዊ ኃይል እንደሌለ ህወሃቶች እንዲያውቁት እንፈልጋለን። ህወሃቶች አንገታችንን አስደፍተው አይገዙንም። ጥቁር ደም ያፈራቻቸው የቁርጥ ቀን ውድ ልጆቿ የነጻነት ታሪክ በጥቁር ቀለም ይጻፍ ዘንድ የሚያደርጉትን ሀገርን የማዳን ጥሪ እንዲህ በቀላሉ መግታት ከቶ አይቻልም። ወያኔዎች አትደናበሩ! ጋሬጣውን መለየትን ለእኛ ተውሉን።
ታዲያ ይህን ንቅናቄ አንድ አንዳርጋቸውን በመግደል ማስቆም የሚቻል የሚመስለው ጅላ ጅል ቡድን አገሪቷን እየገዛ በመሆኑ ተቆጭተናል። አንዳርጋቸውን መግደል ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊ አንዳርጋቸውን መፍጠርና ትግሉንም የሚያጠናክር እና የሚያፋፍም መሆኑን አልተረዱም። የኢትዮጵያ ህዝብ የእምቢተኝነት፣ የአልገዛም፣ የነጻነት ታሪክን ለማስከበር መሰዋእትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆንን ከአንዳርጋቸው ከተማረ ቆይቷል። መቆጨታችን ግን እንዲሁ በቁጭት ብቻ የሚቀር የሚመስለው ካለም ድግሞ ተሳስቷል። ይሄ ቁጭት በየደረሱበት የንፁሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ አገር መምራት የሚመስላቸውን ህውሃቶች ከተንጠለጠሉበት ዙፋን አውርደን በልካቸውና በአቅማቸው እንዲኖሩ ለማድረግ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ያደርገናል። ህወሃት ውስጥ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ግለሰብ ካለ አሁን ቆም ብሎ እንዲያስብ እናሳስበዋለን። ጀንበር ሳትጠፋባችሁ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚደረገውን ትግል ተቀላቀሉ። እርግጥ ነው ለነፃነት የሚደረገው ትግል በየመስኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ህወሃትም የእጁን እንደሚያገኝ ምንም ዓይነት ብዥታ እንዳይኖራችሁ ልንነግራችሁ እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት የቆመበት መሠረት ፅኑ፤ ዓላማውም ህዝባዊ ነው። በዚህ በፀና መሠረት ላይ ህዝባዊውን ዓላማ አንግበው የተነሱ ሚሊዮኖች አሉ። እነዚህ ሚሊየኖች የሌሉበት ሥፍራ የለም። ከቤተ-መንግስት እስከ እርሻ ማሳ፤ ከስለላ ተቋማት እስከ አገሪቷ መከላከያ ኃይል፤ ከሃይማኖት ተቋማት እስከ መንግስት መሥሪያ ቤቶች፤ ከዘመናዊ ትምህር ተቋማት እስከ ተከበሩ ገዳማት ድርስ ለክብራቸው ዘብ የቆሙ ሚሊየኖች አሉ። እነዚህ ሚሊኖች የቆሙት መረቅ የበዛበትን ወጥ ዓላማ አድርገው ሳይሆን በፀናው መሠረት ላይ ለተተከለው ክቡር ዓላማ ነው። ይህ ክቡር ዓላማ ነፃነት፤ ፍትህ ፤እኩልነት እና የህግ የበላይነት እንጂ ሌላ አይደለም። እነዚህ ሚሊየኖች አትኩረው ማየት የሚችሉ ድንቅ ዓይኖች ያሏቸው፤ አጥርተው ማድመጥ የሚችሉ ክቡራን ጆሮዎች ያሏቸው መሆናቸውን ህወሃቶች እንዲያውቁት እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት ማንንም ፍርሃት እና ድንጋጤ ውስጥ መክተት አይፈልግም።እንዲያውም ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚታገለው ዜጎች ሁሉ ከፍርሃት ነፃ ሁነው በደስታ እንዲኖሩ ለማስቻል ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ካሁን ወዲያ ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዓይንና ጆሮ የሚያመልጥ አንዳችም ነገር እንደማይኖር የሚያሳድደን ቡድን እንዲያውቀው እንፈልጋለን። ዓይንና ጆሯችን በሁሉም ሥፍራ በንቃትና በጥንቃቄ ነገሮችን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ህወሃቶች ከትዕቢታችሁ ብዛት የተነሳ የህዝቡን ምክር መናቃችሁን እናውቃለን።የወገኖቻችንንም ድምፅ ጫጫታ እያላችሁ እንደምትሳለቁም እናውቃለን። ይሄ እንደማይጠቅማችሁ ብዙ ግዜ ነግረናችኋል። የህዝቡን ምክር ስሙ፤ የወገኖቻችሁንም ድምፅ አድምጡ ብንላችሁ በእምቢታችሁ ፀንታችኋል። ልቦናችሁ እንደ ፈርዖን ልብ ደንድኗል።ልብ ማደንደን እንኳን እናንተን ለመሠለ ደካማ ፍጡር ይቅርና በዘመኑ እኔ “እምላክ” ነኝ እሰከ ማለት ለደረሰው ለፈርዖንም አልበጀም። እንዲህ ዓይነት የልብ ድንዛዜ እናንተ በዚያ ጠባብ ዓላማችሁ ጣልነው ለምትሉት ለመንግስቱ ኃ/ማሪያምም አልረባውም። አሁንም የእኛ ምክር አጭርና ግልፅ ነው። የመዘዛችሁትን የበቀል ሰይፍ ወደ ሰገባው መልሱ። የዘጋችሁትን በር ክፈቱ። የነጠቃችሁትን የዜጎች ነፃነት መልሱ። በህዝቡ ላይ ያወረዳችሁትን የፍርሃት ድባብ አስወግዱ። የተከላችሁትን የዘረኝነት እሾህ ንቀሉ። ከእውነት ጋርም ታረቁ። እንዲህ ብታደርጉ የዚያችን አገር በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን የሚበላችሁን እሳት ማጥፋት አይቻላችሁም። መጥተናል!!
እኛም ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክረናል። የትግል ዘርፋችን ሰፍቷል። በሁሉም አቅጣጫ መረባችን ተዘርግቷል። ከዚህ መረብ የትም አታመልጡም። ማምለጫ መንገዳችሁ አንድ ብቻ ነው። እርሱም የህዝቡን ድምፅ መስማት፤ እውነተኛ መልስ መስጠት እና ለህግ ተገዢ መሆን። አበቃን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
 source- ginbot7.org

Wednesday, November 13, 2013

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል

በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን።
በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን።
ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው።
በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው።
ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!source ginbot7.org

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ!!!


ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ!!!

የወያኔ ገዢ ጉጅሌ በባህርዩ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አጋጥሟት የማያውቅ ፍጹም ኢሰብዓዊና ነውረኛ ስብስብ እንደሆነ ለመረዳት ኢትዮጵያዊያንን ለማዋረድ የሚጠቀሟቸውን ተግባራትና ቃላትን ማጤን ይበቃል።
በሶማሌ ክልል የኦብነግን ታጣቂዎች ቅስም ለመስበር ልጃገረዶችንና እናቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም ጭምር በቤተሰብ ፊት በደቦ የሚደፍሩ፤ ለዚህ ተግባር የሠለጠኑ የልዩ ጦር አባላት መኖራቸው በስፋት የሚታወቅና በተደጋጋሚም የተዘገበ ጉዳይ ነው። ወያኔ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን በዚህ ጥቃት ተሸማቀው ያነገቡትን መሣሪያ ጥለው ፀጥ-ለጥ ብለው ይገዛሉ ብሎ ተስፋ ያደረገ ቢሆንም እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ዛሬ የሶማሌ ክልል ወንዱም ሴቱም፤ ወጣቱም አዛውንቱም በፀረ-ወያኔ አቋም የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል። በኦጋዴን የወያኔ አስነዋሪ ጥቃት የፈጠረው ምሬት በውጭ አገራትም በሚደረጉ የፀረ ወያኔ ትግሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ተሳትፎ እንዲጎለብት አድርጎታል። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
በአፋር ክልልም ተመሳሳይ ጥቃት የዘወትር ትዕይንት እየሆነ መጥቷል። የአፋር የወል የግጦሽ መሬቶች ለሸኮራ አገዳ ልማት በሚል ሰበብ ሲነጠቁ የተቃወሙ የአገር ሽማግሌዎች ተደብድበዋል፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ተደፍረዋል። በአፋርም ውስጥ ለጾታዊ ጥቃት የሰለጠነ የወያኔ ልዩ ጦር ተሰማርቶ በሴቶች ብቻ ሳይሆን በወንዶችም ላይ አስነዋሪ ጥቃት አድርሷል። በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
በጋምቤላ ውስጥ ወያኔ ወገኖቻችን ከፈጀ በኋላ በሕይወት የተረፉትም ቅስማቸውን ለመስበር ጾታዊ ጥቃት በመሣሪያነት ተጠቅሟል፤ አሁንም እየተጠቀመ ነው። በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
የወያኔ ዝቅጠት ዘግናኝ ነው። ወያኔ ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ጾታዊ ጥቃት ያላደረሰበት የአገራችን ክፍል የለም። ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ቤንሻንጉል … በሁሉም ቦታዎች ያልተነገሩ ጥቃቶች በዜጎታችን ላይ ደርሷል፤ እየደረሰም ነው።
በአንድ ወቅት በመሀል አገር፤ በሰሜን ሸዋ አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት በእብሪተኛ ወያኔ የተገደለውን ባለቤትዋን ብልት ይዛ አስክሬኑን እንድትጎትት መደረጉን ከዓይን እማኞች አንደበት ሰምተናል። በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሰበብ መስዋዕትነት እየተቀበሉ ያሉ ወገኖቻችን “ሽንታም አማራ” እየተባሉ ብልቶቻቸው ይቀጠቀጥ እንደነበር የሰማነው እና የምናውቀው ጉዳይ ነው። በወያኔ መዳፍ ውስጥ ውስጥ ገብተው በእስር ቤቶች በሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ ዘግናኝ ተግባራት እንደሚፈፀሙ መረጃዎች አሉ። በአዲስ አበባ በየቦታው ባሉት ስውር የማሰቃያ ቤቶችም ተመሳሳይ ተግባራት ዘወትር እንደሚፈፀሙ ይታወቃል።
ወያኔ ለጾታዊ ጥቃት ያሰለጠናቸው ሰዎችን በከተሞችም ውስጥ አሰማርቷል። በእነዚህ ጥቃቶች ግለሰቦች ግንባር ቀደም ተጠቂዎች ቢሆንም የተደፈርነው፣ የተዋረድነው ሁላችንም መሆናችን አጽንዖት ሊሰጠው ይገባል። የተደፈርነው እኛ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነን። የተዋረደችው የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያ ነች።
ኢትዮጵያ አገራችን እፍረት ባልፈጠረባቸው ነውረኛ የወያኔ ዋልጌዎች እንድትገዛ እንድትረገጥ በመፍቀዳችን ጥፋቱ የኛም ጭምር ነው። ይህን ነውረኛ ቡድን በሥልጣን ላይ እንዲቆይ በፈቀድንለት መጠን በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያችን ላይ የሚደርሰው በደል እየባሰ እንደሚመጣ በዓይኖቻችን እያየን በጆሮዎቻችን እየሰማን ነው።
ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባል ላይ የደረሰው ጥቃት የዚሁ አካል ነው። እኚህ ወገናችን የደረሰባቸውን ዘርዝሮ ለመናገር የሚከብድ መሆኑ ገልፀዋል። ማፈር የነበረባቸው ጥቃት አድራሾቹ መሆን ይገባቸው ነበር፤ ሆኖም ግን ይሉኝታ አልፈጠረባቸው። ምንም ይሁን ምን በወገናችን ላይ የደረሰው ጥቃት በእሳቸው ላይ ብቻ የደረሰ ሳይሆን በሁላችንም ላይ የደረሰ መስሎ የሚሰማን መሆኑን ልንነግራቸው እንወዳለን። የተዋረደችው ኢትዮጵያ አገራችን ነች።
ይህ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔ ከሥልጣን መወገድ ይኖርበታል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ” ቀዳሚ ሥራችን ነው የሚለው ኢትዮጵያን ለማዳን ከዚህ የሚበልጥ አንገብጋቢና አጣዳፊ ሥራ ስለሌለ ነው። ወያኔን ለማስወገድ እንተባበር።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
SOURCE -WWW.GINBOT7.ORG

Mission Impossible

https://www.youtube.com/watch?v=Pgsvpjf-oQw&feature=c4-overview&list=UU2AvdK6_3mGgyky6T82QBMQby esat tv

A Very Sad Message from Saudi Arabia [Must Watch]

A Very Sad Message from Saudi Arabia [Must Watch] 

Tuesday, November 12, 2013

Grand Demonstration in Oslo -Norway

Stop violence against Ethiopians in Saudi Arabia!!!
The barbaric treatment that Ethiopian citizens are receiving in the hands of Saudis is shameful and the government of Saudi Arabia should be ashamed of its citizens it is shameful that the government is standing by and doing nothing as these kinds of atrocities are being levied against other human beings. How would you feel if your countrymen were treated this way in another country?

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9186

Monday, November 11, 2013

Schools closed after protests in Kucha

ESAT News  November 8, 2013

Many elementary and secondary schools have been closed in  Kucha Woreda, a town that has been wobbled due to ‘identity’ related protests and conflicts for the past few months.
The students seek a right to study in their own language and the rights violations in the area to stop. After the Federal police surrounded the area, 25 to 40 students have been detained.
As the tension escalates, at least 40 people that have been released recently have been rearrested.
Teachers suspected of organising the protest have been called to expose those that led the protest. The officials told the teachers that they can do nothing than talking to mass media such as ESAT, DW and the VoA.
Previously, at least 60 people from the area had been detained and 40 civil servants were sacked. Over 160 Bajaj vehicles have also been seized.
ESAT’s effort to speak to police has been unsuccessful.

Thursday, November 7, 2013

ቅን መሆን ካልቻልክ ቅንቀን አትሁን !

ቅን መሆን ካልቻልክ ቅንቀን አትሁን
አንዳንድ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ግለሰቦች እና ቡድኖች ከወያኔ በማይተናነስ መልኩ የሌላውን ተቃዋሚ ፓርቲ አካሄድ ሲተቹ ብሎም በአደባባይ ሲውቃወሙ ይታያሉ ። ይህ አካሄድ ከወያኔ ምን ይለያቸዋል ። ተቃዋሚ ነኝ ብለህ የምታስብ ከሆነ በወሬ የሚመጣ ምንም አይነት ለውጥ ስለሌለ  የሌሎችን  ተቃዋሚዎችን አካሄድ ከመተቸት  የራስን ብቻ ስራ መስራት ተገቢ ነው ።

Ethiopian man shot dead by Saudi police

Saudi police killed an Ethiopian migrant who tried to flee arrest, authorities said Wednesday, as a crackdown on foreigners working illegally in the kingdom widens with more than 16,000 arrests.

The security sweep comes after seven months of warnings by Saudi Arabia's government, which has created a special task force of 1,200 Labor Ministry officials who are combing shops, construction sites, restaurants and businesses in search of foreign workers employed without proper permits.

Police have also erected checkpoints to enforce the kingdom's strict labor rules that make it virtually impossible to remain in the country without official sponsorship by an employer.

Residents said most shops have been closed since the sweep began Monday, with many of the country's migrants avoiding the streets where they face possible arrest. State-backed Saudi Gazette reported Wednesday that residents are already feeling the brunt of the everyday work the migrants provided, from ritual washings of corpses before burial to food delivery and bagging groceries.

Authorities say that since warnings were issued earlier this year, almost 7 million foreigners in Saudi Arabia corrected their paperwork to accurately reflect their occupation and workplace. The kingdom also issued more than 1 million final exit visas, which ban people from ever returning.

The Saudi-owned Asharq al-Awsat newspaper reported that authorities detained around 16,500 workers in the first 48 hours of the nationwide crackdown. The newspaper quoted Saudi officials as saying that nearly half of the migrants were arrested near the southern border with Yemen. Another 5,000 had been detained in Mecca, where some Muslims stay on illegally after pilgrimage. Less than 1,000 were detained in the main city of Riyadh.

A resident in the poorer neighborhood of el-Manhoufa in Riyadh told The Associated Press he saw police stopping people outside a mosque after prayers and arresting those who did not have the correct papers on them.

The statement Wednesday by Riyadh police chief Nasser el-Qahtani said security forces killed the African migrant worker in el-Manhoufa a day earlier when he and others tried to resist arrest. Those detained will eventually be deported.

The sweep is aimed largely at creating more job opportunities for the kingdom's own citizens, who comprise less than half of the country's work force.

High security checks in Bahir Dar

High security checks in Bahir Dar

ESAT News   November 1, 2013

Special high security checks have been underway for the past four days in Bahir Dar city. According to ESAT’s reporter, the cause for the random and unusual checking is unknown. Especially, yesterday, passengers have been forced to leave their vehicles and undergo security checks in the entrance and exit posts of the City’s doors.

Some residents say the government has been spreading rumours saying that “anti-peace elements” have entered the city while others say it was an attempt of causing fear among the residents. There are also people who are commenting that a similar kind of “concocted explosion” could occur in the city like those that took place in Bole Sub City, Addis Abeba, few weeks ago.

The residents also state that Federal Police officers are harassing them during the checking process. ESAT’s efforts to speak to the regional police officials were unsuccessful.

Speaking with regards to the recent explosion in Addis Abeba, Yihdego Seyoum, Commissioner of the Addis Abeba Police, had said that the Ethiopian government had no reason to joke and do a drama on its citizens.

The Commissioner also criticised politicians who say the explosion was “concocted”.

Recent leaks by Wikileaks revealed that the American Embassy in Addis Abeba believed that the Ethiopian government deliberately coordinated terror attacks.

Meanwhile, a Bajaj driver has been viciously killed in Bahir Dar city. The eyes of the victim, who is a resident of Kebele 7, were gouged out and he was severely attacked when he was found days after his death. The City’s Police Commission has not spoken out regarding the death so far.

Wednesday, November 6, 2013

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል

በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን።

በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን።

ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው።

በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው።

ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው።

ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!