Friday, December 19, 2014

ሰበር ዜና (Update) – አምስት ሰዎች ሲቆስሉ ሁለት ሞተዋል፣ የባህርዳር ህዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን በማሰማት ላይ ነው

(ነገረ-ኢትዮጵያ) ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ከተማ ላይ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ጥረት እያደረ ቢሆንም ህዝቡ በብዛት ተቃውሞውን እየተቀላቀለ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች አምስት ያህል ወጣቶች እንደቆሰሉ ተገልጾአል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከቀበሌ 10 አባይ ማዶ ያለው መንገድ ተቃውሞውን በተቀላቀለው ህዝብ የተዘጋ ሲሆን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ የቀበሌ 8፣ 10ና 11 ነዋሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል፡፡ የአፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አካባቢም በርካታ ህዝብ የተገኘ ቢሆንም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት የሉም እንደተባሉ ገልጸውልናል፡፡
————————-
(ነገረ-ኢትዮጵያ) ባህርዳር ከተማ ውስጥ 04 ቀበሌ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የጥምቀት ታቦት ማደሪያ ለባለሀብት ይሰጣል መባሉን ተከትሎ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን በማሰማት ላይ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጸዋል፡፡Protest in Bahirdar, Ethiopia
ምንጮቹ እንደገለጹት እጅግ በርካታ ህዝብ አደባባይ የወጣ ሲሆን፣ ሰልፈኞቹ በእምነታቸው እየተደረገባቸው የሚገኙትን ጣልቃ ገብነቶችና ሌሎቹንም ስርዓቱ እየፈጠራቸው የሚገኙትን ችግሮች የሚቃወሙ መፈክሮች እያሰሙ ይገኛሉ፡፡
የአማራ ክልል አስተዳደር የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያን የተጠራው ተቃውሞ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከታቦት ማደሪያው 9 ሜትር ገብቶ መንገድ እንዲሰራ እንዲሁም ቀሪው ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች እንዲሰጥ አስተዳደሩ ማዘዙን ተከትሎ ታቦት ማደሪያውን ከነገ ህዳር 10/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሊፈርስ እንደነበር መረጃው የደረሳት ቤተ ክርስቲያን ለህዝበ ክርስቲያኑ አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፏ ታውቋል፡፡
ህዝቡም ‹‹በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገናኝተን በእግዚያብሄር ስም በአስቸኳይ ጠርተንዎታል›› በሚል በቀረበለት ጥሪ መሰረት ዛሬ ጠዋት ተቃውሞውን የጀመረ ሲሆን አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ተገልጾአል፡፡ ህዝቡ ቀበሌ 10 በሚገኘው አዲሱ ምክር ቤት እንዲሁም በዚሁ ቀበሌ በሚገኘው የቀድሞው ምክር ቤት በመገኘት ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲሱ ምክር ቤት ተገኝቶ ተቃውሞውን እያሰማ የሚገኘውን ህዝብ በኃይል ለመበተን ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

Thursday, December 18, 2014

ህወሃት በመንግስት ወጪ 40ኛ አመቱን ለማክበር ሸርጉድ እያለ ነው

በከፍተኛ ዝግጅት ይከበራል የተባለው የህወሃት 40ኛ አመት በአል ወጪ የሚሸፈነው ከመንግስት ካዝና መሆኑ በአባል ድርጅቶች መካከል መነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን የሚናገሩት የኢህአዴግ ምንጮች፣ ከመንግስት ካዝና ለሚወጣው ገንዘብ የተሰጠው ሰበብ  ገጽታ ግንባታ የሚል መሆኑን ገልጸዋል።
ህወሃት በአሉን ከድርጅቱ ካዝና በተለይም የአገሪቱን ሲሶ ሃብት ከተቆጣጠረው ኢፈርት ካዝና መጠቀም እየቻለ፣ ወጪውን መንግስት እንዲሸፍነው ማስደረጉ ለብዙዎቹ አልተዋጠላቸውም። አጠቃላይ ዝግጀቱ ምን ያክል ገንዘብ እንደሚያስወጣ እስካሁን በግልጽ ባይታወቅም፣ እስካሁን እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች ወጪውን እየሸፈኑ ያሉት የክልሉ መንግስትና የፌደራሉ መንግስት በጋራ ነው።
የካቲት 11 ቀን የሚከበረውን የህወሃት ቀን አስመልክቶ የተመረጡ ጋዜጠኞችና አርቲስቶችን በመንግስት ወጪ  ታህሳስ 13 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ትግራይ ይጓዛሉ። ህወሃት ከበዓሉ አስቀድሞ የትግራይ ክልልን ለማስጎብኘት ያሰበው ከወዲሁ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ስራ ለማከናወን እንዲመቸው በማሰብ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
 ኢሳት ዜና 

Wednesday, December 17, 2014

ዓይን አጥፊው የዓይን “ማከሚያ ቤት”

የህንድ የአይን ህክምና ማዕከል (OIA) በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለፀ
indian eye center
* “ብዙ ብር ከፍለን የዓይን ብርሃናችንን አጥተን ተመልሰናል” – ታካሚዎች 
* ከመነሻው የማዕከሉ አደረጃጀት አዋጁን የሚቃረን ነው – የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ
* ማዕከሉ በየዓመቱ የሚታደስ የህክምና አገልግሎት ፈቃድ አልተሰጠውም
ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የተሻለ የአይን ህክምና ለመስጠት፣ ለኢትዮጵያውያን ሀኪሞች የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያደርግና በዘርፉ ምርምርና ጥናት እንዲያካሂድ ታስቦ በዘውዲቱ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የተገነባው የህንድ የአይን ህክምና ማዕከል በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ታካሚዎች እንደተናገሩት በማዕከሉ በተሰጣቸው ህክምና ሳቢያ የዓይን ብርሃናቸውን አጥተዋል፡፡ በማዕከሉ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት የተሟላ የህክምና ቁሳቁስ፣ በዘርፉ በቂ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎችና ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ ሳያሟላ የሚሰጠው ጥራቱን ያልጠበቀ አገልግሎት ዜጎችን ለአይነ ስውርነት፣ ለተጋነነ ወጪና ለእንግልት እየዳረገ ነው፡፡
ማዕከሉ ለኢትዮጵያውያን ሃኪሞች የቴክኖሎጂ ሽግግር ያደርጋል ቢባልም ሁሉም የህክምና ቁልፍ ቦታዎች በህንዳዊያን በመያዛቸው እቅዱ እንዳልተሳካና ከስምምነት ውጪ በተጋነነ የደሞዝ ክፍያ ምዝበራ እንደሚፈፀም ተገልጿል፡፡
የአይን ህክምና ማዕከሉ ከተለያዩ ተቋማት ገምጋሚ ተመድቦለት የአንድ ዓመት ተኩል የስራ አፈፃፀሙ በተገመገመበት ወቅት ከግንባታው ጀምሮ ችግር እንዳለበት በመግለፅ ችግሩ ሳይቀረፍ የትኛውም የመንግስት አካል ለማዕከሉ ድጋፍ እንዳያደርግ ገምጋሚዎቹ ቢያስጠነቅቁም ፈቃድ አግኝቶ ደረጃ ሳይወጣለት፣ ጥራቱን ሳይጠብቅና ባለሙያና መሳሪያ ሳያሟላ ወደ ስራመግባቱ ተገቢ አልነበረም ተብሏል፡፡ መንግስት በተቋሙ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንዳለበትም ገምጋሚዎችና የማዕከሉ ሰራተኞች አሳስበዋል፡፡
ከመነሻው የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑ እየታወቀ የጤና ማዕከሉ፣ ሜዲካል ዳይሬክተር፣ ስራ አስኪያጁ፣ የሃብት ማፈላለጉና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊነቶች በውጭ ዜጎች መያዛቸው የፌደራል በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ አዋጅን ፍፁም የሚቃረን ነው ያሉት በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የጤና ፕሮጀክት ክትትል እና ድጋፍ ባለሙያ አቶ ጥላሁን አለሙ፤ ማዕከሉ በርካታ  ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉበት መሆኑንና የተጠቃሚን አቅም ያላገናዘበ፣ ባለሙያ ያልተሳተፈበትና በከተማ አስተዳደሩ ስልጣን በተሰጠው አካል ያልፀደቀ የክፍያ ተመን በማውጣት የተጋነነ ክፍያ የሚያስከፍል፣ በጤና ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው ብለዋል፡፡
የጤና ማዕከሉ ካሉበት ችግሮች ውስጥ የማዕከሉ የውጭ ሞያተኞች የጤና የስራ ፈቃድ ከመውሰዳቸው በፊት ከኦፕሬሽን ጀምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን እየሰጡ እንደሆኑ የገምጋሚዎቹ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም ማዕከሉ በየዓመቱ የሚታደስ የህክምና አገልግሎት ፈቃድ ያልተሰጠው ህገ-ወጥ ተቋም ነው ሲልም ሪፖርቱ ገልጿል፡፡
አቶ ወ/ፃዲቅ ማናዬ ይባላሉ፤ የ62 ዓመት አዛውንት ናቸው፡፡
አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ኦሎምፒያ አካባቢ ይኖራሉ፡፡ “አምና መጋቢት ወር ላይ ዓይኔን ታምሜ ወደ OIA የሄድኩት ህንዶቹ ጥሩ ህክምና ይሰጣሉ ተብዬ ነው ያሉት አዛውንቱ፤ በመጀመሪያ የሞራ ግርዶሽ ነው ተብለው 4250 ብር ከፍለው የቀዶ ህክምና ማድረጋቸውን ይናገራሉ፡፡ “በመጨረሻ እራሳቸው በፈጠሩት ስህተት ከአንድም ሶስት ጊዜ ኦፕራሲዮን ተደርጌ ሬቲናዬን አበላሹት” የሚሉት አዛውንቱ፤ ከዚያም በኋላ ያለ ምንም መድሃኒትና እርዳታ ዝም ብለው እንዲጠብቁ በመደረጋቸው ቀኝ አይናቸው ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ማየት እንደተሳናቸው በምሬት ገልፀዋል፡፡
ያለ ምንም መድሃኒት ለሁለት ወር ቀጠሮ ሰጥተውኝ ስመለስ “ያንተ የሬቲና ችግር ነው አሉኝ” የሚሉት አቶ ወ/ፃዲቅ፤ “የሬቲና ችግር ከሆነ ለምን ሶስት ጊዜ አደንዝዛችሁ ሞራ ነው በማለት ኦፕሬሽን አደረጋችሁኝ” በማለት ህንዳዊ ሀኪሞቹን መጠየቃቸውን፤ ነገር ግን ከማመናጨቅ ውጭ ቀና ምላሽ ማጣታቸውን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ “ወደ ሌላ ህክምና ለመሄድ ሪፈር ፃፉልኝ፤ አለበለዚያም እናንተ ጋር ያደረግሁትን አጠቃላይ የህክምና መረጃ ስጡኝ” ብለው መጠየቃቸውን የሚናገሩት አዛውንቱ፤ የምናውቀው ነገር የለም የፈለጋችሁበት ሄዳችሁ ክሰሱን፤ ምላሽ እንሰጣለን” በማለት አመናጭቀው እንደሸኟቸውና እይታቸውን አጥተው ቤት ውስጥ ከተቀመጡ 10 ወር እንዳለፋቸው ገልፀው፤ ማንበብና መፃፍ ሁሉ እንደተሳናቸው ተናግረዋል፡፡
በዚሁ የአይን ህክምና ማዕከል የህክምና ስህተት ተፈጽሞብኛል ያሉት የ65 ዓመቱ አዛውንት አቶ ኮሬ ወ/ማርያም፤ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ለህክምና ሲሄዱ የሞራ ግርዶሽ ነው ተብለው አምስት ሺህ ብር ከፍለው ኦፕሬሽን መደረጋቸውን አስታውሰው፣ በ15ኛው ቀን አይናቸው ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ ወደ ማዕከሉ ተመልሰው መሄዳቸውን ይናገራሉ፡፡
“አይኔ መጥፋቱን እያወቁ አንድም ጠብታ ሳያዙልኝ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል እንድሄድ ነገሩኝ” የሚሉት አዛውንቱ፤ ምኒልክ ሆስፒታል ሁለት ሶስት ጊዜ ቢመላለሱም ምንም እርዳታ ሳያገኙ ሲኤምሲ አትሌቲክስ ህንፃ ላይ በሚገኘው “ብሩህ ቪዥን” ክሊኒክ እንዲታከሙ እንደተነገራቸው ገልፀዋል፡፡
India-Eye-Care-Center
ማዕከሉ በመጋቢት ወር በኢህአዴግ ባለሥልጣናት ተመርቆ ሲከፈት
“ብሩህ ቪዥን አንዴ በመርፌ፣ ሌላ ጊዜ በመሳሪያ ይታይ እያሉ ለተጨማሪ 7ሺህ ብር ወጪ ተዳርጌያለሁ” ያሉት እኚህ ታካሚ፤ አራት ወር እንደሆናቸውና አይናቸውንም አጥተው፣ 12 ሺህ ብራቸውን በማፍሰስ ለተጨማሪ ችግር በመዳረጋቸው ተጨማሪ ወጪ እንደሚጠብቃቸው ተናግረዋል፡፡
“የተሟላ መሳሪያ ሳይኖር፣ በዘርፉ የሰለጠነ በቂ ሀኪም በሌለበት የህክምና ማዕከሉ እንዴት ፈቃድ ተሰጠው?” ሲሉ የሚጠይቁት አቶ ኮሬ፤ “መንግስት ለዜጎቹ የሚጨነቅ ከሆነ እንዲህ አይነቶቹን ተቋማትና ሰራተኞች ለፍርድ ማቅረብና ኢንሹራንስ ለተጎጂዎች እንዲከፍሉ፣ ከዚያም በአስቸኳይ ማዕከሉን ዘግቶ ከጥፋታቸው ማስቆም ያስፈልጋል” በማለት ብለዋል፡፡
ወደ ህክምና ማዕከሉ ከመሄዳቸው አስቀድሞ መኪና መንዳት ይችሉ እንደነበር የተናገሩት  የ66 ዓመቱ አዛውንት፤ ከአንድ ዓመት በፊት ህክምና መጀመራቸውን ይናገራሉ፡፡ “ችግሩ የሞራ ግርዶሽ ነው፤ ይህን በቀላሉ እንገፍልሃለን ብለው ኦፕሬሽን ካደረጉኝ በኋላ ጭራሽ አይኔ ማየት አቁሞ ቤት ተቀምጫለሁ” ሲሉ በምሬት የገጠማቸውን ችግር ገልፀዋል፡፡
“ከዚያ በኋላ አይኔ ጠፋ ብዬ በተከታታይ ብመላለስም ምንም መፍትሄ ሳላገኝ እስካሁን አለሁ” ያሉት አዛውንቱ፤ “እርግጥ እኔ የካርድ 40 ብር ከመክፈል በስተቀር ያወጣሁት ወጪ የለም፤ ምክንያቱም የነፃ ህክምና ወረቀት አፅፌ ነበር የሄድኩት” ብለዋል፡፡ እሳቸው ደግሞ የጨረር ህክምና ተደርጐላቸውም መሻሻል እንዳላሳየ ገልፀው ወደ ምኒልክ ሆስፒታል ሪፈር እንደተፃፈላቸው ይናገራሉ፡፡ “ሚኒልክ ሆስፒታል ሄጄ ስመረመር አይንህ ተበላሽቷል፤ የማየትም ተስፋ የለውም ብለው መለሱኝ” የሚሉት ተጎጂው፤ ተስፋ ቆርጠውና እይታቸውን ተነጥቀው ቤት መቀመጣቸውን ጠቅሰው ወዴት አቤት እንደሚባል ግራ እንደገባቸው፤ ይህን ላድርግ ቢሉም አቅምና የእይታ ችግር እንደማይፈቅድላቸው ተናግረዋል – “እግዜር ይክሰሳቸው” ሲሉም በምሬት ተናግረዋል፡፡
በአንድ የመንግስት የሚዲያ ተቋም ውስጥ የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ለህክምና ወደ ማዕከሉ መሄዱንና መቶ ብር ከፍሎ ካርድ ማውጣቱን ይናገራል፡፡ እንደ ሌሎቹ የሞራ ግርዶሽ ችግር ሳይሆን ረጅም ርቀት እይታ ችግር እንዳለበት ተነግሮት፤ ለህክምናው መዘጋጀቱን ነገር ግን በመሃል ወረፋ ሲጠብቅ ስለ ማዕከሉ መጥፎ መጥፎ ነገሮች ሲነገሩ በመስማቱ ህክምናውን እንዳቋረጠ ይናገራል፡፡ “ችግሬን ከድጡ ወደ ማጡ አላደርግም ብዬ ህክምናውን አቁሜ ይልቁንም ክሊኒኩ ውስጥ አለ የተባለውን አሻጥር እየመረመርኩ ነው” ያለው ጋዜጠኛው፤ በማዕከሉ ከሚሰሩ ኢትዮጵያውያን የህክምና ባለሙያዎች የሰማው እጅግ የሚዘገንን ህገ-ወጥ አሰራር አይነ ስውር ከመሆን ያተረፈውን አምላኩን እንዲያመሰግን እንዳደረገው አጫውቶኛል፡፡
ማዕከሉ ከዚህ በተጨማሪም በብልሹ አሰራሮች መተብተቡን የግምገማ ሪፖርቶቹ ይጠቁማሉ፡፡ በሪፖርቱ ከተጠቀሱት ችግሮች መካከል የፋይናንስ፣ የግዢና የሰው ሃብት አስተዳደር ማኑዋሎች የሌሉትና ለምዝበራ የተመቻቸ መሆኑ፣ ማዕከሉ በአዋጅ ኃላፊነትና ስልጣን በተሰጠው ደረጃ መዳቢ አካል ደረጃ ያልወጣለት መሆኑና በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የተባለው ማዕከል ምንም አይነት የላብራቶሪ፣ የጠቅላላ ሰመመን፣ የድንገተኛና መሰል የአገልግሎት ክፍሎች ያልተሟሉለት መሆኑ ይገኙበታል፡፡
በሃገር ውስጥ ሊሟሉ የሚችሉ የቢሮ ቁሳቁሶች በከፍተኛና ወጪ ከውጭ ከመግባታቸው በተጨማሪ ተፈራራሚ አካላት ቢያንስ በፅሁፍ እንዲያውቁት አለመደረጉ የተጠቆመ ሲሆን የፕሮጀክት ክለሳ ሳይደረግ ከእቅድ ውጭ ለሆነ ግንባታ 634ሺ 986 ዶላር እንዲሁም ለህክምና መሳሪያና ለቢሮ ቁሳቁስ 315ሺ 171 ከ37 ሳንቲም በድምሩ 950ሺ 157 ከ37 ዶላር ያለ አግባብ ወጪ መደረጉን የገምጋሚው ኤክስፐርት ሪፖርት አመልክቷል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ማዕከሉ ሄደን የተለያዩ ህንዳዊያን ሃኪሞችን ለማነጋገር የሞከርን ሲሆን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ወደ ህንድ በመሄዳቸው መረጃ ማግኘት የምንችለው እሳቸው ሲመለሱ ብቻ እንደሆነ ተገልፆልን ተመልሰናል፡፡ (ምንጭ: አዲስ አድማስ)

ቤኒሻንጉል ጉሙዝን ለመገንጠል የሽብርተኝነት ድርጊት ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩ ተከሰሱ

-የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማስተጓጐል ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተጠቁሟል በታምሩ ጽጌ
በኤርትራ መንግሥት ድጋፍ ኤርትራ ውስጥ የተለያዩ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድና በመዘጋጀት፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ለመገንጠል የሽብርተኝነት ድርጊት ፈጽመዋል በሚል በተጠረጠሩ አሥር የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ታኅሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡
በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ተሰናድቶ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች አብዱልዋሀብ መኸዲ (በሌለበት)፣ አብዱራህማን ናስር (በሌለበት)፣ ኩርፊል ጅማ፣ ያሲር ጃባላ፣ ኢማም አብዱራዛቅ፣ ደፈአላ መሐመድ፣ አደም በደዊ፣ ሙድወኪል ከማል፣ አልፋዮድ በዳናና አዜን አህመድ ናቸው፡፡ 
ተጠርጣሪዎቹ በሰው ሕይወት፣ በአካልና በንብረት ላይ የተለያዩ ጉዳቶች ማድረሳቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ኅብረተሰቡን ለማስፈራራት፣ የአገሪቱን መሠረታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ ሕገ መንግሥታዊና ማኅበራዊ ተቋማትን ለማናጋትና ለማፈራረስ ራሱን የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ቤሕነን) ብሎ በሚጠራው በሽብር ተግባር ላይ በተሰማራ ድርጅት ውስጥ ሆነው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ክሱ ያብራራል፡፡ 
አብዱልዋሀብ መሀዲ የተባለው ተጠርጣሪ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ቤሕነን የሚባለውን ሕገወጥ ድርጅት በማቋቋምና በሊቀመንበርነት ከመምራቱም በተጨማሪ፣ ኤርትራ ውስጥ ሆኖ የተለያዩ የፖለቲካ ሥልጠናዎችንና የሽብር ተልዕኮዎችን ሲሰጥ መቆየቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡
ተጠርጣሪው ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ኤርትራ ውስጥ በሚገኘውና ‹‹ሀሆና›› በሚባለው ወታደራዊ ማሠልጠኛ በመግባት፣ ከሁለት እስከ ስድስት ወራት ሥልጠና መውሰዳቸው በክሱ ተገልጿል፡፡ የመሣሪያዎች አጠቃቀም፣ የወታደራዊ አካል ብቃትና የፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂ ማጥመድ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውንም ክሱ አክሏል፡፡ 
ተጠርጣሪዎቹ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ሸርቆሌና አልቤሮ በተባሉ አካባቢዎች በሚገኘው፣ ዱምድ አቤ ተብሎ በሚጠራ መንገድ ላይ ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎችን በማጥመዳቸው፣ ጥቅምት 26 ቀን 2006 ዓ.ም. 12 ሰዎችን ጭኖ ከሸርቆሌ ወደ አስቢሮ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ላይ የፍንዳታ ጉዳት በማድረስ ሦስት ሰዎች ወዲያውኑ እንዲሞቱና በዘጠኝ ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡
የክልሉን መንገዶች በማጥናትና ፈንጂዎችን በማጥመድ ከፍተኛ አደጋ እንዲደርስና የንፁኃን ሰዎች ሕይወት እንዲጠፋ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ፣ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎችን በማስቆም፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላትንና ሌሎች ሲቪል ሰዎችን መግደላቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ 
ተጠርጣሪዎቹ ከሁለተኛው ተጠርጣሪ አብዱራህማን ናስር ከሚኖርበት ሰሜን ሱዳን በኩል በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ደማዚን አሻራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመገናኘት፣ የተለያዩ የሽብር ተልዕኮ ማስፈጸሚያ የጦር መሣሪያዎችን፣ ለምግብና የተለያዩ ወጪዎች የሚሆን ገንዘብ ይቀባበሉ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡ 
ተጠርጣሪዎቹ በሚያዚያ ወር 2006 ዓ.ም. ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚወሰደውን መንገድ በድንጋይ በመዝጋት፣ ከአሶሳ ከተማ ወደ ግድቡ 28 ሰዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ የመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪን በማስቆምና በማስወረድ፣ በአካባቢው በነበረ ጫካ ውስጥ በማስገባት፣ ሦስተኛው ተጠርጣሪ በጥይት ደብድቦ እንደገደላቸውና የያዙትን ገንዘብ እንደወሰዱ ክሱ ይገልጻል፡፡ ተሽከርካሪውንም ከራሱ ቤንዚን ስበው በማርከፍከፍ እንዳቃጠሉት ክሱ ያብራራል፡፡ 
ተጠርጣሪዎቹ የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም ቆርጠው በመነሳታቸው በተለያዩ ጊዜያት መንገድ በመዝጋትና ተሽከርካሪዎችን በማስቆም፣ ተሳፋሪዎችን በጥይት ደብድበው በመግደል፣ እንዲሁም የተወሰኑ ሰዎችን እጃቸውን ወደኋላ በማሰር፣ በድንጋይና በዱላ በመደብደብና አንገታቸውን በመቆልመም የግድያ ወንጀል መፈጸማቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ 
የመከላከያ ሠራዊት በደረሰው ጥቆማ መሠረት ባደረገው ከበባ ለ30 ደቂቃ ያህል ተኩስ ከተለዋወጡ በኋላ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተገድለው፣ ሌሎቹ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በተጠረጠሩበት የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡    

Monday, December 15, 2014

ጀግኖችን እያሰብን የበኩላችንን እንወጣ!! በመስዋዕትነት ነፃነት ይረጋገጣል፤ ሰላም ይሰፍናል። (በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ)

መምሀር የኔሰው ገብሬ በዳውሮ ከተማ ነዋሪና ትጉህ መምህር ነበር። እንደማንኛውም አገር ወዳድና የወገን ተቆርቋሪ እርሱም የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓተ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ገደብ የለሽ ሰቆቃ መቀበል ባለመቻሉ ፣ በአንፃሩ በተቃውሞ አቋሙን በአደባባይ የሚገልጽና ይህ እኩይ ድርጊት እንዲቆም ታግሎ ለማታገል በጽናት ስለቆመ የሥርዓቱ ሰለባ ሆነ። እስራቱና እንግልቱ አልበቃ ብሎ ከሥራ መደቡም ተገለለ ። በዚያው ላይ ፍትህ ለማግኘት የሚያስብ ሕሊናና የሚሰማ ጆሮ እንደሌለ ተረድቶ ለአሰቃዩትም ለአጠቃላይ ሕዝቡም መራር መልእክት ያስታላልፋል ብሎ ያሰበውን መስዋዕትነት መርጦ ራሱን በጋዝ አንድዶ ሕዳር 1 ቀን 2004 ዓ.ም መስዋዕት ሆነ። ይህ ተግባሩ ቀደም ሲል ለአገር አንድነትና ለሕዝብ ሉዓላዊነት ፣ ለመምህሩ መብትና ጥቅም መከበር ሲታገሉ መስዋዕት የሆኑትን፣ በእስራት የማቀቁትን፣ ከእናት አገራቸው ተሰድደው በባዕድ አገር ያለውዴታቸው የእንግልትና የናፍቆት ኑሮ የሚገፉትን መምህራን፣ የሙያ ማህበሩ የኢመማ መሪዎችን፣ ደጋፊዎቻቸውንና ተባባሪዎቻቸውንም የሚያስመካ አንጸባራቂ መስዋዕትነት ሆኖ አልፏል። መቼም ቢሆን ነፃነት ያለመስዋዕትነት ተገኝቶ አያውቅም። በሕዝቡ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ የሚገኘውን ጨካኙን፣ ዘረኛውን፣ ግፈኛውን፣ —-  [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–
 

Sunday, December 14, 2014

ለሀገር ነጻነት የወጣቱ ተሳትፎ ቀጣይነት ይኑረው!

Dec 4, 2014
ከ1997 ምርጫ ማግስት ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጣቶችና በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ዜጎች ለሀገራቸው የዲሞክራሲ መብት መከበር እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ ላቅ እያለ መምጣቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህን ተከትሎ ዛሬ ወጣቱ የወላጆቻችን ደምጽ ይከበር፣ ኢትዮጵያዊነት በዘረኝነት አይፈተንም! ነጻነት ዳቦ አይደለም! እስራትና ግድያ በኢትዮጵያ ይቁም! የወያኔ አገዛዝ በቃን! በሚሉ በበርካታ ወጣቶች ጩኸት የወያኔ ሹማምንትና አገልጋዮቹ ላይ የፈጠረው ድንጋጤ ወጣቱን ሽብርተኛ አስደርጎታል።
ወጣቶች ህዝብን አስተባብረው ለተቃውሞ በማሳደም የወያኔን ዘረኝነት በመቃወም ረገድ የተለያዩ ዘዴዎችን ከሌሎች የነጻነት አቢዎት እንቅስቃሴ በመማር እምቢተኝነትን በማሳየት ጅማሮ ላይ ናቸው። ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ የተጀመረው የእምቢተኝነት ዘመቻ በሚቀጥለው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ይቀጣጠል ዘንድ ወጣቱ ሃላፊነት አለበት። ሀገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው መራራ ትግል ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርበታል። አባቶቻችን የውጪ ሀገራትን ወራሪዎች ወራራ ለመመከት ሁሉም ሰው የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ ያደረጉት ጥሪ አሁንም ላይ ይሰራል።
ለራሳችን ክብር፣ አንድነት፣ ለሀገር ነጻነትና ህልውና መከበር ኢትዮጵያዊ እምቢተኝነት የሚጀምረው ከትንሽ ነው። ህወሃት በጠላትነት የፈረጃችሁ የዛሬ ወጣቶች የሆናችሁ ዘመን በሚፈቅድላችሁ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በመላው ሀገሪቱ ወረቀት ከመበትን አንስቶ ሌሎች ይትግል ስልቶችን ተጠቀሙ። ኢትዮጵያ ሀገራችሁ በአንድ ጠባብ ዘረኛ ቡድን መዳፍ ውስጥ ማልቀስ ከጀመረች ሰነባብታለች። ዜጎቿ የግለሰብም ሆነ የቡድን መብታቸው ተረግጦ በባርነት እየተገዙ ነው። ጉልበታቸውና ሀብታቸው እየተመዘበረ ሲሆን፤ ለነጻነት፣ ለዲምክራሲና ለፍትህ የጮኹ ሁሉ ሽብርተኛ ተብለው ወደ ማጎሪያ እየተወረወሩ ነው።
ስለዚህ ስለ ሀገራችን፣ ስለራሳችን የግልም ሆነ የቡድን ጥቅም ስንል በሀገሪቱ የትኛውም ከፍል የተጀመረውን የእምቢ አልገዛም ባይነት እንቅስቃሴ እንደግፍ፣ እንሳተፍ! በባህርዳር የተጀመረውን የወጣቶች እንቅስቃሴን አድንቀን ይህ ተነሳሽነት በሌላውም የሀገሪቱ ክፍል መቀጠል ያለበት ነው።
ይህን በማድረግ ወደ ትግሉ በመቀላቀል ካልተሳተፍን በስተቀር ትግላችን አንድ እርምጃ ወደፊት ፈቀቅ ማድረግ እንደማንችል ግንቦት 7 ያምናል። ስለሆነም ሁሉም አካላት በያለበት በየሚኖርበት፣ በሚችለው አቅሙ ሁሉ ወደትግሉ በንቃት ተሳተፍ! አብረን ታግለን ነጻነታችንን እናረጋግጥ! ለኢትዮጵያ ትንሳኤ፣ የነጻነት አዋጆች ነጋሪ፣ አብሳሪ ትውልዶች እንሆን ዘንድ ሳንታክት እንታገል ዘንድ ወቅቱ የሚጠይቀው ጥሪ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Saturday, December 13, 2014

ለለውጥ የጓጓው ወጣት ዱር ቤቴን ምርጫው ማድረጉ የኢትዮጵያ ሁኔታ የግድ የሚለው ነው

ለለውጥ የጓጔው ወጣት ዱር ቤቴን ምርጫው ማድረጉ የኢትዮጵያ ሁኔታ የግድ የሚለው ነው::በኢትዮጵያ ሌሎችን የአፍሪካ አገሮች የሚጎበኛቸው ህዝባዊ ነውጥ በከተማ ብቻ ይከሰት ይሆን ? ወያኔ ወጣቱን አጋር አልባ ሆኖ ሲያገኝው ያለርህራሄ እየቀጠቀጠው ነው።የህወሃት መሩን መንግስት ጭካኔ የተመለከተ ከከተማ የተሻለ አማራጭ ያስባል ማለት ያስደፍራል:: መንገዱም ዛሬ የሰጠ ነው:: አንድ ዘዴ ካልሰራ ሌላ ዘዴ መሞከሩ:ወይም ዘዴዎችን በጣምራ መሞክሩ የግድ ነው:: ለወያኔ የሳት እራት ከመሆን ከገጠር እሳት ጭሮ ወደከተማ መግባትን በአንክሮ ማሰብ የግድ ይላል። 
2015 የወያኔ የጭንቀትና የፖለቲካ ውጥረት የሚጦዝበት ዓመት ሊሆን ይችላል። ይህ እንዲሆን ደግሞ የሚኬድበትን መንገድ መፈተሽን ይጠይቃል:: ወያኔ ከስልጣኔ የራቀ በመሆኑ ለህዝባዊ የከተማ እምቢተኝነት ያለው ምላሽ ዘግናኝ ጭካኔ ነው። ህወሃት መሩ መንግስት  ይሄው ዛሬ ሌሎች አገሮች እንደሰማነው: እንዳየነው ያለ ህዝባዊ አመጽ ሳይጎረብጠው እንዳሻው ሲረግጥ ሲዘርፍ ሲያስር ይሄው ሁለት አሰርት ዓመታት አለፉ። እካሁን ድረስ ደግሞ እስሩ ድብደባውና ግድያው ካገር ገፍቶ ማሰደዱ ሰርቶ ነበር:: ዛሬ ለየት የሚለው እነዚህ ሁሉ እኩይ ተግባራት የሚሰጡት ውጤት ህዝብን ከማስፈራራት ይልቅ አደፋፋሪ መሆናቸው እየጨመረ መሄዱ ነው። ህዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያ አይቀሬ ነው:: ይህን ደግሞ የመንግስቱ ተችዎች ብቻ ሳይሆኑ ራሱ ህወሃት መሩ መንግስት ያመነው ነው። 2015 የወያኔ ጭንቀትና የፖለቲካ ውጥረት የሚጦዝበት ዓመት ሊሆን የሚችለው የከተማው ህዝባዊ አመጽ በገጠር በመሳሪያ የታጀበ አመጽ ጋር ሲዋሀድ ብቻ ነው። ህወሃት መሩ መንግስት እንቅልፍ የሚያጣበትም አቢይ ጉዳይም ይህ ብቻ ነው:: ለፈረንጆች ያመነው “ያለመረጋጋት አደጋ” የሚለው ይህኑ ነው::
ያለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ያመጡት: ለህዝቡ የፈየዱት ምንም የለም:: በኢትዮጵያ በአፍሪካም በጥቅል ምርጫ የለሽ ዲሞክራሲ ዛሬ ምንም አላመጣም ።ዛሬ የህወሃት አብዮታዊ ዲሞክራሲም አሰልቺ የሞኝ ዘፈን ነው:: በስልጣን መባለግ:ስርቆት:ጭካኔ:ተንኮል የተስፋፋባት ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች እንደሆነ ለመናገር የሚክብድ አይደለም። በሴኒጋል ቡርኪና ፋሶ ቶጎ እና ቻድን ይዞ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ህዝብ በቃ ብሎ መነሳቱ በኢትዮጵያም ጊዜውን ብቻ የሚቆጥር ትዕይንት ያደርገዋል:: ሆኖም በእነዚህ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች እንደሆነው በኢትዮጵያም በተመሳሳይ መልኩ አመጹ ተነስቶ  የህወሃት መሩ መንግስት ፍጻሜ ላይሆን ይችላል? የህወሃት መሩ መንግስት የከተማ አመጽን ለመግታት ሀይልና ብቃት ልምድ ጨምሮ አለው። ወታደራዊ ሀይሉንም በአስተዳደር ተብትቦ ባይነቍራኛ የሚጠብቀው ነው:: በግብጽና በቡኪና ፋሶ እንደሆነው ወታደራዊ ሀይሉ ለከተማው ህዝባዊ አመጽ ቶሎ የሚደርስ ደጀን መሆኑን ለመናገር ዛሬ አስቸጋሪ ነው:: ወታደራዊ ሀይሉንም እንደ ህዝቡ ተመሯልና ብረት ያነሱ ሀይሎች አስተማማኝ ደጀኖች ከሆኑት ግን ልቡ ክህዝቡ መሆኑን መናገር ፈጽሞ አይቸግርም:: ለምን ለሀብታም ጄኔራል ብሎ ይሙት? የሌባ ጎሬ ለሆነው ለህወሀት ይሙት ? መሞት ለአገርና ለራስ ክብር ነው::
ዛሬ በአዲስ አበባ የሚታየው ህዝባዊ አመጽ የመሪዎቹንና የተከታዮቹን ጀግንነት አስደናቂ ቢያደርገውም ትርፉ ለወያኔ ነው:: የወጣውን ሀይል ይቀጠቅጣል ያልወጣውን ሀይል ያስፈራራል። ይህ ሁኔታ ግን እንዲህ ሊቀለበስ ይችላል:: በገጠር የታጠቁ ሀይሎች በጥቃቅን ድሎች መጀመሪያ ኋላም አቢይ ድሎች ተቀዳጅተው ሲበረቱ ለከተማ አመጽ ደጀን ይሆናሉ:: የመንግስት ሀይላትም እንደወትሮ መግደል ጊዜው ማብቃቱን ያስተውላሉ ወይም ተጠያቂነትን ማሰብ ይጀመር ይሆናል:: ይህ ሲሆን የህወሃት አብዮታዊ ዲሞክራሲም ሞትን ተቃረበ ማለት ነው። ደርግ የክተማ አመጽን ደምስሶ አስራሰባት ዓመት ስለገዛባት አገር ወያኔም\ህወሀት ከገጠር ወደ ከተማ ስለገባባት ኢትዮጵያ ስለሆነ ሃሳብ የምንለዋወጠው ይህን ማለት አይክብድም።አያከራክርም:: ጣሊያን ኢትዮጵያን በደፈረበት ዘመን ጣሊያን የተመረረው በገጠር ባሉ አርበኞች ነበር:: የውስጥ አርበኛው እየረዳ:: አዲስ አበባ በሳት ቀለበት ውስጥ ነበረች::  ለለውጥ የጓጔው ወጣት ዱር ቤቴን ምርጫው ማድረጉ የኢትዮጵያ ሁኔታ የግድ የሚለው ነው:: ፈረንጅ ለወያኔ የለገሰውን አድማ መበተኛ መሆን ማብቃት አለበት:: በፈረቃ በወያኔ መቀጥቀጥ ይብቃ:: ሌላ መንገድ ይታሰብ!
በአረብ አገራትና ክሳሃራ በታች በሚገኙ አገራት ሙስናው ፡የኑሮ ችግሩ፡በስልጣን ብልግናው፡ስራ አጥነቱ፡ ተስፋ ማጣቱ አይደለም አመጹን ያነነደደው እሳት ? ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ ባሰ እንጂ ተሻለው ብሎ የሚል ማን ነው? የህወሃት መሩ መንግስት ራሱ ተገንዝቦ ለፈረንጆች ባደባባይ አምኖአል። ይህን ራሱ ያመነውን የተናገሩ:የጻፉ ጋዜጠኞች ግን በእስር ይማቅቃሉ። የድንበር ጦርነቱ እና ረሀቡ ከሁለት አሰርት ዓመታት በላይ የተዳፈኑ እሳት ናቸው። ከሁለት አሰርት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ በጤና: በትምህርት: በቴክኖሎጂ እጅግ ኋላ መቅረትዋ በማስረጃ እየተደገፋ ተጽፏል። ኢትዮጵያ በሁሉም የድህነት መለኪያ ዝርዝር ትታወቃለች:: ከወያኔ መወገድ ማግስት ለሚከተለው መዘጋጀት ያገር ወዳዱ ሁሉ ከፍ ያለ ግዴታ ነው::ከባዱም ፈተናም ይህ ነው።
በኢትዮጵያ ይህ መምጣቱን የምንጠብቀው ለውጥ ብቻ ሳይሆን በለውጡ ማግስት የሚክተለው ግዝፈት ያለው ችግር ነው አሳሳቢው:: እነመለስ የተራቆተ መንግስት አልተረከቡም:: በጎሳ የተሸነሸነ አገር አልጠበቃቸውም። ለሽግግር የሚያግዝ የተማረ የሰው ሀይል አልቸገራቸውም።ስልጣንን መከታ አድርገው በሚሊዮን ያካበቱ አልነበሩም:: ከውጭም አይዟችሁ ያሉዋቸው ብዙ ነበሩ:: ሁሉም አልጋ ባልጋ ነበር። ትልሙ የወያኔን ስንብት እየደገሱ ሽግግሩ ከወዲሁ ማሰብና መዘጋጀት ነው::
ያለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ወደኋላ ሲስተዋሉ ለህወሃት መሩ መንግስት ባለስልጣኖችና ደጋፊዎቻቸው የተመቸ ኑሮ የመሰረቱባቸው ሀብት ያካበቱባቸው ዓመታት ናቸው። ክዚህ ምቾት በምርጫ አሰናብታቸዋለሁ በሰላም እሸኛቸዋለሁ የሚል ካለ ቅዠት ውስጥ ያለ: ሰለወያኔ ግፍ ያልሰማ ወይም ይቅርታ ጠያቂ ነው:: ወያኔን በከተማ ለክብሩ:ለነጻነቱ:ለሀይማኖቱ ላገሩ በማለት ተጋፍጦ ይገኛል። ኢትዮጵያ የዚህ ትውልድ ናት
ዛሬ በዚህ ርእስ ለመጸፍ እጅግ የሚያደፋፍረው አንድ ሰው አለኝ የሚለው የተለየ መረጃ ወይም የተንታኝነት ችሎታ ሳይሆን ራሱን ችሎ የህወሃት መሩ መንግስት ተግባሮች ናቸው። አንድ ትውልድ በክተማ እንዳለ ቀርቷል:: ዛሬ “ያ ትውልድ” እየተባለ የሚነገርለት። የደርግን የግፍ በትር እነመለስ በዱር አሳለፉት:: ዛሬም እሾህን በሾህ! በዚህ መነጋገር መልካም ነው::
ክቢላል አበጋዝ

Thursday, December 11, 2014

ግንቦት ሰባት ሆይ…. ከሄኖክ የሺጥላ

ውድ ወዳጆቼ ሆይ ፣ ዛሬ ተክሌን መሆን አምሮኛል ( ተክሌ ይሻውን ሳይሆን ተክለሚካዔል ሳህለ ማርያምን )። ልጅ ተክሌ መቼም እኔ’ነቴን ለምን ወሰድክብኝ እንደማትለኝ ነው ። እንኩዋን እኔነት ፣ የእኔነት መፈጠሪያ የሆነችውን ሀገርህን ወስደዋትስ የለ ።
የዛሬ ጽሁፌ የሚያጠነጥነው ትልቁንና እና ጠንካራውን ድርጅት ግንቦት ሰባትን ላይ ነው ። እንደውም ጽሁፌን ከማውጠንጠን ማነጣጠር ሳይሻል አይቀርም ( የታጠቀን እንዲያ ነው እንጂ !) ። እና የምወደውን ግንቦት ሰባት ፣ ባልሞትለት እንክዋ የምደማለት ግንቦት ሰባትን ፣ የኔ የምለውን ግንቦት ሰባት ፣ የ አንዳርጋቸውን ግንቦት ሰባት ፣ የብርሃኑ ነጋን ግንቦት ሰባት ፣ የዔፍሬም ማዴቦን ግንቦት ሰባት ፣ የአበበ ገላውን ግንቦት ሰባት ፣ አዎ ስለሱ ነው ።
andargachew
አንተ ግንቦት ሰባት ሆይ ፣ አንተን ካወቅኩበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ትቢት ትቢት ይለኛል ፣ ወያኔ ምን ለማስፈራራት ቢሞክር ፣ ነገራቸው ሁሉ ድንፋታ እንጂ አንዳች ፍርሃት ልቤን ይሁን ሆዴን ቅም አይለውም ፣ ስላንተ ሳስብ አባቱን ከሩቅ እንዳየ ህጻን እፈነድቅአለሁ ፣ ስምህ በክፉ ሲነሳ ፊቴ ደም ይለብሳል ፣ የባንክ ደብተሬ እንኩዋ ዜሮ እያሳየ ስላንተ ስሰማ ምን እንደሆነ ባላውቅም መንዝር መንዝር ይለኛል ፣ ዘርዝር ዘርዝር ይለኛል ፣ ያም ሆኖ አንዳርጋቸው ከታሰረ ወዲያ ላንተ ያለኝ ፍቅር ወደ ንዴት እየሄደ ነው ። ይሄም የሆነው አንዳርጋቸው በመያዙ ሳይሆን ፣ የአንዳርጋቸውን መያዝ ተከትሎ ይህ ነው የሚባል አጸፋዊ እርምጃ ባለመውሰድህ ነው ። ሰማያዊ እንኩዋ ነጭ እርግብ ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ ሰላም ሰላም እያለም ፣ እየተገፈተርም ቢሆን ሰልፍ ወጥቶዋል ፣ “የምንገለው ባይኖረንም የምንሞትለት ሕዝብ ግን አለን” ብሎ ይሄው እሳት ከጨበጠ ጋ በ እስክርቢቶ ትግሉን ሀ ብሎ ከጀመረ ቆየ ፣ አረ እንደውም እስክርቢቶ መግዣውን እኔም ተባብሬያለሁ ( በሱም በጣም ደስተኛ ነኝ ) ። ኢንጂነር ይልቃልን ሳስብ ማህታማ ጋንዲ ወይም ማርቲን ሉተር ኪንግ ትዝ አይሉኝም ፣ ምክንያቱ ደሞ፣ ወዳጄ ይልቃል እንደነሱ ጠንካራ አይሆን ይሆን ብዬ ስለማስብ ሳይሆን ፣ መሃተማ ጋንዲና ማርቲን ሉተር ኪንግ መስዋት የሆኑላቸው አይነት ሕዝብ ከጎኑ ስለሌለ ብቻ ። ይልቃል እና ጉዋደኞቹ እንደውም ከማህታማ ጋንዲም ሆነ ከ ማርቲን ሉተር ኪንግም ይበልጣሉ ፣ ለምን ቢባል ፣ የሚታገሉት ስርዓት ምን ያህል ጨካኝ እንደሆነ እያወቁት ትግሉ ውስጥ በአስር ጣታቸው እንደገቡበት ሳስብ ። የብረት ትግል የሚል ነገር ባያነሱም ግን ከብረት ትግል እኩል የሕይወት መስዋትነት እየከፈሉ እንደሆነ ስገነዘብ እውነት እውነት እልሀለው ደግሜ ደጋግሜ አከብራቸዋለሁ ። እንደውም አንዳንዴ ግር የሚለኝ ፣ እነሱ ለተገረፉት ፣ እነሱ ለተሰቃዩት ፣ ” በሰላማዊ ትግል ወያኔ ይወድቃል ብሎ ማስብ ዘበት ነው !” እያልኩ እኔ ራሴ አወራ ነበር ። ግን ቆይቶም ቢሆን የገባኝ ለካ ለሀገር ሲሉ መሞቱን ነው ” ሰላም ” ያሉት እንጂ ትግሉማ መች ሰላም አለው ብለህ ነው ። መቼም በደንብ እንደምታውቀው እኔ ” ወያኔ ባሩድ አሽትተን እንጂ ፣ እርግብ አሳይተን እናሸንፈዋለን ማለት ዘበት የሚመስለኝ ሰው ነኝ ” እንዴት ሸለምጥማጥን እርግብ ሆነህ ትቀርበዋለህ ?
ወደ አብይ ጥያቄዬ ስመጣ ስለ ትግሉ ሳስብ ሆድ ይብሰኛል ፣ መቼ ይሆን ጦርነቱ የሚጀመረው እያልኩ ከራሴ ጋ አወራለሁ ፣ በይበልጥ በግንቦት ሰባት ስም የተገደሉ ፣ የታሰሩ ፣ ከስራ የተፈናቀሉትን ሰዎች ሳስብ ፣ በጣም የዘገየህ ይመስለኛል ፣ ይሄ የኔ ብቻ ጥያቄ እና መብሰልሰል እንዳይመስልህ ፣ ያው እኔ ስለማልፈራ ነው ጥያቄውን የጠየቅኩት እንጂ አሁን አሁን የብዙ ወዳጆቼ ጥያቄ እየሆነ ነው ። መቼ ነው አዲስ አበባ ላይ የወያኔ ባለስልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ ሲባል የምንሰማው ? መቼ ነው የወያኔ ባለስልጣኖች ሲንማ-ራስ መቃም የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ከህዝብ ጋ መተራመስ የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ቀን የግንቦት ሰባትን አባላት እና ሌሎች ንጹሃን ሰዎችን ማዕከላዊ ወፌ ላላ ሲገርፍ የዋለ የ ወያኔ ባለስልጣን ማታ አንገቱ ተቆርጦ የምናየው ? መቼ ነው ? የክርስቶስ ዳግም መምጣት እንኩዋ እንዳንተ ውጊያ መጀመር በዙም አልጉዋ-ጉዋ-ንኝም !
መልሱን በድርጊት ትመልሱልኝ ዘንድ ከወገቤ ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ ።

Wednesday, December 10, 2014

የዓለም ባንክና አይኤምኤፍ መንግሥት ከምዕራብ የፋይናንስ ተቋማት እንዲበደር አሳሰቡ

የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ መንግሥት ለካፒታል ፕሮጀክቶች ከአንድ የገንዘብ ምንጭ ብቻ መበደር እንደሌለበትና ይልቁኑም ለምዕራብ የገንዘብ ተቋማት በሩን ክፍት ሊያደርግ እንደሚገባ ምክረ ሐሳብ ለገሱ፡፡
ሁለቱ ግዙፍ የገንዘብ ተቋማት በኅዳር ወር መጨረሻ ከዋሽንግተን ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ በርካታ የአውሮፓ ባንኮች የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች ብድር ለመስጠት ፍላጎት እያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን መንግሥት በቂ ድርድር በማድረግ የሚቀርብለትን ፋይናንስ መጠቀም ሲገባው፣ ፈጣን ምላሽ አለመስጠቱንና ከአንድ ምንጭ ብቻ መጠቀሙን (የቻይና መንግሥት) ደብዳቤው ጠቁሞ፣ አንድ የገንዘብ ምንጭ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉ ጉዳት እንዳለው ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
በአንፃሩ የጀርመን፣ የእስራኤልና የእንግሊዝ ባንኮች ለኢትዮጵያ ፋይናንስ ለማቅረብ ዝግጁ ቢሆኑም የመንግሥትን ትኩረት አለማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡
የሁለቱ የፋይናንስ ተቋማት ደብዳቤ መንግሥት በቅርቡ ቦንድ ለዓለም ገበያ ማቅረቡን መልካም ጅማሬ መሆኑን ጠቅሶ፣ ከዚህ በበለጠ ምዕራባዊ ባንኮችን ሊጠቀም እንደሚገባና አንድን የገንዘብ ምንጭ ብቻ መጠቀም ጉዳት ሊኖረው እንደሚችል ይገልጻል፡፡
ክሬዲት ስዊስ፣ በርክሌ፣ ጄፒ ሞርጋንና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የመሳሰሉ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋማት ለኢትዮጵያ መንግሥት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ለማቅረብ ፍላጎት አሳይተዋል፡፡ ሁለቱ የገንዘብ ተቋማት በኢትዮጵያ የፋይናንስ ግኝቶች ላይ ግምገማ ማካሄዳቸውን ገልጸው፣ የንግድና የካፒታል ፕሮጀክቶች ብድሮች ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በአንድ የገንዘብ ምንጭ ላይ ብቻ ያተኮሩ መሆናቸውን በግምገማቸው መረዳታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ተቋማቱ መንግሥት የዕዳ አስተዳደሩን መቀየጥ እንደሚኖርበት በጻፉት ደብዳቤ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ መንግሥት ለካፒታል ፕሮጀክት አብዛኛውን ብድር የሚያገኘው ከቻይና መንግሥት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከታዋቂ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዕውቅና እየተቸረው በመሆኑ፣ የምዕራብ የፋይናንስ ተቋማት ብድር ለማቅረብ ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፡ ነገር ግን ከቻይና ሲነፃፀር፣ የምዕራብ የፋይናንስ ተቋማት የወለድ ምጣኔ ከፍተኛ ስለሆነ መንግሥት ብዙም ትኩረት እንዳላደረገ ምንጮች ይናገራሉ፡፡
zehabesha.com

Tuesday, December 9, 2014

ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አቋም መግለጫ

ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ  ከተቋቋመበት አላማዎች አንዱና ዋነኛው በሃገራችን  በኢትዮጲያ ያለውን ኢፍትሃዊ የአንድ ዘር የበላይነት የሰፈነበትን አምባገነን  ስርሃት በማውገዝ እንዲሁም በመታገል ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጲያን ማለትም  የዜጎችን እኩልነት የተረጋገጠባት፣  የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ፣ የዜጎች ሰብአዊ መብት የተከበረባት ፣  የህግ የበላይነት የሰፈነባት፣ እንዲሁም  ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በኩል አይን የሚታይባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመገንባት የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል መደገፍና ብሎም በአጋርነት ሞቆም ነው፡፡
ስለሆነም ባሳለፍነው ሳምንት ማለትም ህዳር 27/28 የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የሃገሪቱ ህገ- መንግስት በሚፈቅደው መሰረት  ለሃያ አራት ሰአት የሚቆይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተው እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ሆኖም በማን አለብኝ ሃገሪቱን እንዳሻው የሚያደርግ ህውሃት(ኢህአዴግ)አሁን በህብረተሰቡ ዘንድ የተፈጠረውን የለውጥ ስሜት እንዲሁም ለዚህ ክስተት ምክኒያት ናቸው ያላቸውን የ9ኑ ፖርቲዎች ትብብር ከመቼውም በላይ ስላሰጋው ከላይ  በተጠቀሰው ቀን የአደባባይ የ24 ሰአት ሰልፍ እንዳይካሄድ የትብብሩን አምራሮችና አባላትን በማዋከብ ስራ በዝቶበት ሰንብቷል፡፡
በመጨረሻም በሰልፉ ላይ የተገኙ የ9ኙ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮችና አባሎችን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፍርሃት ባሸበረው ህውሃት (ኢህአዴግ)በጭካኔ ተደብድበዋል፣ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ተግዘው ታስረዋል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ  በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመገኝታቸው ብቻ ከጎዳና ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔዊ እርምጃ ሰለባ ሆነዋል፡፡ እስካሁንም በዚሁ ዘረኛና አረመኔያዊ አገዛዝ ቁጥራቸው ከ300 የሚበልጡ  ሰላማዊ ታጋዮች በእስር ቤት ታፍነውከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል ፡፡
ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ  አምባገነኑ ህውሃት(ኢህአዴግ) በሰላማዊ ታጋዮች እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊያሰሙ በወጡ ዜጎች ላይ የወሰደውን አረመኔያዊ እርምጃ በጥብቅ እያወገዘ የ9ኙ ፖርቲዎች ትብብር እያደረገ ያለውን እልህ አስጨራሽ ትግል በንቃት የሚከታተልና ከጎናችሁ መቆሙን እየገለጸ ለተጀመረው የነጻነት ትግል አጋርነቱን ይገልጻል፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ!!!!!
ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ !!

ከ5 ሚሊዮን የማያንሰው ዐማራ ዬት ደረሰ?

moresh-logoየትግሬ-ወያኔ ለ17 ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ23 ዓመታት ደግሞ በገዢነት ተፈናጦ በዐማራ ሕዝብ ባደረሰው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምን ያህል ንፁሃን ዐማሮች እንደተጨፈጨፉ የተለያዩ አስተያዬቶች ሲደመጡ ቆይተዋል። ሞረሽ ወገኔ ባደረገው ዝርዝር የሕዝብ ብዛት ቆጠራ ትንተና መሠረት ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ ደብዛቸው ከምድረ-ገፅ እንዲጠፉ የተደረጉት ዐማሮች ብዛት ከ5 ሚሊዮን እንደማያንስ ይጠቁማል። ይህ ምንን ያመለክታል? ከጥናቱ ውጤት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ጎልተው ይወጣሉ።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አገር አቀፍ ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ የተካሄደው በ1976 ዓ.ም. ነበር። በወቅቱ ኤርትራን እና የአሰብ አስተዳደርን ጨምሮ ጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 42,616,876 ያህል ነበር። በኤርትራ እና በአሰብ አስተዳደር ኗሪ የነበሩት ዜጎች ቁጥር ሲቀነስ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ሕዝብ ብዛት 39,868,572 ይሆናል። በወቅቱ በሕዝብ ብዛት አንደኛ የነበረው የኦሮሞ ነገድ ብዛቱም 12,387,664 ሲሆን፤ እንዲሁም ዐማራ በሁለተኛ ደረጃ 12,055,250 ያህል ተወላጆች ነበሯቸው። ስለሆነም በወቅቱ በሁለቱ ነገዶች ተወላጆች ብዛት መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት 332,414 ይሆናል ማለት ነው። የመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ከተደረገ ከ23 ዓመታት በኋላ፣ ማለትም በ1999 ዓ.ም. በተደረገው ሦሥተኛው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት ዐማራው ቁጥሩ በአዝጋሚ ሁኔታ ወደ 19,867,817 ሲጨምር የኦሮሞዎቹ ብዛት ግን ከእጥፍ በላይ አድጎ ወደ 25,488,344 ደርሷል። ስለዚህ በኦሮሞ እና ዐማራ ተወላጆች ብዛት መካከል ያለው የቁጥር ልዩነት 5,620,527 አሻቅቧል ማለት ነው። በዐማራው እና በኦሮሞው መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት ተመጣጣኝነት እንዳለ እንደተጠበቀ ይቀጥል ቢባል እንኳን ከ23 ዓመታት በኋላ ሊኖር የሚችለው ልዩነት ከ664,828 አይበልጥም። በመሆኑም ከ5ሚሊዮን የማያንሰውን ዐማራ ዬት እንዳደረሱት የሚያውቁት የትግሬ-ወያኔዎች እና ሎሌዎቻቸው ናቸው።
ባለፉት 23 ዓመታት ከ4,751,333 በላይ የዐማራ ነገድ ተወላጅ የጠፋው ወያኔ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር «የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው፤» « ዐማራን፣ የአማርኛ ቋንቋን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ማጥፋት አለብን!» ብለው የተሰለፉ በመሆናቸው የዐማራውን ነገድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመግደላቸው ነው። በግልፅ እንደሚታወቀው ወያኔ የዐማራውን ነገድ በሚከተሉት ሥልቶች አጥፍቷል። እያጠፋም ነው፥
  • በተለያዩ ሰበቦች በጅምላ በመግደል፦ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት፣ በአርማጭሆ፣ በራያ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ፣
  • በአሰቦት ገዳም፣ በአርባ ጉጉ፣ በወተር፣ በበደኖ በሌሎችም የሐረርጌ እና አርሲ አካባቢዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ የፈፀሙት የግፍ ጭፍጨፋ፤
  • በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በጅማ ያካሄዷቸው ዐማራን በጅምላ የመግደል ዘመቻዎች፤
  • ከ1983 -1987 ዓ.ም. ድረስ በሕወሓት ሠራዊት አማካይነት በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃም እና በጎንደር ኗሪ በሆኑ ዐማሮች ላይ የ«ሽፍታ ምንጠራ» እና «ብረት ማስፈታት» የሚሉ የሽፋን ዘመቻዎች በማካሄድ በፈፀሟቸው ጭፍጨፋዎች፤
  • ዐማራውን በተለያዩ ተፅዕኖዎች በማስፈራራት ዐማራነቱን ክዶ የሌላ የነገድ ማንነት እንዲቀበል በማስገደዳቸው፤
  • ዐማራውን እየለዩ ከሥራ በማባረር በርሃብ በመጨረሳቸው፤
  • «የመሬት ድልድል» በሚሉት እና ዐማራን «መሬት አልባ የትግሬ-ወያኔ ጭሰኛ» ለማድረግ በቀየሱት ፖሊሲ ዐማራው ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ተለይቶ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል አርሶ እና ሠርቶ እንዳይኖር በማድረጋቸው፤
  • ነባሩን የወባ መከላከያ ድርጅት ዘግቶ ድርጅቱን ወደ ትግራይ በማዛወር የዐማራውን ነገድ ተወላጆች የወባ መከላካያ አገልግሎት በማሳጣት አያሌ ዜጎች እንዲያልቁ በማድረጋቸው፣ በተለይም በጎጃም ሕዝብ ላይ ከ1985-1989 ዓ.ም. ያደረሱት እልቂት በምሣሌነት ይጠቀሣል፤
  • የዐማራውን ነገድ ተወላጆች በዘር ጠላትነት ፈርጀው የኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ቫይረስን በመርፌ በማስተላለፍ በገፍ እንዲያልቁ በማድረጋቸው፤
  • የዐማራውን ተወላጆች መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በመንፈግ በተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እንዲያልቁ በማድረጋቸው፤
  • በወሊድ ቁጥጥር ስም የነገዱን አባሎች መካንና ታማሚ በማድረጋቸው፤
  • ከዐማራ የጸዱ ክልሎችን ለመፍጠር በተያያዙት የዘር ማፅዳት ዘመቻ «ኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሔር-ብሔረሰቦች፣ ቤንሻንጉል-ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር እና ሶማሌ» ብለው በከለሏቸው «ባንቱስታን-መሠል» ግዛቶች ይኖሩ የነበሩት ዐማሮችን በግፍ እና በገፍ በማባረር፣ በመግደልና በመደብደብ ለተደራራቢ ችግሮች በማጋለጣቸው፤
ለዐማራው ነገድ ቁጥር መቀነስ ዋና እና ተያያዥ ምክንያቶች ናቸው። ስለሆነም ያለምንም ማወላወል የዐማራው ነገድ በትግሬ-ወያኔ በተከፈተበት የማያባራ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ሰለባ መሆኑን ትውልዱ ሊገነዘበው ይገባል።
በተለይ ለዐማራው ነገድ ተወላጆች እና ለሃቀኛ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ጥሪ፦
ይህን መረጃ በማባዛት ለዓለም ሕዝብ ባሉት የመገናኛ መሣሪያዎች በመጠቀም በማሰራጨት፣ ሆን ተብሎ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለተፈጸመበት የዐማራ ነገድ ድምፅ ልንሆን ይገባል። ለተበደሉ እና የመኖር ሰብአዊ መብት ለተነፈጋቸው ሰብአዊ ፍጡሮች ድምፅ መሆን ዘረኝነት ወይም ጠባብነት አይደለም። በመሆኑም የዐማራው ተወላጆች ብቻ ሣይሆኑ፤ ለሰብአዊነት የቆሙ ሁሉ ለዚህ ነገድ ድምፅ ከመሆን አልፈው፣ በኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ዓይነት የከፋ ወንጀል የሚፈፅሙትን ለፍትኅ አደባባይ ለማቅረብ ለተያያዝነው ትግል፥ የመረጃ፣ የምክር፣ የዕውቀት እና የገንዘብ ልገሣ እንድታደርጉልን በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችን እናቀርባለን።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ዳግም ትንሣዔ በቆራጥ ልጆቿ ተጋድሎ ዕውን ይሆናል!

በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን !!!

በአብዛኛው በወጣት ወንዶችና ሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነበት የዘጠኝ ፓርቲዎች ኅበረት፣ “ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የተሰኘ የአንድ ወር መርሀ ግብር አውጥቶ፤ ችግሮችን ተጋፍጦ አብዛኛውን ተግባራዊ አድርጓል። የመርሀ ግብሩ አቢይ አካል የነበረውና በህዳር 27 እና 28 ሊከናወን ታድቆ የነበረው የ24 ሰዓት የአደባባይ ተቃውሞ ግን በአገዛዙ የኃይል እርምጃ ምክንያት በታቀደው መንገድ ሊከናውን አልቻለም። የህወሓት ቅልብ የሆኑት ሲቪል የለበሱ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊስ በተቃውሞው ተሳታፊዎች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ጥቃት ፈጽመዋል።
ከጅምሩ፣ የፓርቲዎቹ ኅበረት የተቃውሞ ማሳወቂያ ደብዳቤውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስገባት የገጠመው ችግር የህወሓት አገዛዝ የመንግሥትን መዋቅር ለፓርቲ ሥራ፤ የመንግሥት ተቀጣሪዎችን ደግሞ እንደ ህወሓት አገልጋዮች የሚጠቀምባቸው መሆኑ አንዱ ማሳያ ሆኗል። ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ማሳወቅ የፈለጉት ፓርቲዎች ህወሓት የዘረጋውን አፋኝ ሥርዓት የሚታገሉ በመሆናቸው ብቻ ደብዳቤዓቸውን የሚቀበል እንኳን አጥተው ተጉላልተዋል። ለሰልፉ ቅስቀሳ ማድረግም በራሱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ወጣቶች ተንገላተዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል። ያም ሆኖ ውጣ ውረዶች ታልፈው ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ. ም. ደረሰ።
የኅበረቱ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ጥሪውን የሰማ ሕዝብ ወደ መስቀል አደባባይ ማምራት ሲጀምር ሲቪል የለበሱ የአገዛዙ ታጣቂዎች እና ፌደራል ፓሊሶች ከሰንደቅ ዓላማዎችና መፈክሮች ባለፈ አንዳች ነገር ያልያዙትን እድሜያቸው ከሃያዎች ያልዘለሉ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችን ደብድበዋል፤ ብዙዎቹም አፍነው በአሰቃቂ ሁኔታ እያንገላቱ ወደ እስር ቤቶች ወስደዋል። ወጣቶች ተወልደው ባደጉበት አገር፤ ስሜታቸውን በነፃነት ለመግለጽ በመድፈራቸው ብቻ በጭካኔ ተረግጠዋል፤ ተፈንክተዋል፤ እጅና እግሮቻቸው ተሰብሯል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህ የህወሓትን ፋሺስታዊ እርምጃ አጥብቆ ይቃወማል። ግንቦት 7፣ ህወሓት ከስልጣን እስካልተወገደ ድረስ እንዲህ ዓይነቱን ፋሺስታዊ ተግባር መፈፀሙን የማይተው እኩይ ኃይል እንደሆነ ያውቃል፤ በዚህም ምክንያት የትግላችን ግብ ህወሓትን ማስወገድና በምትኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መመሥረት መሆን ይኖርበታል ብሎ ያምናል፤ ለዚህም ይታገላል።
ግንቦት 7፣ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም. “መብቶቻችንን በህወሓት ዘረኛ አምባገነኖች አናስነጥቅም” በማለት አደባባይ የወጡ ወጣቶችን ጽናት ያደንቃል። ህወሓት የሚለውን ሳይሆን የይስሙላ ህጉ የፈቀደላቸውን ለማድረግ በመድፈራቸው በህወሓት የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የሚደረገውን ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት አራምደውታል።
እያንዳንዱ የፓለቲካ ድርጅት ከዚህ ኩነት የሚወስዳቸው ተጨማሪ ትምህርቶች ቢኖሩም የሚከተሉትን ነጥቦች ብዙዎችን ያስማማሉ ብለን እናምናለን።
1. ህወሓት በምንም ዓይነት ቢሆን የያዘውን ስልጣን ለሕዝብ ፈቃድ ማስገዛት አይፈልግም፤
2. ህወሓት አገራችን ወደ ትርምስ እየገፋት እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፤
3. ስልጣኑን የሚያሳጣው ከመሰለው እና አቅሙ እስካለው ድረስ ዘግናኝ እርምጃዎችን ከመውሰድ አይመለስም፤
ከህወሓት አገዛዝ መገላገል የሚቻለው ተገዶ ሲወገድ ብቻ ነው። ህወሓት እንዲወገድ ደግሞ የመጨቆኛ አቅሙ መዳከም ይኖርበታል። ህወሓትን የማስወገጃ አማራጭ መንገዶች ብዙ ሲሆኑ ተቀናጅተው ቢሠሩ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ ብለን እናምናለን፤ “ሁለገብ ትግል” የምንለው የትግል ስልት ጭብጥ ይህ ነው። “እምቢ ለነፃነቴ” ብሎ የተነሳ ሕዝብ ህወሓትን ምን ያህል እንደሚያስደነግጥ በተደጋጋሚ ታይቷል። ህዳር 27ን መንደርደሪያ አድርገን በመውሰድ ከዚህ በተሻለ ለተደራጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና አመጽ ራሳችን እናዘጋጅ።
በዚህ አጋጣሚ ግንቦት 7፣ ለመከላከያ ሠራዊት እና ፓሊስ አባላት ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ማድረግ ይሻል። የመከላከያ ሠራዊት እና ፓሊስ አባላት እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በህወሓት ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ የተበደላችሁ መሆኑን እናውቃለን። የህወሓት ሹማምንት ከሆኑ አዛዦቻችሁ መላቀቅና ራሳችሁን ነፃ የማውጣት ኃላፊነት የወደቀው በእናንተው በራሳችሁ ላይ ነው። ሠራዊቱ ራሱን በራሱ ነፃ ማውጣት ይኖርበታል። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ህወሓት መወገዱ የማይቀር በመሆኑ ሠራዊቱ ራሱን ነፃ አውጥቶ ከሕዝብ ጋር ካልወገደ እጣ ፈንታው የተሸነፈ ሠራዊት መሆን ነው። ከዚህ በላይ የሠራዊቱ አባል እየደበደበ ያለው የራሱን ልጅ፣ ወንድሙን ወይም እህቱን እንደሆነ ይወቅ። ይህ ወሳኝ ጊዜ ነው እያንዳንዱ የሠራዊቱ አባል በግል ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ሊሰማው ይገባል።
በሁሉም ዓይነት የትግል ዘርፎች የኢትዮጵያ ወጣቶች በስፋት እየተቀላቀሉ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው። ጊዜው የለውጥ ነው። የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተደጋግፈው እንዲሄዱ መደረግ ያለበት ወቅት ላይ ነን። በህዳር 27 ቀን በህወሓት ቅልብ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊሶች አማካይነት የደረሰው ጉዳትና የፈሰሰው ደም ለፍትህና ለነፃነት የተከፈለ ዋጋ ነው። ህመማችሁ ህመማችን፤ ትግላችሁ ትግላችን ነው። የተለያዩ መንገዶች ወደ ነፃነት አደባባይ እያመሩ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Monday, December 8, 2014

የህወሃት ምርጫ የህዝብ መከራ!

ህወሃቶች እኛ ከሌለን ይህችን አገር እንበትናታለን፤ ይህችን አገር የምንሰብር እኛ የምንጠግን እኛ እያሉ እንደሚያሟርቱ ሰምተናል። እኛ የቀረፅነው ፖሊስ ከሚቀየር ሞታችንን እንመርጣለን እያሉ ማቅራራታቸውም ከህዝብ የተሰወረ ነገር አይደለም። የህወሃት ፖሊሲ የሚቀየረው በመቃብርችን ላይ ነው የሚል የማይናወፅ አቋማቸው መቼም ቢሆን በሠለጠነ መንገድ በውይይትና በድርድር እንደማይቀየር ደጋግመው አሳይተውናል። ህወሃቶችን በሠለጠነ መንገድ ተደራድሮ እና ሰጥቶ በመቀበል መርህ ለለውጥ አዘጋጃለሁ ማለት ከእባብ የእርግብ እንቁላል እንደመመኘት ያህል ነው። ከእባብ የእርግብን ዘር የሚጠብቅ ማን ነው?
እንግዲህ ህወሃቶች ይህን የመሰለ የከረረ አቋም ይዘው ምርጫ ለምን ያደርጋሉ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል። ይሄ ህወሃቶች ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ራዕይ የሌላቸው ከመሆን የሚመነጭ ነው። ድርጅቱ ራዕይ አልባ የሆነው ደግሞ በህወሃት ውስጥ የተሰባሰቡ ግለሰቦች ራዕይ አልባ በመሆናቸው ነው። ህወሃቶች የሚኖሩለትም ሆነ የሚሞቱለት ቁም ነገር ከመብልና መጠጥ የዘለለ አይደለም። ህወሃቶች ራዕይ ቢኖራቸው ኑሮ በታሪክ የሚያስወቅሳቸውንና የህዝቡን ፍቅር የሚያሳጣቸውን እኩይ ተግባራት ባልፈፀሙ ነበር። ራዕይ የሌላቸው በመሆኑ ለሚፈፅሙት ወንጀል ሁሉ ገደብ እንዳይኖራቸው ሆኑ። ራዕይ ያለው ሰውም ሆነ ድርጅት እኔ ብቻ አይልም። ራዕይ የሰነቀ ድርጅትም ሆነ ሰው ከራሱ ክበብ አልፎ ሌላው እንደምን ሁኖ በሠላም እና በደስታ እንደሚኖር ያስባል እንጂ ዕለት ዕለት ደም በማፍሰስ አይኖርም።
ህወሃት በምርጫ ስልጣኑን እንደማይለቅ ለራሱ የማለ ድርጅት ነው። እዚህ መሃላ ላይ ያደረሰው ደግሞ እስከ ዛሬ የፈፀማቸው ወንጀሎቹ ናቸው።የጨበጠውን ስልጣን በምርጫ ቢለቅ ነገ የሚከተለውን ጠንቅቆ ያውቃል። ትላንት ያፈሰሱት የንፁሃን ደም ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እየጮኸ ነው። ዘርፈው የገነቡት ህንፃ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ቆመው ሌብነታቸውን እየመሰከሩባቸው ነው። በልማት ሥም ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተዘርፎ የተደራጀው የንግድ ተቋም በኢትዮጵያ ህዝብ ወዝና ደም ታጥኖ እንዳማረበት አለ። ህወሃት የኢትዮጵያ የህዝብ ጠላት ሆኖ ራሱን ያቆመ ቡድን በመሆኑ በሰላማዊ እና በሰለጠን መንገድ የያዘውን ሥልጣን ለህዝብ አይለቅም።
እንግዲህ ምን ይሻላል ?
ህወሃቶች ኑና እንወዳደር ብለዋል። እነዚህ ቡድኖች ኑና እንወዳደር ሲሉ እነርሱ የብረት ቦክስ ጨብጠው፤ ሌሎቹ ደግሞ ሌጣቸውን ሁነው ያለ በቂ ታዛቢ እንዲፎካከሯቸው ወስነው ነው። እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ሁነንም ቢሆን የምንወዳደረው ለነፃነት መሆን ይኖርበታል። ከነፃነት በመለስ ያለው ማንኛውም ዓይነት የምርጫ ውጤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ዝሪፊያ፤ ዘረኝነት፤ እሥራት እና ግድያ ያስቆማል የሚል ዕምነት በማንም ዘንድ ያለ አይመስለንም። በምርጫ ውድድር የምናተርፈው የህግ የበላይነት፤ እኩልነት እና ነፃነት ካልሆነ ተጎጂው ሰፊው ህዝብ ይሆናል።
ህወሃት የብረት ቦክስ ጨብጦ እኛ ደግሞ ሌጣችንን ሁነን መወዳደር ፍትሃዊ አይደለም በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ ያሉት ወገኖችም የህዝብን መሠረታዊ ፍላጎት ለሟሟላት አስፈላጊ የሆነው ነፃነት ዋነኛው ግባቸው መሆን ስለሚኖርበት ይመስለናል። ወደ ውድድር ከመግባታችን በፊት ህወሃት የብረት ቦክሱን ያውልቅ፤ የመወዳደሪያ መድረኩም እኩል ይሁን ማለታቸው የሚሰማ ቢኖር ፍትሃዊ ጥያቄ ነው።የህወሃትን የብረት ቦክስ ለማስወለቅ መሥዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውም ለነፃነት የሚከፈል ዋጋ ይሆናል። ከህወሃት ጭካኔና ድንቁርና ስንነሳ በዚህ መንገድ የሚሄዱት የሚከፍሉት መሥዋዕትነት ከባድ እንደሚሆን እንጠብቃለን። ግን ደግሞ ነፃነት ያለ መሥዋዕትነት እንደማይገኝ ሌላው ቀርቶ ነፃነትን የማያውቁት ህወሃቶች ያውቃሉ። በማንኛውም መልኩ ከህወሃቶች ጋር አገት ለአንገት ተናንቀው በአገር ቤት ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ድርጅቶች ልበ ሙሉነታቸውን እጅግ አድርገን እናደንቃለን። እምቢ ለነፃነቴ፤ እምቢ ለክብሬ፤ እምቢ ለህወሃቶች ቀይ መስመር ማለት ይሄ እንጂ ሌላ አይደለም። እንግዲህ ዘረኞቹና ዘራፊዎቹ ቡድኖች ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት መቀነስ የሚቻልበትን መንገድ ማሰብ ተገቢ ይሆናል። ህዝቡ በልዩ ልዩ ሰንሰለት የታሠረ በመሆኑም በሚፈለገው መጠን ወጥቶ የትግሉ አካል ካልሆነም ተስፋ መቁረጥ አይገባም።በተጀመረው ላይ ይበልጥ እያጠናከሩና እየጨመሩ እየተካሄደ ያለውን ትግል መቀጠል ምርጫ የሌለው ሥራ ነው።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገር ቤት ሁነው ከጭካኔ በቀር ሌላ ዕውቀት ከሌላቸው ህወሃቶች ጋር በትግል ላይ ያሉ ድርጅቶችን ያደንቃል። ያመስግንማል። በርቱ ከማለት በቀር የምንለው ሌላ የለንም።
እኛ የጀመርነውን ሁለ ግብ ትግል እያጠናከርነው ነው። የአገራችንን ውርደት፤ የወገኖቻችንን ጉስቁልና እያየን ዝም ብንል እርግማን ይሁንብን ያሉ ወጣቶች የአያቶቻቸውን ጋሻና ጦር አንስተዋል። እናቶችም ልጆቻቸውን መርቀው ፋኖ ተሠማራ ብለዋል። ሌሎች ደግሞ የኋላ ደጀን ሁነው ሳያቅማሙ ቁመዋል። ብዙ ባለሙያዎች ለአገራቸው የሚከፈልውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጀተዋል።
እንግዲህ የጀመርነውን ትግል የሚያስቆመን ምድራዊ ኃይል የለም። የህወሃት የመረጃ መረብ ይበጣጠሳል። የጦር ኃይሉ ከጥቂት ዘረኞችና ሌቦች ይልቅ ወገኑን እንደሚመርጥ በየቀኑ የሚደርሱን መረጃዎች ያሳዩናል። የከተማው ህዝብ ህወሃቶችን አክ እንትፍ ካላቸው ብዙ ዘመን ሁኖታል። የገጠሩም ህዝብ የህወሃት ዋሻ የመሆኑ ነገር አብቅቷል። ይሄ ሁሉ የእኛ አቅማችን ነው። ይሄን አቅም አደራጅተንና ሥራ አሲይዘን አገራችንን ነፃ የምናወጣበት ግዜ ሩቅ አይደለም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !



    ከኢቲቪ ዋና ሥራአስኪያጅነት በአቅም ማነስ ተሰናብተው ለማካካሻ ወደ ኢትዮጽያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተመደቡት አቶ ዘርዓይ አስገዶም በብሮድካስት ባለስልጣን የህትመት ድርጅቶች የሚገቡት አስገዳደጅ ውል በማዘጋጀት በግዴታ በማስፈረም ላይ መሆናቸው ተሰማ፡፡

    -ባለስልጣኑ አሳታሚዎች ዓመታዊ የንግድ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ ወደንግድ ሚኒስቴር ሲሄዱ በየዓመቱ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ የሚገደዱ ሲሆን የሙያ ብቃቱን ለማግኘት ባለፉት ወራት ወደብሮድካስት ባለሰልጣን የሄዱ አሳታሚዎች ያልጠበቁትን ግዴታ እነዲገቡ የሚቃወሙ ከሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት እንደማይሰጣቸው በተነገራቸው መሠረት አብዛኛዎቹ ተገደው ፈርመዋል፡፡
    በንግድ ምዝገባ ፈቃድ መስጫ መደብ ቁጥር 89 ሺ 510 የጋዜጣና መጽሔት አሳታሚ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚሰጣቸው ሰዎች ከሚፈርሙዋቸው ግዴታዎች መካከል ” የተሟላ የሥራ ሪከርድ እና ሰነዶች አደራጅቼ እይዛለሁ፣ ለምርመራ ሲፈለግም ለባለሰልጣኑም ሆነ ለሚመለከታቸው ሕጋዊ አካል የማቀርብ መሆኔን አረገጋግጣለሁ”  የሚል ይገኝበታል፡፡ የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነጻነት አዋጁ ቁጥር 590/2000 አክብሬ አስራለሁ የሚልም ተከታይ አስገዳጅ ውል ውስጥ ሰፍሮአል፡፡
    አሳታሚዎች በተለይ “ሰነድ አሳያለሁ፣ ሪከርድ እይዛለሁ” የሚለው አስገዳጅ አንቀጽ ከባለስልጣኑ ሥልጣን ውጪ የሆነና የፕሬስ ነጻነትን የሚጻረር መሆኑን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ አሳታሚዎቹ በሥራ ላይ ያለ አዋጅ አክብሮ መሥራት የሁሉም ዜጋ ግዴታ መሆኑ እየታወቀ እንደገና በውል አከብራለሁ የሚል አስገዳጅ ፊርማ ለምን እንደተቀመጠ ግራ እንደገባቸው፣ ምናልባት አሳታሚዎች ተሸማቀው በጋዜጣና መጽሔት ይዘቶቻቸውን ምንም ዓይነት የተቃውሞ ጽሑፍ እንዳያስተናግዱ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ፡፡
    በዚሁ አስገዳጅ ውል አንቀጽ 9 ላይ «ከባለለስልጣኑ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ስወስድ የመረጥኩትን ይዘት ከባለለስልጣኑ ዕውቅና ውጪ ለውጥ ባደርግ እና የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቱን መሰረት የህትመት ሥራዬን ባላከናውን የተሰጠኝ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ሊሰረዝብኝ እንደሚገባ ተስማምቼ ይህን የውል ግዴታ መግባቴን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ» የሚልም ሰፍሯል፡፡ ይህ አንቀጽ ምናልባትም እነ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የመሳሰሉ ጋዜጠኞች አንዱ ሕትመት ሲዘጋባቸው በሌላ ህትመት ብቅ የማለታቸው ልምድ ሌሎችም እንዳይከተሉት  ለመዝጋት ሆን ተብሎ የተቀመጠ ሊሆን እንደሚችል ጉዳዩን የተከታተሉ ወገኖች ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
    የመንግስትን ኢፍትሃዊ አሰራሮችን በድፍረት በመዘገብ የሚታወቁት ጋዜጦች ከመንግስት በሚደርስባቸው ጫና እንዲዘጉ መደረጉ ይታወቃል። በርካታ ጋዜጠኞች በእስር ላይ ሲገኙ ብዙዎቹ ደግሞ ወደ ጎረቤት አገሮች ተሰደዋል።
     ኢሳት ዜና

    Friday, December 5, 2014

    የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በፖሊስ ተከብቦ አደረ

    ምንነቱ የማይታወቅ ወረቀት ሲበተን አድሯል

    የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በፖሊስ ተከብቦ ማደሩንና አባላት ከውጭ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለአዳር ሰልፉ ቅስቀሳ ዝግጅት ቢሮ ያደሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አመራሮችና አባላቱ እራት በልተው ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሲመለሱ ቢሮው በፖሊስ ተከብቦ እንዳገኙትና ወደ ውስጥ እንዳይገቡ እንደተከለከሉ በቦታው የነበሩት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ገልጸዋል፡፡ 

    አመራሮችና አባላቱ ፖሊስ ከ200 ሜትር ርቀት ውጭ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ጽ/ቤት መጠጋት እንደማይችል ቢከራከሩም ፖሊሶቹ ‹‹መመሪያ ተሰጥቶናል፤ አንሄድም!›› ማለታቸው ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ከፖሊስ ጋር ሲከራከሩ የአካባቢው ህዝብ በመውጣቱ ፖሊሶቹ ፓርቲው ጽ/ቤት እንደራቁ ታውቋል፡፡

    በሌላ በኩል ከውጭ ወደ ቢሮ ከሚመጡበት ወቅት የፓርቲው ቢሮ አካባቢ ምንነቱ ያልታወቀ ወረቀት ተበትኖ እንዳገኙና እነሱ ሲደርሱ ፖሊሶቹ እንዳነሱት የፓርቲው የምክር ቤት አባል ወጣት እየሩስ ተስፋው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡

    Thursday, December 4, 2014

    ፀረ-ኢትዮጵያዊውና ዘረኛው ወያኔ በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስም አይነግድም!

    ኮለምበስ፣ ኦሃዮ – ፀረ-ኢትዮጵያዊውና ዘረኛው ወያኔ በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስም አይነግድም!

    December 3, 2014
    መርሐ አንድነት የኢትዮጵያውያን ሲቪክ ማህበር በኮለምበስ፣ ኦሃዮ

    Click here for PDF

    የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ቅጥረኛ የሆነው ፀረ-ኢትዮጵያዊውና ቅኝ-ገዥው ወያኔ ባሕር ማዶ ተሻግሮ በሃገረ አሜሪካ ኮለምበስ ኦሃዮ “በስሜን አሜሪካ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች Tigray People Front, TPLFየባሕል ክብረ በዓል” በሚል ስም እሑድ ኅዳር 28 ቀን 2007 ዓ/ም ( Sunday, December 7, 2014 ) ከቀኑ 1:00pm ጀምሮ በሃያት ረጀንሲ ሆቴል (Hyatt Regency Hotel @ 350 North High Street, Columbus, OH 43215) ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛል። ለዚህ በዓል መሰናዶ፤ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የወያኔ ኢምባሲ የበላይ መሪ በመሆን፤ በአካባቢያችን ያሉትን የለየላቸው ከሃዲዎችና የባንዳ ልጆችና የልጅ ልጆች በአስተባባሪነት በማሰለፍ ነው።
    ለአለፉት 23 ዓመታት ሃገራችንን ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር በማዋል የፖለቲካውን ኃይል፣ የኢኮኖሚውን ዘርፍ፣ የማህበራዊ አውታሩን፤ የወታደራዊ ተቋሙንና የደኅንነቱን መረብ በሙሉ የተቆጣጠረው ፀረ-ኢትዮጵያዊውና ዘረኛው ወያኔ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የባሕል ክብረ በዓል ለማክበር የኅሊና ብቃት አለው ወይ?
    1. ማን ሆነና ነው ብሔር ብሔረሰቦችን እርስ በእርሳቸው ለያይቶና ከፋፍሎ የሚያስጨራርሰው?
    2. ማን ሆነና ነው ብሔር ብሔረሰቦችን በሃይማኖት ከፋፍሎ የሚያወዛግበውና የሚያዋጋው?
    3. ማን ሆነና ነው ወገናችን አማራውን፣ ኦሮሞውን፣ ሱማሊውን፣ አኝዋኩን፣ አፋሩን ወዘተ… እየጨፈጨፈ የምድር ሲዖል እያሳየ የዘር ማጽዳት ዘመቻ የሚያካሂደው?
    4. ማን ሆነና ነው በቅርብ ጊዜ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩትን አማራዎች ሃብትና ንብረታቸውን እያዘረፈ፣ ቤታቸውን እያቃጠለና እየገደለ ከሃገራችን ውጡ እያለ ከጉራፈርዳ፣ ከቤኒሻንጉል-ጉሙዝ፣ ከጋምቤላ ወዘተ.. ያፈናቀለውና ያባረረው?
    5. ማን ሆነና ነው ለቀንደኛ ደንበር-ዘለል ተስፋፊና ዘራፊ ሃገሮችና ኩባኒያዎች ለም ድንግል መሬቶቻችንን በመሸጥ በመቶ ሺህዎች የሚገመቱትን የደቡብ ኢትዮጵያና የጋምቤላ ብሔር ብሔረሰቦችን ከቀያቸው በማፈናቀል ሃገራችንን ለከፍተኛ አደጋ ያጋለጠው?
    6. ማን ሆነና ነው ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብት ክምችት ያለውን የሃገራችንን ዳር-ድንበር ለም መሬት ለሱዳን የሽጠው?
    7. ማን ሆነና ነው የብሔር ብሔረሰቦችን የጋራ ማህበራዊና ባሕላዊ እሴቶቻቸውንና አብሮነታቸውን የሸረሸረውና ለማጥፋት ተንኮልንና ሴራ የሚሸርበው?
    8. ማን ሆነና ነው ርካሽና አስነዋሪ የባእድ ባሕሎች በብሔር ብሔረሰቦቻችን ላይ እንዲስፋፋ ያደረገው?
    9. ማን ሆነና ነው በሺህዎች የሚቆጠሩትን ወገኖቻችንን በብሔር ማንነታቸው እየወነጀለ ወደ ወህኒ የሚወረውረው?
    10. ማን ሆነና ነው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ቁጥር አንድ አጀንዳውን አንግቦ ከደደቢት፣ ትግራይ የተነሳው?
    ይህን ሁሉ ግድያ፣ ግፍ፣ መከራ፣ በደልና ሰቆቃ በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ላይ የሚፈጽመው ፀረ-ኢትዮጵያዊውና ዘረኛው ወያኔ አይደለምን? አዎ ነው። ስለዚህ፣ እኛ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ልጆችም በነፍስ ገዳያችን ድግስ አንገኝም። በታላቅ ቆራጥነት በነፍስ ገዳያችን ላይ ሕዝባዊ ትግሉን እናጧጥፋለን እንጅ።
    ስለዚህ፣ በኮለምበስ ከተማና በአካባቢው ከተሞች፤ እንዲሁም በአጎራባች ስቴቶች የምትገኙ ሃገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን፤ ዘረኛውና ጎጠኛው ወያኔ እሑድ ኅዳር 28 ቀን 2007 ዓ/ም ( Sunday, December 7, 2014 ) ከቀኑ 1:00pm ጀምሮ ኮለምበስ ኦሃዮ በሚገኘው ሃያት ረጀንሲ ሆቴል ( Hyatt Regency Hotel @ 350 North High Street, Columbus, OH 43215) በጠራው ስብሰባ ላይ እንዳትገኙ፤ ወራሪውንና ፋሽስቱን ወያኔ ሲፋለሙ በታላቅ ጀግንነት በተሰውት የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሱማሊ፣ የአኝዋክ፣ የአፋር ወዘተ… የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ልጆች ስም ሃገራዊ ጥርያችንን እናስተላልፋለን። ሆኖም ግን፣ ይህን ሕዝባዊ ጥሪ ባለመቀበል በዚህ የወያኔ ስብሰባ የምትገቡ፤ የተሰውትን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ልጆች አጥንት ረግጣችሁ እንደገባችሁ እወቁት። እኛም እንደ እናንተ ያለውን ሆድ-አደር ባንዳ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ የምናጋልጥ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን።
    የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት በትግላችን ይመሠረታል!
    ፀረ-ኢትዮጵያዊውና ቅኝ-ገዥው ወያኔ በሕዝባዊ ክንዳችን ይደመሰሳል!
    ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
    መርሐ አንድነት የኢትዮጵያውያን


      ሲቪክ ማህበር በኮለምበስ፣ ኦሃዮ

      Monday, December 1, 2014

      ከ40 በላይ የአንድነት አባላትና አመራሮች በቃሊቲ እስር ቤት ታገቱ

      Nov 29, 2014 (በኤልያስ ገብሩ)
      የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃን ጨምሮ ከአርባ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ታገቱ፡፡
      አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪ ቃል ከህዳር 14 ጀምሮ እያካሄደያለው የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ አካል የሆነውን የህሊና እስረኞችን የመጎብኘት መርሀ-ግብር ለመሳተፍ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ያቀኑት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃ እና የፓርቲው የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶነገሰ ተፋረደኝን ጨምሮ 40 የአንድነት ፓርቲ አባላት ለግዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሰበብ በእስር ቤቱ ግዜያዊ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡
      አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪቃል በዚህ ሳምንት እያካሄደ ያለው ንቅናቄ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ትኩረት ማግኘቱ ገዢውን ቡድን ማስቆጣቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
      ዘግይቶ የደረሰን ዜና እንዳመለክተው ከሆነ ደግሞ; የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፈረደኝ፣ ንዋይ ገበየሁ፣ ዳንኤል ሙላትና አቶ ብርሐኑና ትግስት ክራውን ሆቴል አካባቢ አሁንም ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገለጹ፡፡
      ስማቸው ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች የታሰሩ የህሊና እስረኞችን ለመጠየቅ ወደቃሊቲ አምርተው ከነበሩት ሰዎች መካከል ይገኛሉ፡፡

      ተማሪዎች፣ መምህራን እና የተቋማት ፕሬዚዳንቶች ለአመጽ ተነሱ!

      ዘረኛውና አምባገነኑ የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከላትነት ለይቶ የማያይ ስለመሆኑ በተቋማቱ ውስጥ የሚደረጉ ተግባራት ማረጋገጫዎች ናቸው። ለዚህ ተግባሩ በሰነድ ደረጃ መቅረብ ከሚችሉት የቅርብ ጊዜ ማስረጃዎች ዋነኛው በህዳር 2007 ዓ.ም. በሥራ ላይ የዋለው “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል” የተሰኘው በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላለፈው ሰነድ ነው። ይህ ሰነድ፣ የህወሓት አሳፋሪ የትምህርት ፓሊሲ ባፈጠጠ መልኩ የተገለፀበት፤ የኢፌዴሪ መንግሥት ተብሎ በሚጠራው የህወሓት አገዛዝ ተቋም እና በህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲ መካከል ለይምሰል እንኳን ልዩነት አለመኖሩ በግላጭ የሚታይበት ሰነድ በመሆኑ በዚህ ርዕሰ አንቀሳችን በስፋት ልንዳስሰው ወስነናል።
      ሰነዱ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ መርዙን መርጨት የሚጀምረው ገና በመግቢያው ስለማንዋሉ አስፈላጊነት ሲገልጽ ነው። ማንዋሉ “ከምንም በላይየብጥብጥና የሁከት መንስኤ የሆነውን ተማሪ በኢህአዴግ አመራር አባላት እየታገዙ ለመያዝ የሚያስችል ነው” በማለት ህወሓት ተማሪውን የሚመለከተው “ከምንም በላይ በብጥብጥ መንስኤነት” መሆኑ፤ ለዚህ መድሀኒቱ ደግሞ ተማሪውን በኢህአዴግ አመራር አባላት “መያዝ” መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ይገልፃል። ቀጥሎም “በምርጫው ሊፈጠር የሚችለውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሁከትና ብጥብጥ ለማስቆም በማደራጀት መረጃ ለመጥለፍ አመችነቱ የላቀ እንደሚሆን ታምኖበታል” በማለት መረጃ መጥለፍ የዩኒቨርስቲዎችና የትምህርት ሚኒስቴር ሥራ እንደሆነ አድርጎ ያቀርባል።
      የማንዋሉን ዓላማዎች በሚገልፀው ክፍል ደግም “… የከፍተኛ ትምህርት የትምህርት የልማት ሰራዊት ግንባታን ወይም የፓለቲካ ሰራዊት ግንባታ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተደራጀና በተናቀጀ ሁኔታ በማቀጣጠልና በማስቀጠል … ምርጫ 2007 ውጤታማ ለማድረግ እና የኢህአዴግን አሸናፊነት ለማረጋገጥ ነው” በማለት ተቋማቱን የኢህአዴግ የምርጫ መሣሪያ መሆናቸውን፤ ግባቸውም የኢህአዴግ አሸናፊነትን ማረጋገጥ መሆኑ ይገልፃል።
      በገጽ 3 ላይ ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች “በኢህአዴግ ላይ ያላቸው አቋም የወረደ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማንኛውም ተቃውሞ ድምፅ ከተጠሩ፤ ሰልፍ የሚያደምቁ፤ ተቃውሞን ከግብ ለማድረስ ሁነኛ መሳሪያ ናቸው። ተማሪዎች በየትኛውም ሐገር እንደታየው አደባባይን የመያዝ ህዝብን አስተባብረው ለተቃውሞ የማሳደም እድላቸው የሰፋ በመሆኑ ከዚህም ሲያልፍ፤ የኢህአዴግ ምከታን በመቃወም ለጠላት ጎራ ተሰልፈው የመታጠቅ እድላቸው ከፍተኛ ነው” ሲል “በወጣቱ እጠላለሁ” የሚለው የህወሓት/ኢህአዴግን ስጋት አፍረጥርጦ ያወጣል። ትንሽ ወረድ ብሎ ደግሞ “በተለይ በአሁኑ ሰዓት ፈተና ላይ የጣለን የምርጫ ጉዳይ እንደምናሸንፍ ቃል የተያዘለት ቢሆንም፤ ፈተናዎች የሚፈጠሩት በህዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግስት ክንፍ አይቀለበስም ብሎ ማሰብ አይቻልም። በዚህም ቀድሞ መዘጋጀት ያለበት እና ለሁከት እና ለብጥብጥ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው የህዝብ ክንፍ የተማረው ሃይል ሊሆን ስለሚችል ሊታሰብበት ይገባል” ሲል በተማረው ወጣትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሠራተኞች ላይ ያለው ጥርጣሬና ፍርሃት ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ይገልፃል።
      የ2007 ምርጫ በህወሓት ሹማምንት ላይ የፈጠረውን ጭንቀት በዚህ ሰነድ ላይ በገሀድ የሚታይ በመሆኑ እያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር በጥንቃቄ ሊነበብና ሊተነተን የሚገባው ነው። ለምሳሌ በገጽ 6 ላይ ስለዩኒቨርስቲ ተማሪ ሲገልጽ “የአመፅ እና የብጥብጥ መነሻ ሊሆን የሚችል ሀይል መሆኑን በአክራሪዎች ሲጠለፍ፤ ከመንግስት ሃይማኖቱን እየመረጠ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ፤ በጅማ ዩኒቨርስቲ፤ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ እና በሌሎችም ትምህርቱን ትቶ ሲኮበልል ተመልክተናል” ይላል። ለተማሪዎች፣ ከመንግሥት እና ከሃይማኖት አንዱን እንዲመርጡ ተደርጎ ሃይማኖታቸውን የመረጡ መኖራቸውን እና ይህ ደግሞ አደገኛ ነገር መሆኑን ነው ይህ ዓረፍተ ነገር የሚነግረን። ለመሆኑ ይህ ምን የሚሉት ምርጫ ነው? በእንዴት ያለ ሥርዓት ነው ዜጎች ከመንግስትና ከሃይማኖት አንዱን ምረጡ የሚባለው? እንዲህ ዓይነት ምርጫ ቀርቦ ሃይማኖትን መምረጥ እንዲህ ክፉ ነገር የሆነው ለምንድነው? ይህ ጉዳይ ብቻውን ብዙ የሚያነጋገር ነገር አለው።
      በገጽ 8 ላይ ደግሞ “ከፍተኛ አመራሩ ተቋማዊ ለውጥ እንዲሁም የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ ቴክኒካዊ ሳይሆን ፓለቲካዊ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝቦ ካለእርሱ ባለቤትነትና ቀጥተኛ ተሳትፎ ሰራዊት መገንባት እንደማይቻል በመገንዘብ የመሪነት ሚናውን ካለምንም ማወላዳት መወጣት ይጠበቅበታል” በማለት እየተሠራ ያለው የፓርቲ ወገንተኛ የሆነ ፓለቲካ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የትምህርት ተቋማት መሪዎች ዋና ተልዕኮ ትምህርት ማስተማር ሳይሆን የወያኔ ፖለቲካን ማስፈጸም መሆኑን ምንም ሳይጎረብጠው ፍርጥርጡን ያወጣዋል። ትንሽ ወረድ ብሎም “የጋራ መግባባት የምንለካው በመጀመሪያ ለምርጫው የኢህአዴግ የድጋፍ የድል ሰራዊት ብዛት ነው” በማለት ከላይ ያለውን በማጠናከር ወገንተኛነቱም ለኢህአዴግ መሆኑ ያውጃል። በመጨረሻም “ … ሁሉም የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው ለምርጫው በሚያዘጋጁት የድጋፍ ሃይል ይወሰናል” በማለት የአካዳሚ ነፃነት ብቻ ሳይሆን የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓትን ለቀብር ያዘጋጃል።
      ይህ ነው የህወሓት የትምህርት ፓሊሲ! የዩኒቨስቲዎች ቁጥር ለማመን በሚቸግር መጠን ቢጨምር፤ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ በብዙ መቶኛዎች ቢያድግ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው። በእንዲህ ዓይነቱ ፓሊሲ ከተገነባ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ይገኛል የምንለው ፋይዳ ምንድነው?
      ህወሓት በገሀድ በጠላትነት የፈረጃቸው የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ መምህራንና ሠራተኞች ይህንን አሳሳቢ ጉዳይ በአጽንኦት እንዲመለከቱ ግንቦት 7፣ የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያሳስባል። ትውልድንም የትምህርት ሥርዓቱንም የማዳን ግንባር ቀደም ኃላፊነት በተማሪዎችና በመምህራን የወደቀ ሸክም ነው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል። መላው የትምህርት ሥርዓት ለአንድ ፓርቲ የምርጫ ውድድር መሣሪያነት ሲውል ማየት እና የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች የሥራ አፈፃፀም የሚወሰነው ለገዢው ፓርቲ ባስገኙት ድምጽ ብዛት ነው መባሉ፤ እነሱም ይኸንን ተቀብለው መሥራት መቀጠላቸውን የመሰለ አሳፋሪ ነገር በአካዳሚያ ውስጥ የለም። የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን ይህን ውርደት መቀበል የለባቸውም። ሰነዱ ህወሓት ከፍተኛ ትምህርትን የሚመለከትበት ዕይታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነውና ለምርጫ ወቅት ብቻ የተዘጋጀ የአጭር ጊዜ መመሪያ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ይህ ሰነድ ህወሓት፣ ተማሪዎችንና መምህራንን እንደጠላት፤ ተቋማቱን ደግሞ ጠላትን እንደመቆጣጠሪያ መሣሪያ እንደሚመለከት፤ ይህ ዕይታው ደግሞ ቋሚ መሆኑ በግልጽ ያሳያል። በህወሓት ዕይታ ከተገነቡ ተቋማት ምን ዓይነት ትምህርት ይገኛል?
      የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የትምህርት ኃላፊዎችና ፕሬዚዳንቶች ሆይ! ለገዛ ራሳችሁ ክብር፣ ለአካዳሚ ነፃነት፣ ለትውልድ ስትሉ በዚህ መመሪያ ላይ አምጹ! “እንቢ፣ አሻፈረን፣ በዚህ መመሪያ አንገዛም” በሉ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችሁ ይቆማል።
      ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!


        ginbot7.org