ለለውጥ የጓጔው ወጣት ዱር ቤቴን ምርጫው ማድረጉ የኢትዮጵያ ሁኔታ የግድ የሚለው ነው::በኢትዮጵያ ሌሎችን የአፍሪካ አገሮች የሚጎበኛቸው ህዝባዊ ነውጥ በከተማ ብቻ ይከሰት ይሆን ? ወያኔ ወጣቱን አጋር አልባ ሆኖ ሲያገኝው ያለርህራሄ እየቀጠቀጠው ነው።የህወሃት መሩን መንግስት ጭካኔ የተመለከተ ከከተማ የተሻለ አማራጭ ያስባል ማለት ያስደፍራል:: መንገዱም ዛሬ የሰጠ ነው:: አንድ ዘዴ ካልሰራ ሌላ ዘዴ መሞከሩ:ወይም ዘዴዎችን በጣምራ መሞክሩ የግድ ነው:: ለወያኔ የሳት እራት ከመሆን ከገጠር እሳት ጭሮ ወደከተማ መግባትን በአንክሮ ማሰብ የግድ ይላል።
2015 የወያኔ የጭንቀትና የፖለቲካ ውጥረት የሚጦዝበት ዓመት ሊሆን ይችላል። ይህ እንዲሆን ደግሞ የሚኬድበትን መንገድ መፈተሽን ይጠይቃል:: ወያኔ ከስልጣኔ የራቀ በመሆኑ ለህዝባዊ የከተማ እምቢተኝነት ያለው ምላሽ ዘግናኝ ጭካኔ ነው። ህወሃት መሩ መንግስት ይሄው ዛሬ ሌሎች አገሮች እንደሰማነው: እንዳየነው ያለ ህዝባዊ አመጽ ሳይጎረብጠው እንዳሻው ሲረግጥ ሲዘርፍ ሲያስር ይሄው ሁለት አሰርት ዓመታት አለፉ። እካሁን ድረስ ደግሞ እስሩ ድብደባውና ግድያው ካገር ገፍቶ ማሰደዱ ሰርቶ ነበር:: ዛሬ ለየት የሚለው እነዚህ ሁሉ እኩይ ተግባራት የሚሰጡት ውጤት ህዝብን ከማስፈራራት ይልቅ አደፋፋሪ መሆናቸው እየጨመረ መሄዱ ነው። ህዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያ አይቀሬ ነው:: ይህን ደግሞ የመንግስቱ ተችዎች ብቻ ሳይሆኑ ራሱ ህወሃት መሩ መንግስት ያመነው ነው። 2015 የወያኔ ጭንቀትና የፖለቲካ ውጥረት የሚጦዝበት ዓመት ሊሆን የሚችለው የከተማው ህዝባዊ አመጽ በገጠር በመሳሪያ የታጀበ አመጽ ጋር ሲዋሀድ ብቻ ነው። ህወሃት መሩ መንግስት እንቅልፍ የሚያጣበትም አቢይ ጉዳይም ይህ ብቻ ነው:: ለፈረንጆች ያመነው “ያለመረጋጋት አደጋ” የሚለው ይህኑ ነው::
ያለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ያመጡት: ለህዝቡ የፈየዱት ምንም የለም:: በኢትዮጵያ በአፍሪካም በጥቅል ምርጫ የለሽ ዲሞክራሲ ዛሬ ምንም አላመጣም ።ዛሬ የህወሃት አብዮታዊ ዲሞክራሲም አሰልቺ የሞኝ ዘፈን ነው:: በስልጣን መባለግ:ስርቆት:ጭካኔ:ተንኮል የተስፋፋባት ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች እንደሆነ ለመናገር የሚክብድ አይደለም። በሴኒጋል ቡርኪና ፋሶ ቶጎ እና ቻድን ይዞ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ህዝብ በቃ ብሎ መነሳቱ በኢትዮጵያም ጊዜውን ብቻ የሚቆጥር ትዕይንት ያደርገዋል:: ሆኖም በእነዚህ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች እንደሆነው በኢትዮጵያም በተመሳሳይ መልኩ አመጹ ተነስቶ የህወሃት መሩ መንግስት ፍጻሜ ላይሆን ይችላል? የህወሃት መሩ መንግስት የከተማ አመጽን ለመግታት ሀይልና ብቃት ልምድ ጨምሮ አለው። ወታደራዊ ሀይሉንም በአስተዳደር ተብትቦ ባይነቍራኛ የሚጠብቀው ነው:: በግብጽና በቡኪና ፋሶ እንደሆነው ወታደራዊ ሀይሉ ለከተማው ህዝባዊ አመጽ ቶሎ የሚደርስ ደጀን መሆኑን ለመናገር ዛሬ አስቸጋሪ ነው:: ወታደራዊ ሀይሉንም እንደ ህዝቡ ተመሯልና ብረት ያነሱ ሀይሎች አስተማማኝ ደጀኖች ከሆኑት ግን ልቡ ክህዝቡ መሆኑን መናገር ፈጽሞ አይቸግርም:: ለምን ለሀብታም ጄኔራል ብሎ ይሙት? የሌባ ጎሬ ለሆነው ለህወሀት ይሙት ? መሞት ለአገርና ለራስ ክብር ነው::
ዛሬ በአዲስ አበባ የሚታየው ህዝባዊ አመጽ የመሪዎቹንና የተከታዮቹን ጀግንነት አስደናቂ ቢያደርገውም ትርፉ ለወያኔ ነው:: የወጣውን ሀይል ይቀጠቅጣል ያልወጣውን ሀይል ያስፈራራል። ይህ ሁኔታ ግን እንዲህ ሊቀለበስ ይችላል:: በገጠር የታጠቁ ሀይሎች በጥቃቅን ድሎች መጀመሪያ ኋላም አቢይ ድሎች ተቀዳጅተው ሲበረቱ ለከተማ አመጽ ደጀን ይሆናሉ:: የመንግስት ሀይላትም እንደወትሮ መግደል ጊዜው ማብቃቱን ያስተውላሉ ወይም ተጠያቂነትን ማሰብ ይጀመር ይሆናል:: ይህ ሲሆን የህወሃት አብዮታዊ ዲሞክራሲም ሞትን ተቃረበ ማለት ነው። ደርግ የክተማ አመጽን ደምስሶ አስራሰባት ዓመት ስለገዛባት አገር ወያኔም\ህወሀት ከገጠር ወደ ከተማ ስለገባባት ኢትዮጵያ ስለሆነ ሃሳብ የምንለዋወጠው ይህን ማለት አይክብድም።አያከራክርም:: ጣሊያን ኢትዮጵያን በደፈረበት ዘመን ጣሊያን የተመረረው በገጠር ባሉ አርበኞች ነበር:: የውስጥ አርበኛው እየረዳ:: አዲስ አበባ በሳት ቀለበት ውስጥ ነበረች:: ለለውጥ የጓጔው ወጣት ዱር ቤቴን ምርጫው ማድረጉ የኢትዮጵያ ሁኔታ የግድ የሚለው ነው:: ፈረንጅ ለወያኔ የለገሰውን አድማ መበተኛ መሆን ማብቃት አለበት:: በፈረቃ በወያኔ መቀጥቀጥ ይብቃ:: ሌላ መንገድ ይታሰብ!
በአረብ አገራትና ክሳሃራ በታች በሚገኙ አገራት ሙስናው ፡የኑሮ ችግሩ፡በስልጣን ብልግናው፡ስራ አጥነቱ፡ ተስፋ ማጣቱ አይደለም አመጹን ያነነደደው እሳት ? ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ ባሰ እንጂ ተሻለው ብሎ የሚል ማን ነው? የህወሃት መሩ መንግስት ራሱ ተገንዝቦ ለፈረንጆች ባደባባይ አምኖአል። ይህን ራሱ ያመነውን የተናገሩ:የጻፉ ጋዜጠኞች ግን በእስር ይማቅቃሉ። የድንበር ጦርነቱ እና ረሀቡ ከሁለት አሰርት ዓመታት በላይ የተዳፈኑ እሳት ናቸው። ከሁለት አሰርት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ በጤና: በትምህርት: በቴክኖሎጂ እጅግ ኋላ መቅረትዋ በማስረጃ እየተደገፋ ተጽፏል። ኢትዮጵያ በሁሉም የድህነት መለኪያ ዝርዝር ትታወቃለች:: ከወያኔ መወገድ ማግስት ለሚከተለው መዘጋጀት ያገር ወዳዱ ሁሉ ከፍ ያለ ግዴታ ነው::ከባዱም ፈተናም ይህ ነው።
በኢትዮጵያ ይህ መምጣቱን የምንጠብቀው ለውጥ ብቻ ሳይሆን በለውጡ ማግስት የሚክተለው ግዝፈት ያለው ችግር ነው አሳሳቢው:: እነመለስ የተራቆተ መንግስት አልተረከቡም:: በጎሳ የተሸነሸነ አገር አልጠበቃቸውም። ለሽግግር የሚያግዝ የተማረ የሰው ሀይል አልቸገራቸውም።ስልጣንን መከታ አድርገው በሚሊዮን ያካበቱ አልነበሩም:: ከውጭም አይዟችሁ ያሉዋቸው ብዙ ነበሩ:: ሁሉም አልጋ ባልጋ ነበር። ትልሙ የወያኔን ስንብት እየደገሱ ሽግግሩ ከወዲሁ ማሰብና መዘጋጀት ነው::
ያለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ወደኋላ ሲስተዋሉ ለህወሃት መሩ መንግስት ባለስልጣኖችና ደጋፊዎቻቸው የተመቸ ኑሮ የመሰረቱባቸው ሀብት ያካበቱባቸው ዓመታት ናቸው። ክዚህ ምቾት በምርጫ አሰናብታቸዋለሁ በሰላም እሸኛቸዋለሁ የሚል ካለ ቅዠት ውስጥ ያለ: ሰለወያኔ ግፍ ያልሰማ ወይም ይቅርታ ጠያቂ ነው:: ወያኔን በከተማ ለክብሩ:ለነጻነቱ:ለሀይማኖቱ ላገሩ በማለት ተጋፍጦ ይገኛል። ኢትዮጵያ የዚህ ትውልድ ናት
ዛሬ በዚህ ርእስ ለመጸፍ እጅግ የሚያደፋፍረው አንድ ሰው አለኝ የሚለው የተለየ መረጃ ወይም የተንታኝነት ችሎታ ሳይሆን ራሱን ችሎ የህወሃት መሩ መንግስት ተግባሮች ናቸው። አንድ ትውልድ በክተማ እንዳለ ቀርቷል:: ዛሬ “ያ ትውልድ” እየተባለ የሚነገርለት። የደርግን የግፍ በትር እነመለስ በዱር አሳለፉት:: ዛሬም እሾህን በሾህ! በዚህ መነጋገር መልካም ነው::
ክቢላል አበጋዝ
No comments:
Post a Comment